የትራፊክ አደጋ አራት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችን ህይወት ቀጥፏል።የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የነበሩ አራት ባለሙያዎች በመኪና አደጋ ህይዎታቸው ማለፉን ተቋማቸው ነው ይፋ ያደረገው።

ሰራተኞቹ በአማራ ክልል ደባረቅ ዞን ሳንቃ በር አከባቢ ልዩ ስሙ አበርጊና በሚባል ስፍራ ለመስክ ስራ ሲንቀሳቀሱ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ነው ሕይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ሃዘናቸውን በማህበራዊ ገጻቸው ገልጸዋል ፥ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። አራቱ ባለሙያዎች እንዴትና በምን መነሻ አደጋው እንደደረሰባቸው ዶክተር ሊያ አልጠቆሙም።

Leave a Reply