“በትግራይ ኢኮኖሚው ኮንትሮባንድና አራጣ ሆኗል” ሳልሳይ ወያኔ

“በትግራይ ክልል ኢኮኖሚው ኮንትሮባንድና አራጣ ሆኗል” ሲሉ የሳልሳይ ወያኔ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክንፈ ሃዱሽ ተናገሩ። ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ «ሙሉ በሙሉ» መዘጋቱንና የሽግግር መንግት እንዲቋቋም የጠየቁ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተሳደዱና አፈና እየተደረገባቸው መሆናቸውን አመልከቱ።

በትግራይ ወቅታዊ ጉዳት መግለጫ መስጠታቸውን ጠቅሶ የጀርመን ድምጽ ከመቀለ ባሰራጨው ዘገባ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ” አሁን እንደ ህዝብ ወደ ከፋ ደረጃ ደርሰናል” ሲሉ ተደምጠዋል። “ድሮም አልጠቀመም፣ ወደፊትም አይጠቅምም” ሲሉ ድምጻቸውን ያሰሙት አቶ ክንፈ ትግራይ በፍትህ፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ችግር መተብተቧን ጠቅሰው “በትግራይ ክልል ኢኮኖሚው ኮንትሮባንድና አራጣ ሆኗል” ብለዋል። አራጣ ሲሉ የጠሩትንና ኮንትሮባንድ ያሉትን ህገወጥ ተግባር ሲያስረዱ በዝግጅት ክፍሉ አልተሰማም።


‹‹በትግራይ በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው እየተሸጡ ነው›› በትግራይ ክልል የመድኃኒት እጥረት ቢኖርም መቀሌ ከተማ ውስጥ ግን አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው መድኃኒት ሲሸጡ አይተናል፤በመቀሌ በህዝብ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እጥረት ቢኖርም በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው እየተሸጡ ነው፡፡


ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተባለው ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት በክልሉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩን ገልጾ ባዘጋጀው መግለጫ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በመቐለ የጠራውና ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች የተገኙበት ሕዝባዊ ስብሰባ በታጣቁ ኃይሎች መበተኑን አመልክቷል። በተለይም በትግራይ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የጠሩ የፖለቲካ ፖርቲዎች ተለይተው ዓፈና እየደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል። ይህን አካሄድ ከፖለቲካው ምህዳር መዘጋት ጋር ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ “ትናንት አልጠቀመንም፣ ወደፊትም አይጠቅመንም” ሲል ኮንኗል። ትግራይ የአንድ ድርጅት ንብረት መሆኗን የማይቀበሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ድርጊቱ ሕገ ወጥና ፀረ ዴሞክራሲ ብሎታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፖርቲው የትግራይ ክልል በአስከፊ ፖለቲካዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል። ለዚህም ተጠያቂዎች ያላቸውን ሁለት አካላት “ውስጣዊና ውጫዊ” ሲል ጠቅሷል። ለችግሩ ተጠያቂዎች ከውጭ ትግራይ ክልል ላይ «መዘጋትና ከበባ» የጣለውና ” ጠላት” የተባለው የኢትዮጵያ መንግስት ሲሆን፣ ከውጭ ደግሞ «ትግራይን መምራት አልቻለም» ያለውን ትህነግ እየፈጸመ ያለውን የከፋ ብሎታል።

See also  አየር ሃይል የተመረጠ የታጣቂ ማሰልጠኛና መሳሪያ ማከማቻ አጠቃ

በትግራይ ያለውን ሃብት በአግባቡ ተጠቅሞ ውስጣዊ ሁኔታዎችን ለማሻሻል አቅምም ሆነ ፍላጎት እንደሌለው ጠቅሰው ትህነግን የኮነኑት አቶ ክንፈ ፓርቲያቸው ለወደፊቱ ያሰበው ምን እንደሆነ አላስታወቁም። የጀርመን ድምጽ የትህነግን ሃሳብ ለማካተት እዛው መቀለ ከተማ ባለው ዘጋቢ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳካ ተመልክቷል።

በቅርቡ በትግራይ ዝርፊያና ህገወጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን በዩቲዩብ ዜና ማሰራጨቱ የሚታወስ ነው።

Leave a Reply