ትህነግ ያሰማራቸው 247 የጉህዴን ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 247 የጉህዴን ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ።

የወረዳውን የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እያረጉ እንደሚገኙ የገለፁት፣ የወረዳው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ ደምስ ዳኘ እነዚህ የጥፋት ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ከቀረበላቸው የሠላም ጥሪ በተጨማሪ፤ በአካባበቢው ህግን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው የኦፕሬሽን ሥራ ተገደውም ጭምር ብዙዎች እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወረዳውን ሰላም ለማስከበር በግዳጅ ላይ ተሰማርተው የሚገኙት የመከላከያ ስራዊት፣ ልዩ ሀይል እና የሚሊሻ አባላት በቅንጅት እየሰሩ በመሆናቸው በርካታ የጥፋት ቡድኑ አባላት በተለየ ሁኔታ ከነጦር መሳሪያቸው እጅ እየሰጡ መሆናቸውን የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የኮማንድ ፖስት ሃላፊውን ጠቅሶ ዘግቧል።

Leave a Reply