ፊቼ ጫምባላላ- ይከበራል

  • የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫንባላላን በዓል በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል

የዘንድሮውን የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫንባላላን በዓል በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቃቸውን የሲዳማ ክልል ባህል፣ ቱርዝምና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው አስታወቁ።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የቢሮው ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የፊቼ ጫንባላላ በዓል ከሲዳማ አልፎ በUNSCO መመዝገቡ የተመዘገበ ነው። በዓሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአለማችን ላይ በተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ምክንያት በጉዱማለ ሳይከበር መታለፉን ገልጸዋል።

በሲዳማ ክልልም ሆኖ በአገርቱ በተለያዩ ከተሞች በድምቀት ለማክበር የክልሉ መንግስት በዓሉን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተደራጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል ያሉት የቢሮው ኃላፊ፣ ፊቼ ጫንባላላ በዓል ሲዳማ ካሉት ግዙፍ ማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱና ዋነኛ ነዉ ብሏል።

እንደ ቢሮው ኃላፊው ገለጻ የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫንባላላ በዓል ከሳባት አመት በፊት በUNSCO’ መመዝገቡን አስታዉሰዉ ፣ የፊቼ ጫንባላላ ባዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል።

ላኦ’ የተሰኘ በዓሉ የሚታወቅበት ቀን የከዋከብትና ጨረቃን ውህደትን በማንበብ የሚወሰን ይሆናል ያሉት ኃላፊው ህዝቡ በዓሉን ያለ አንዳች ችግር እንዲያከብር የተለያዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልጸዋል።

ለበዓሉ አከባበር የቅቤ ፤ የቆጮ ፤ ሽማንግለወች የሚደረግ ለህዝብ የሚጸልዩበት እና በአገርቱ በሽታ ካለ እሱን ፈጣሪ እንድያስወግድ የሚሟጸኑበት ና መጭዉ አመት የልላሜና የተስፋ እንድሆን የሚመኙበት ፤ የተጣሉ ካሉ የምታረቁበት ህደቶች ከቅድመ ዝግጅቶች መካከል የምገለጹ መሆናቸውን አብራርተዋል ።

በዓሉም ከሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሚከበር ይሆናል።

በአድሱ አዶላ (ሀዋሳ)

See also  Toward a Peaceful Order in the Horn of Africa - ABIY AHMED

Leave a Reply