በመላው አገሪቱ የአክራሪዎች ሴል አባላት እየተለቀሙ ነው፤ አዲስ አበባ ንብረት ያወደሙ በካሜራ እየተለዩ ነው

በመላው አገሪቱ የአክራሪዎች ሴል አባላት እየተለቀሙ ነው፤ አዲስ አበባ ንብረት ያወደሙ በካሜራ እየተለዩ መሆኑ ታውቋል። ክልሎችና ከተሞች የማተራመሱ ሴል አባላት የሆኑትንና በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቁትን እየለቀሙ መሆኑ ተሰማ። ልጆች ያሉበትን ቦታ ወላጆች እንዲያውቁ አቅጣጫ እየተጠቆመ ነው።

ከወላጆቻቸው ጋር የተለያዩ ሕፃናት ያሉበት ቦታዎች!!

በአዲስ አባባ ስታዲየም እና አካባቢው የኢድ አካባበር በአል ላይ ለመሳተፍ መጥተው ከቤተሰባቸው ጋር የተጠፋፉ በርካታ ህፃናት በሚከተሉት ቦታዎች ይገኛሉ:-

1. በጀርመን እና ፍልውሃ መስጂድ

2. በስቴዲየም ቀይ መስቀል ፣

3 ካሳንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ

4. ለገሀር እና

5. ደምበል ፓሊስ ጣቢያ ስለሚገኙ ወላጆች ወደ እነዚህ ቦታዎች በመሄድ ልጆቻችሁን ማግኘት ትችላላችሁ ።

ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ከወላጆቻቸው ጋር የተለያዩ ሕፃናት እንዲገናኙ እንረባረብ።

በዛሬው ዕለት የኢድ ሶላት ከመደረጉ በፊት በተነሳው ረብሻ መስቀል አደባባይ ዙሪያ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቢሮዎች ተሰባብረዋል። ድንጋይ ወረዋሪዎቹ የእምነት አባቶች ጉዳት እንዳያደርሱ ቢለምኗቸውም ንብረቶችን ከመሰባበር ሊታቀቡ እንዳልቻሉ ምስክሮች አስታውቀዋል።

“ሃብታሙ ምናለ ቅኝት ባረኩበት ወቅት ያገኘኹት ምላሽ” ሲል የጉዳቱን ልክ በምስል አስደግፎ በግል የፌስ ቡክ ገጹ “ዓይናችን እያየ ብዛት ስላላቸው መከላከል አቅቶን የምንጠብቀውን መሥሪያ ቤት መስታውት ሰባብረውታል” ሲሉ በየድርጅቶቻቸው በጥበቃ ላይ የተሰማሩ አባት እንደነገሩት አመልክቷል።

ከፖሊስ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ድንጋይ ሲወረወሩና ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ በምስል እየተለዩ ነው። የጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መረጃውን በምስል የያዘ በመሆኑ በጥፋቱ የተሰማሩ በሰዓታት ውስጥ እስከ ወይም ማምሻው ድረስ ህግ እንደሚይዛቸው ተመልክቷል።

ክልሎች በሙሉ በሚባል ደረጃ በዕምነት ስም የሚፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉ አገር የማተራመስ ተግባር እንደማይታገሱና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ እያስታወቁ ባለበት በአሁኑ ሰዓት፣ በፌደራል ደረጃ ለጸጥታ ሃይሉ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል። በየክልሉ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ያለው የጽንፈኞች ሴል እየተያዘ መሆኑም ታውቋል። እርምጃው ከዚህ በፊት ከነብረው በተለየ መልኩ የከረረና የማያዳግም እንደሚሆን ነው የተሰማው። ሕዝብ በምሬት መንግስት በጽንፈኞች ላይ እገሌ ከገሌ ሳይል የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ሲጠይቅ እንደነበር ይታወሳል።

ጎንደር ላይ ሕዝብን ያሳተፈው ዘመቻ ውጤታማ እንደሆነና ሰማ ፈላጊው ሕዝብ የተሳተፈበት ዘመቻ ውጤት እንዳስገኘ የገለጹ አዲስ አበባን ጨምሮ ሁሉም አካባቢዎች ሕዝብን አሳትፈው ጥቂት አክራሪዎችን ማስወገድ እንደሚችሉ እየመከሩ ነው። ከሙስሊምም ሆነ ከከርስቲያን አክራሪዎችን መሸከም ሊበቃ እንደሚገባ፣ ማንም ሆነ ማን ማስረጃ ከተገኘበት ሕግ ፊት ሊቀርብ እንደሚገባ እነዚሁ ወገኖች እየጠየቁ ነው። ላምትንንና የህዝብ ንብረትን ማውደም ተገቢ ቅጣት እንደሚያሻውም እየተመለከተ ነው።

” የመንግሥት መኪና አቁሜ ቤት ገብቼ ነበር። ረብሻውን ሰምቼ ስወጣ መኪናዬን ከበው እናቃጥላት እያሉ ነበር። ለምኜ መኪናዋን ለማትረፍ ችያለሁ” ሲል አንድ የመንግሥት መኪና ተቀጣሪ ሾፌር እንዳናገረው አመልክቷል።

“እንኳን የግለሰቦችን የመንግሥት ተቋማትን መከላከል የሚያስችል አቅም አልነበረንም!” በሚል ፌዴራል ፖሊስ አባላት መናገራቸውን፣ “ና ውጣ አንተ የውሻ ልጅ ሲሉኝ ነበር” በሚል የትልቅ ተቋም ጥበቃ መግለጹን ሃብታሙ በፊስ ቡክ ገጹ አኑሯል።

ይህ በየትኛውም መስፈርት ሙስሊሙን እንደማይወክል በመግለጽ ድምጻቸውን የሰጡ ” መንግስት እንዲህ ያለውን ድርጊት በህግ ቢያርቅ የበኩላችንን እንወጣለን” ብለዋል።

መስታውት የተሰባበረባቸውን ተቋማት ከቦሌ ወደ ፒያሳ ባለው መንገድ ብቻ ያሉትን በመጠኑ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል። ሃዲያ ሱፐር ማርኬት ፣የኢዜማ ቢሮ፣ የውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት፣ ሲንቄ ባንክ፤ ወጋገን ባንክ 2 ብራንቾች፣ ወጋገን ባንክ ኤቲኤም፣ የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅት፣ ራንዴቩ፣ LA patissere cafe፣ ቤልሞን ካፌ፣ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየሙ ከሁለት መኪናዎቹ ጭምር፣ ከቦሌ ወደ ስታዲየም ያለው እካፋይ የመንገድ ብረት፣ የመስቀል አደባባይ የተወሰኑ መቀመጫ ወንበሮች፣ የመስቀል አደባባይ ፖርኪንግ መግቢያ በመስታውት የተሰራ ቤት፣ሞደን ሴራሚ ፣ብሔራዊ የጀግኖች ሕጻናት አምባ፣ ኢትዮ ባስ ትኬት ቢሮ ፣ አባይ ባስ ትኬት ቢሮ ፣ መስቀል አደባባይ የትራፊክ ማረፊያ ፣ክየመስቀል አደባባይ ፖሊስ ኮሚኒቲ ቢሮ

ምስጋና ለሃብታሙ ምናለ ፌስ ቡክ ገጽ

You may also like...

Leave a Reply