“የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን”

ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት አስመልክቶ እንዳሉት፤ የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ እኩይ አካላትን አንታገስም ብለዋል ርዕሰ መሥተዳድሩ።

ርእሰ መስተዳድሩ ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት፡፡

ይህ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ነው ያሉት።

የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ክትትል አድርጎ እርምጃ ይወስዳል ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply