81ኛዉ የአርበኞች ቀን- ከዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ በመላቀቅ አገርን ማፅናት

81ኛዉ የአርበኞች መታሰቢያ ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀ መግለጫ

ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ ጦርነቶችን አካሂዳለች፡፡ ጠላቶቿ የተኙላት ጊዜ የለም፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ጦርነት ፈልጋ እና ተመኝታ፣ የሌላዉን ሉዓላዊነት ጥሳ ወረራ ፈፅማ አታዉቅም፡፡ ሁሌም የራሷ በሆነዉ ሃብት ወይም ሌላ ጉዳይ በጠላቶቿ ትጠቃለች፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም ጦርነቶች በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡ ጦርነቶቹን ያሸነፈቻቸዉ በጠላቶቿ ድክመት ወይም በታጠቀቻቸዉ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ብልጫ አይደለም፡፡

ሁሌም ጠላት ሲመጣ በሚሰባሰቡትና ጠላትን በአንድነት በሚመክቱት ጅግኖች ልጆቿ ነዉ፡፡ ሁሌም ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ስትነካ ትዕግስት የሌላቸዉ ዉድ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት በደምና በአጥንታቸዉ የአገራቸዉን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት ሳይደፈር አስከብረው አቆይተዋታል፡፡

በታሪክ ሁልጊዜ ከሚታወሱት የጀግንነት ታሪካችን አንዱ ከስምንት አስርት-ዓመታት በፊት ለአገር ክብርና ለሕዝቦች ነፃነት የአባት አርበኞች የፈፀሙት ገድል ነዉ፡፡ በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል የተደረገዉ የአድዋ ጦርነትና ጦርነቱ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት መፈፀሙ በወራሪዎች ዘንድ ከፍተኛ የዉርደት ስሜትና ፀፀት አስከትሏል፡፡ ሽንፈቱ በወቅቱ የበቀል ስሜትን ቀስቅሷል፡፡ ከስሜትም አልፎ የአገዛዝና የአስተሳሰብ ለዉጥን አስከትሏል፡፡

ከነዚህም ለዉጦች መካከል አንዱ የፋሽስታዊ አስተሳሰብ መወለድና የመሪዉ ቤኒቶ ሙሶሎኒ የመንግስት ስልጣን መቆናጠጥ ነበር፡፡ ይህ ፋሽስታዊ ብሔርተኝነትና መሪዉ እንደ ግብ ከያዘዉ አንዱ እና ዋነኛዉ ኢትዮጵያን ዳግም በመዉረር ከሽንፈቱ ድባቴ በመላቀቅ የጣሊያንን ታላቅነት መመለስ የሚል ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ከ40 ዓመት የአድዋ ድል በኋላ ፋሽስታዊ አገዛዙ እ.አ.አ በጥቅምት 1935 ዓ/ም ኢትዮጵያን ወረራት፡፡

በወቅቱ የጠላት ጦር በያዘዉ የጦር መሳሪያና በሰለጠነ የወታደር የበላይነት ምክንያት ለጊዜዉም ቢሆን የወገን ጦርን ለመበተን ቻለ፡፡ ሆኖም ግን ለባርነትና ለጠላት እጅ መስጠጥ የማያዉቁ ኢትዮጵያዉያን ራሳቸዉን በማደራጀት በአዲስ መልክ በጠላት ላይ ተነሱ፡፡ ቀያቸውንና ንብረታቸዉን ትተዉ ዱርና ገደሉን ቤታቸዉ አደረጉ፡፡

እንደ ስሙ የአንበሶች ስብስብ የሆነዉን ‘የጥቁር አንበሳ’ የተሰኘዉን የአርበኞች ስብስብ መሰረቱ፡፡ አርበኞቹ በመላ ኢትዮጵያ በብሔርና በቋንቋ ሳይለያዩ በሁሉም አካባቢዎች በመደራጀትና በመንቀሳቀስ ጠላትን እንቅልፍ አሳጡት፡፡ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ጠላትን እረፍት በመንሳት እ.አ.አ ግንቦት 5/1941 አርበኞቹ የነፃነት ታጋዮች በጠላት ላይ ድል ተቀዳጁ፡፡ ለአምስት ዓመታት አገር ለቀዉ ዉጭ አገር በስደት የቆዩት ንጉሱም በድል ወደ አገራቸዉ ተመለሱ፡፡

ዕለቱም እስከ ዛሬ ድረስ የአርበኞች የድል ቀን በመባል ይከበራል፡፡ ጀግኖች አርበኞችም ለአገራቸዉ ክብርና ለሕዝቦቿ ነፃነት ላደረጉት ተጋድሎ በየዓመቱ ሚያዝያ 27 ቀን ይወደሳሉ፣ ይታወሳሉ፤ ለዘለዓለም በትውልድ ሲወደሱም ይኖራሉ፡፡
የዘንድሮዉን 81ኛዉ ዓመት የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ስናከብር የድሉን ትሩፋቶች በማጉላትና ለትዉልድ በማስተላለፍ መሆን ይኖርበታል፡፡ ኢትዮጵያ ከሩቅና ከቅርብ በታሪካዊ ጠላቶቿ ስትጠቃና ስትወረር ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡

ምንም እንኳን ፈልጋ የሰዉን አገር ወራ ባታዉቅም ጠላቶቿ አልተኙላትም፣ አይተኙምም፡፡ ሆኖም ግን በሕዝቦቿ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትና በአልገዛም ባይነት ወኔያቸዉ ሉዓላዊነቷና የሕዝቦች ነፃነት ተጠብቆ ይቀጥላል፡፡ ዛሬም አገራችን ከቅርብና ከሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቿ በሚሰነዘርባት ሁለንተናዊ ጥቃት ሳትንበረከክ ልጆቿ ከአባቶቻችን በወረሱት የአገር ፍቅር ለሕዝቦች ክብርና ለአገር አንድነት ዘብ ቆመዋል፡፡ መጪዉ ትዉልድም ለጋራ አገሩና ለክብሩ በአንድነት በመቆም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እንደሚያሸጋግራት ጥርጥር የለዉም፡፡

የፋሽስቱ አገዛዝ እንደ ወሳኝ የማሸነፊያ መሳሪያ ተማምኖ የነበረዉ በታሪክ “ፋሺዝም” ተብሎ የሚታወቀዉን ጫፍ የረገጠ ፅንፈኝነትና አክራሪነትን ነበር፡፡ ትዉልዱ ፅንፈኝነትና አክራሪነት ራሱን በልቶ የሚያጠፋ አስተሳሰብ መሆኑን ከፋሺስታዊ አገዛዙ በመማር ከዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ በመላቀቅ አገሩን ማፅናት ይጠበቅበታል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply