“ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ ነው” ጄ.ል ጌታቸው ጉዲና

የአገርና የህዝብ መከታ የሆነ ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ጠንካራ የአገር መከላከያ ሰራዊት እየተገነባ መሆኑን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለጹ።

የአገር መከላከያ ሠራዊት የህዝብ ወገንተኝነቱን አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ለማድረግ አዲስ የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ የሪፎርም ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁላችንም የሆነችውን አገር መከታ ሆኖ የሚጠብቅ ኢትዮጵያን የሚመስል ጠንካራ ሰራዊት እየተገነባ ነው ብለዋል።

ሰራዊቱ ለፓርቲ፣ ለብሔር ወይም ለቡድን የወገነ ሳይሆን የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለአገር ሉዓላዊነትን የቆመ በህገ መንግስቱ የሚመራ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በህወሓት መራሹ ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን የሰራዊቱ አደረጃጀት የኢትዮጵያ መልክና ገጽታ እንዳልነበረው አስታውሰው አሸባሪው ህወሃት ስልጣኑን የሚጠብቁለትን አካላት መሰብሰብ ቀዳሚ ተግባሩ እንደነበር ገልጸዋል።

ይህ ቡድን እስከ 8ዐ በመቶ የሚሆነው የሰራዊቱ አመራርና ስታፍ ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች በማደራጀቱ በህዝባዊ ጫና ስልጣኑን ካጣ ወዲህ አደረጃጀቱን አገር ለማተራመስና ለማፍረስ ሴራው እንደተጠቀመበት ገልጸዋል።

ለዚህም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ክህደት ማረጋገጫ መሆኑን አስታውቀዋል።

ነገር ግን ሰራዊቱ ክህደት ተፈጽሞበት በህልውና ዘመቻና በዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ተጋድሎ ውስጥ ሆኖም ትልልቅ የሪፎርም ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንና ሠራዊቱን ትክክለኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ተምሳሌት ለማድረግ ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሰራዊቱ ከመላ ኢትዮጵያ በተውጣጡ ልጆች መደራጀቱን ተናግረው ይህም የእኔነት ስሜት እየፈጠረና ትክክለኛ ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያውያን ለጋራ ደህንነታቸውና ሉአላዊነታቸው መጠበቅ አምነውና ፈቅደዉ የገነቡት የአገር ሉአላዊነት የመጨረሻው መሸሸጊያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Related posts:

አማራ ክልል "የህግ ማስከበሩ ይቀጥላል"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022
Number of IDPs Hits Record High GloballyMay 22, 2022

Leave a Reply