የወያኔ አጀንዳ አሻሻጭ የመንፈስ ልጆች ወያኔ በአደባባይ በአዋጅ “በአማራ ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ድረስ እወርዳለሁ” ሲል ተከትለው አትዝመቱ ከማለት ጀምሮ በዘመቱ ሰዎች ላይ አቃቂር ሲያወጣ የነበረው የባንዳው ባንዳ “ጦርነቱ እኛን አይመለከትም፤ጦርነቱ የኢትዮጵያን ሕልውና ሳይሆን የአብይን ስልጣን ለማስቀጠል ነው” ማለቱን የምናስታውሰው ጉዳይ ነው። አሁን ደግሞ ወያኔ ከውጭ ባዳ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት ለዳግም ወረራ በተዘጋጀበት ከሰሞኑ እነ ጌታቸው ረዳና ደብረፅዮን አማራን እንደወዳጅና ስለሰላም የተናገሩትን ማዘናጊያን ተከትሎ የመንፈስ ልጆቹ #No More War ወደሚል ዘመቻ ከፍተዋል።

በእውነቱ የሰሞኑን የወያኔን የማዘናጊያ የሰላምና የወዳጅነት ፕሮፖጋንዳ የመንፈስ ልጆቹን የጦርነት አያስፈልግም ጎጅ ነው የባንዳነት የዘመነች ዘዴ አለማድነቅ አይቻልም። ወያኔያዊ ግብራቸውን መሸፈኛ ሊሆን የሚችል ከትናንቱ አንፃር ይህ ለነገ ክርክርም የሚጠቅማቸው ስልት ነው።

ማንም ሰው ማወቅ ያለበት ሰላም በአንድ ወገን ብቻ ፍላጎት የሚመጣ ወይም የሚረጋገጥ ጉዳይ አይደለም። ሰላምና ትዳር እንዲሁም የሚተላለፉ መኪናዎች በአንደኛው ወገን ጥንቃቄ ወይም ጥረት ብቻ አይረጋገጡም ወይም አይሰምሩም። የሁሉንም የነቃ መልካም ተሳትፎና ጥንቃቄን ይጠይቃል።

ሰላምም በስብከት ብቻ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም። አለም ላይ ለሺ ዘመናት ስለጦርነት አስከፊነትና ስለሰላም አስፈላጊነት ያለማቋረጥ ተሰብኳል። ነገር ግን አለማችን በየጊዜው ሚሊዮን ሰዎችን የጨረሰ ቢሊዮን ዶላሮችን ያወደመ ጦርነትን ደጋግማ አካሂዳለች። አሁንም በዩክሬንና በሩሲያ መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነትም ስለሰላም አስፈላጊነት ስለጦርነት አስከፊነት ግንዛቤ የሌላቸው ሆኖ ሳይሆን አንደኛው ወገን ጥቅሜን ማስከበር የምችለው በጦርነት ነው ብሎ ስለሚታመን ነው።

ጦርነት መግባት ሳትፈልግ ጦርነት እንድትገባ ከተገደድክ ምርጫህ ጦርነቱን ቀድሶ አሸናፊ ለመሆን መታገል ነው። ሰላምን ማንም ስለፈለገ በአንደኛው ወገን ብቻ የሚረጋገጠው ነገር አይደለም። ጦርነትን ማሸነፍ የሚቻለው በሰላሙ ቀን ለጦርነት ለመዘጋጀት ሲቻል ነው። የወያኔ የመንፈስ ልጆች እያደረጉት ያለው የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲዘናጋ ብቻ ሳይሆን የጥፋት መንገድ እንዲመርጥ ለዳግም ወረራ ለጦርነት ለተዘጋጀውና ጦርነቱንም ሕዝባዊ ነው እያለ ላለው ወያኔ ደግሞ እንደተለመደው መንገድ መጥረግ ነው።

ማንም ያለውን ቢል የቱንም ያህል የጦርነት ዝግጅት ቢያደርግ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከማስከፈል ያለፈ የትም መድረስ አይችልም።

ያለመስዋዕትነት ደግሞ ድል የለምና ለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝቧ ሰላምና ዘላቂ ጥቅም መከበር መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ለመክፈል ሁሌም የነቃንና የተዘጋጀን ነን!

Via – https://t.me/TJMMA Tomas j

Leave a Reply