የሞተር አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ- ከ6 ሺህ ሊትር በላይ ሕገወጥ ናፍጣ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ክልከላ ማድረጉን አስታወቀ።

ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር በማሰብ፤ አዲሱ ጥናት ተጠናቆ እስኪወርድ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጪ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እገዳ መጣሉን ነው የገለጸው።

ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ከትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው ጀመረ ያሳያል።

በሕገ ወጥ መንገድ ሊጓጓዝ የነበረ ከ6 ሺህ ሊትር በላይ ናፍጣ በቁጥጥር ስር ዋለ።

መነሻውን ባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በማድረግ ወደ ሰቆጣ ሊጓጓዝ የነበረ ከ6 ሺህ ሊትር በላይ ናፍጣ ሚያዝያ 5/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00 በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በመምሪያው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ክፍል ኀላፊ ኢንስፔክተር ተስፋየ ፍሬው እንዳሉት 6 ሺህ 750 ሊትር ናፍጣ ላይ የታሸገ ውኃ በማድረግ ከባሕር ዳር ወደ ሰቆጣ ሊጓጓዝ ሲል በፀጥታ መዋቅሩ እና በማኅበረሰቡ ርብርብ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ተጠርጣሪውም በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብለዋል።

መሰል ሕገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ማኅበረሰቡ የተለመደውን ጥቆማ የመስጠት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኀላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

Leave a Reply