ሻዕቢያና ትህነግ – ሰሞኑን ይህ ሆነ

ለወሬው ድምቀት ሁለቱን የቀድሞ ወዳጆች በፍቅር ስማቸው እንጥራቸው። ሰሞኑንን የሆነው እየተለኳኮፈ ቢነገርም በደንብ አልተነገረምና በተንተን አድርጎ ማሳየቱ ለቀታዩ የዕብደት ሩጫ ትምህርት ሊሆን ይችላል። እንዲህ ነው።

በራማና ባድመ በኩል የሻዕቢያን ሃይል ለመውጋት የትህነግ ሃይሎች ከባድ መሳሪያቸውን ደርድረው ገጥመ ነበር። ቢቢሲ “ወዳጆቼ ነገሩኝ” ብሎ ረዥም ጊዜ የቆየ ውጊያ አለመካሄዱንና የትህነግ ሃይል ዱላውን መቋቋም አቅቶት ማፈግፈጉን እንዳስታወቀው ብቻ ሳይሆን ነገሩ ድራማም ነበረበት። የጦርነት ድራማ!!

ኤርትራ ፕሬስ ላይ ለኮፍ ተደርጎ እንደቀረበው ሻዕቢያ ትህነግ በተጠቀሰው ቦታ ትህነግ ውጊያ ለመክፈት የነበረውን ዝግጅት ያውቅ ነበር። ባይጻፍም ሻዕቢያ ውጊያ እንደሚከፈትበት ብቻ ሳይሆን በየት በኩል፣ ምን ያህል ሃይል እንደሚሰለፍ፣ ከነመሳሪያ ዕቅዱን ያውቅ ነበር።

ሰበር መረጃ‼️ የህወሃት አዲስ ወረራ ስትራቴጂ ተደርሶበታል !! የኤርትራ የስለላ ተቋም በህወሃት ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት የህወሃትን ቀጣይ የወራራ ስትራቴጂ ደርሶበታል። ወረራው በቀጣዩ የክረምት ወቅት የሚጀመር ሲሆን ወረራውን የሚያካሂደው በኤርትራ እና በአማራ ክልል በበለሳ እብናት ጎጃም አቅጣጫ መሆኑን ነው። ይህን እቅድ ለመተግበር በአማራ ክልል የሃይማኖት ግጭት መፍጠር እና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ፣ የአገውና የቅማንት ቅጥረኞችን ግጭት እንዲቀሰቅሱ በመስራት ላይ መሆኑን ተደርሶበታል። ህወሃት በኤርትራ ላይ ከባድ ወረራ በማድረግ የሱዳንን ኮሪደር ለማስከፈት ጫና ለመፍጠር ማሰቡ ተደርሶበታል።
Via ኤርትራ ፕሬስ ኤጀንሲ

በዚሁ መሰረት ማክሸፊያ ዕቅድ ተሰርቶ ትህነግ ባሰበው መልኩ ለማጥቃት በደረቱ እየተሳበ ሲገባ “ና ግባ” ተብሎ ተመቻቸለት። ትህነግ የውጊያ ስልቱና አሰላለፉ ውጤታማ እንዳደርገው በማሰብ የድል ብስራት ለማሰማት በዝግጅት ላይ ሆኖ በነደፈው ካርታ መሰረት ወደፊት ገፋ። ከመጠነኛ ጠሽ ጠሽ ምላሽና የቁጩ መከላከል ውጪ የከበደ ነገር አልነበረም።

የትህነግ ሃይሎች በደን ከገቡ በሁዋላ ለአጭር ጊዜ ለወሬና ነጋሪ የማይመች የተናበበ ጥቃት አካባቢውን አናወጠው። በካባድ ሜካናይዝድ ጦር ታጅቦ ያደፈጠው የሻዕቢያ ሃይል ማጥቃት ጀመረ። ከዛ በሁዋላ ቢቢሲ እንዳለው “ጦርነቱ የአጭር ጊዜ ነበር” ሻዕቢያ ስቦ አስገብቶ ወቀጠ!! ይህ ነው ሰሞኑንን የሆነው። በአፋር በኩልም በተመሳሳይ ትህነግ ወደ ፊት ገፍቶ ለመሄድ አስቦ ለአርባ ደቂቃ አረር እንደወርደበት በቅርብ አይተናል። ይኸው ነው።

ወዲ በርሃሌው ነኝ

ዝግጅት ክፍሉ – ራሳቸውን በብዕር ስም የሚጠቅሱት ሰው የጦር መኮንን ናቸው።

Leave a Reply