Site icon ETHIOREVIEW

“ህሊናን የሚፈታተን” የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ – አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

…ንጹሃን ዜጎችን በተናጠል ከመግደል በተጨማሪም የጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሙም በጥናቱ የተረጋገጠ ሲሆን 6 ሺ 985 ንጹሃን ዜጎች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ሳይኖራቸው የተገደሉ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 2 ሺ 808 የተረሸኑና 579 በድብደባ የሞቱ መሆናቸውም ታውቋል። ሌሎች 1 ሺ 797 ንጹሃን ዜጎች ደግሞ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በተለይም በቀወት ሁለትና በአንጾኪያ ገምዛ ስድስት የጅምላ መቃብሮች እንዲሁም በጭና፣ በአጋምሳ፣ በኮምቦልቻና በመርሳ የጅምላ ግድያዎችን ከእነ ጅምላ መቃብራቸው በማየትና በማመሳከር በጥናቱ መረጋገጡ ተገልጿል።

የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶችን ያብራሩት የአጥኝ ቡድኑ አባላት በሕዝቡ ላይ ከደረሰበት ሰብአዊና ስነ ልቡናዊ እንዲሁም ቁሳዊ ጉዳት በተጨማሪ 828 ሺ 862 ሰዎች በቀጥታ በወረራው የተጎዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 409 ሺ 1 መቶ 78 ሴቶች ሲሆኑ 263 ሺ 3 መቶ 28 ደግሞ ህጻናት ናቸው።

የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች አምስት ወር የፈጀ ነው ያሉትን ሪፖርት ይፋ አድርገዋል። የትህነግ ሃይሎች ክልሉን በወረሩበት ወቅት አደረሱ የተባለውን ዝርዝር ሪፖርት ያነበቡ ” ህሊናን የሚፈታተን” በሚል በማህበራዊ ገጾች እያሰራጩት ነው። የትህነግ ታጣቂዎች ከአለቆቻቸው በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ከግብረሰዶም ጀምሮ እያንዳንዱ ፈጽመውታል የተባለው ሁሉ በሪፖርቱ ተካቷል። ከሰባት ሺህ አምስት መቶ ያላነሱ ሰዎች የትህነግ ታጣቂዎች ምን እንዳደረጓቸው አይታወቅም። ወዴት እንዳደረሷቸው ቤሰቦቻቸው አያውቁም። ሙሉ ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል። ትህነግ ለዚህ ሪፖርት ምላሽ ካለው ይስተናገዳል።

የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ሕዝብ ላይ ባካሄደው ወረራ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም የሠራው ጥናት ይፋ ሁኗል። በጥናቱ ከ288 ቢሊየን 16 ሚሊየን 448 ሺ 452 ብር በላይ የሚገመት ሀብት መውደሙና መዘረፉም ታውቋል።

በዛሬው እለት በባህር ዳር ከተማ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጠው ፎረሙ ወራሪው ኃይል በአማራ ክልል 8 ዞኖች ከሰኔ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ባደረገው ወረራ የደረሰውን ሰብአዊ፣ ስነ ልቡናዊ እና ቁሳዊ ጉዳት በጥልቀት የሚያሳየውን ጥናት አቅርቧል።

ጥናቱን ለሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች ያቀረቡት የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሰብሳቢ ዶ/ር ታፈረ መላኩ በተገኙበት የአጥኝ ቡድኑ አባላት ዶ/ር አዳነ ተስፋየ ከባህር ዩኒቨርሲቲ፣ አቶ አማረ ዳኘው ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን የአማራ ክልል ቅርንጫፍ፣ ዶ/ር ደነቀው ቢተው ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና አቶ ሳሙኤል ማለደ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ናቸው።

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው በወረራው ምክንያት በርካታ ዜጎች ለሰብአዊ፣ ስነ ልቡናዊና ቁሳዊ ጉዳት መዳረጋቸውን ሲሆን በተለይም በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ባልነበራቸው ሰላማዊ ዜጎች ላይ የጅምላና የተናጠል ግድያ፣ የአካል ማጉደል፣ ድብደባና በቡድንና በተናጠል የካህናት ሚስቶችንና ወንዶችን ሳይቀር አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጥናቱ አረጋግጧል።

የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ሀብቱን፣ ባህሉን፣ ሃይማኖቱን ሁሉ ለማውደም ጥረት ያደረገ ሲሆን የስነ ልቡና ጥቃት በማድረስ ተሸናፊና ተንበርካኪ ሁኖ እንዲኖር ለማድረግ የታቀደ የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀል እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን ጥናቱ አሳይቷል።

የአጥኝ ቡድኑ አባላት ጥናቱ ወራሪው ቡድን ይዟቸው በነበሩ የአማራ ክልል 8 ዞኖች ውስጥ ከሚገኙ 89 ወረዳዎች 87ቱ እና ከ 979 ቀበሌዎች ውስጥ 945 ቀበሌ አስተዳደሮች ላይ የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

240 ሺ 236 ሰዎች በቀጥታ ሰብአዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የደረሰው የጉዳት አይነትም በጦርነቱ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ ድብደባ፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት፣ አስገድዶ መደፈር፣ የጉልበት ብዝበዛ በተለይም አስገድዶ ምሽግ ማስቆፈር፣ ስንቅና ትጥቅ ተሸክመው መንገድ እንዲመሩ መደረግ፣ ክብረ ነክና ዘር ተኮር ስድቦችና ዛቻዎች፣ እገታና አፈና፣ የጥይት ማብረጃ እንዲሆኑ በማሰብ ነዋሪዎችን የጦር መሳሪያ ሳይዙና ስልጠናው ሳይኖራቸው በጦር ግንባር ፊት ለፊት እንዲሰለፉ ማድረግ

ሁለንተናዊ ጉዳቱን ለመረዳትም ቤት ለቤት በመሄድ፣ የደረሰውን ጉዳት በአካል ተገኝቶ በማየት፣ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በማነጋገር እና የደረሰውን ስነ ልቡናዊ ጥቃት ለመረዳት የቡድንና የተናጠል ጥልቅ ውይይትና ቃለ ምልልሶች በማድረግ ከታህሳስ 7 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ለ 5 ወራት የተከናወነ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶችን ያብራሩት የአጥኝ ቡድኑ አባላት በሕዝቡ ላይ ከደረሰበት ሰብአዊና ስነ ልቡናዊ እንዲሁም ቁሳዊ ጉዳት በተጨማሪ 828 ሺ 862 ሰዎች በቀጥታ በወረራው የተጎዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 409 ሺ 1 መቶ 78 ሴቶች ሲሆኑ 263 ሺ 3 መቶ 28 ደግሞ ህጻናት ናቸው።

በአማራ ሕዝብ ላይ ያጋጠመውን የስነ ልቡና ጫና እና የመንፈስ ስብራት ሳይጨምር የደረሰው ሰብአዊ ጉዳት በጥናቱ ተብራርቷል።

በዚህም መሰረት 240 ሺ 236 ሰዎች በቀጥታ ሰብአዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የደረሰው የጉዳት አይነትም በጦርነቱ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ ድብደባ፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት፣ አስገድዶ መደፈር፣ የጉልበት ብዝበዛ በተለይም አስገድዶ ምሽግ ማስቆፈር፣ ስንቅና ትጥቅ ተሸክመው መንገድ እንዲመሩ መደረግ፣ ክብረ ነክና ዘር ተኮር ስድቦችና ዛቻዎች፣ እገታና አፈና፣ የጥይት ማብረጃ እንዲሆኑ በማሰብ ነዋሪዎችን የጦር መሳሪያ ሳይዙና ስልጠናው ሳይኖራቸው በጦር ግንባር ፊት ለፊት እንዲሰለፉ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

የትግራይ ወራሪ ኃይል ዜጎችን ወደ ማይታወቁ ቦታዎች እያፈነ ይወስድ እንደነበር በጥናቱ የተረጋገጠ ሲሆን 7 ሺ 460 ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።

ንጹሃን ዜጎችን በተናጠል ከመግደል በተጨማሪም የጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሙም በጥናቱ የተረጋገጠ ሲሆን 6 ሺ 985 ንጹሃን ዜጎች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ሳይኖራቸው የተገደሉ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 2 ሺ 808 የተረሸኑና 579 በድብደባ የሞቱ መሆናቸውም ታውቋል።

ሌሎች 1 ሺ 797 ንጹሃን ዜጎች ደግሞ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በተለይም በቀወት ሁለትና በአንጾኪያ ገምዛ ስድስት የጅምላ መቃብሮች እንዲሁም በጭና፣ በአጋምሳ፣ በኮምቦልቻና በመርሳ የጅምላ ግድያዎችን ከእነ ጅምላ መቃብራቸው በማየትና በማመሳከር በጥናቱ መረጋገጡ ተገልጿል።

ከሰብአዊ ጉዳቶች መካከልም አስገድዶ መድፈርን ለጦርነት ዓላማ ማዋል አንዱና ዋነኛው ሲሆን 1 ሺ 782 ሰዎች መደፈራቸው ተዳስሷል። ከእነዚህም ውስጥ 22 ወንዶች ላይ ግብረ ሰዶም ተፈጽሞባቸዋል። ተደፍረው ማርገዛቸውን ካረጋገጡ በኋላ በጸጸት ራሳቸውን ያጠፉ ሴቶችም ያሉ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል።

የስነ ልቡና እና አእምሯዊ ጉዳትን በተመለከተም የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ሕዝብ ላይ በአጭርና በረዥም ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ በባህሪ፣ በስሜትና በአስተሳሰብ የስነ ልቡናና የስነ አእምሮ ጠባሳ ጥሎ እንዳለፈ በጥናቱ ተመላክቷል።

ቁሳዊ ውድመትም አንዱ የጥናቱ ተተኳሪ አርዕስት ሲሆን ወራሪው ቡድን በቤተሰብ ጥሪት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች እንዲሁም የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት ማድረሱ ተነስቷል።

ይህ ውድመትም በጥቅሉ በገንዘብ ሲተመን 288 ቢሊየን 16 ሚሊየን 448 ሺ 452 ብር መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል። ከዚህም መካከል 9 ቢሊየን 144 ሚሊየን 947 ሺ 808 የሚሆነው የመኖሪያ ቤትና የቤት ውስጥ ንብረቶች ውድመት ሲሆን ቀሪው በሌሎች ተቋማትና መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰ ጉዳት ነው።

ሌሎች 1 ሺ 797 ንጹሃን ዜጎች ደግሞ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በተለይም በቀወት ሁለትና በአንጾኪያ ገምዛ ስድስት የጅምላ መቃብሮች እንዲሁም በጭና፣ በአጋምሳ፣ በኮምቦልቻና በመርሳ የጅምላ ግድያዎችን ከእነ ጅምላ መቃብራቸው በማየትና በማመሳከር በጥናቱ መረጋገጡ ተገልጿል።

ከሰብአዊ ጉዳቶች መካከልም አስገድዶ መድፈርን ለጦርነት ዓላማ ማዋል አንዱና ዋነኛው ሲሆን 1 ሺ 782 ሰዎች መደፈራቸው ተዳስሷል። ከእነዚህም ውስጥ 22 ወንዶች ላይ ግብረ ሰዶም ተፈጽሞባቸዋል። ተደፍረው ማርገዛቸውን ካረጋገጡ በኋላ በጸጸት ራሳቸውን ያጠፉ ሴቶችም ያሉ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል።

የጤና ተቋማት ውድመትን በተመለከተም ሰፊውን የገጠሩን ማኅበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ 748 የጤና ተቋማት የወደሙ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን 12 ቢሊየን 340 ሚሊየን 644 ሺ 880 ብር እንደሆነ በጥናቱ ተብራርቷል። ከእነዚህ የጤና ተቋማት ውስጥ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና ኬላዎች፣ የደም ባንኮች፣ የእክስጅን ማምረቻ ፕላንት፣ የማገገሚያ ማእከልና የኅብረተሰብ ጤና ፈጣን ምላሽ መስጫና የምርምር ማእከል፣ የጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤቶች፣ ክሊኒኮችና ፋርማሲዎች እንዲሁም እነዚህ ተቋማት በውስጣቸው ይዘዋቸው የነበሩ ውድ ሀብቶች ይገኙበታል።

በዚህም በጥናቱ እንደተረጋገጠው 800 ሰዎች በመድኀኒት እጦት መሞታቸው ተረጋግጧል።

ሌላው ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የትምህርት ዘርፉ ሲሆን ወራሪው ኃይል 1ሺ 145 የትምህርት ተቋማት ላይ ውድመትና ዘረፋ ያደረሰ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎችን ሳይጨምር 5 ቢሊየን 917 ሚሊየን 953 ሺ 429 ብር ወድሟል። ከዚህ በተጨማሪም ሦስት የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በእነዚህ ተቋማት ብቻ በገንዘብ ሲተመን 19 ቢሊየን 423 ሚሊየን 611 ሺ 67 ብር ጉዳት ደርሷል።

ወራሪው ኃይል የሕዝቡን ባህልና እሴት ለማጥፋት በማለም 54 የክልሉን ሕዝብ ባህል ለማስተዋወቅ የሚሠሩ ተቋማትን አውድሟል። ከጥናቱ ግኝቶች መካከል 190 የሀይማኖት ተቋማትን እንዲሁም በገንዘብ ተመን ሊወጣላቸው የማይችሉ 457 በላይ የከበሩ ጥንታዊ ቅርሶች ላይ ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል። በ868 የቱሪዝም ተቋማት ላይም ውድመት መድረሱ በጥናቱ ተብራርቷል።

በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የደረሰው ጉዳትም መጠነ ሰፊ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ከወደሙት መካከል 49 የግብርና ነክ፣ 22 የጨርቃጨርቅ፣ 65 የእንጨትና ብረታብረት፣ 44 የኬሚካልና የግንባታ ግብአት አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙበት በጥናቱ ተገልጿል።

የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ላይም ጉዳት የደረሰ ሲሆን ወረራው የተፈጸመው ከፍተኛ የግብርና ሥራ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ውድመት እንደደረሰ የጥናቱ ግኝት አረጋግጧል።

የወደመው የሰብል፣ አትክልትና ስራስር፣ ቋሚ ተክልና የቤት እንስሳ፣ የግብርና ሀብቶች እና ሌሎች ግብአቶችም በጥናቱ በሰፊው ተዳሰዋል። ለአብነትም ሁለት የግብርና ምርምር ማእከላት፣ አንድ የአፈር ለምነት ምርምር እና አንድ ቲሹ ካልቸር ቤተ ሙከራዎች፣ 233 የአርሶአደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎች፣ 2 ሺ 9 መቶ 93 ማኅበራት፣ 139 የእንስሳትና የእጽዋት ክሊኒኮች፣ 19 ችግኝ ጣባያዎች፣ ሁለት ዶሮ እርባታ ማእከላት ውድመትና ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል።

ከእነዚህ ተቋማት በተጨማሪም ጥናቱ የመጠጥ ውሀ አገልግሎትና የመስኖ ልማት እንዲሁም በመንግሥትና የሕዝብ መገልገያ ቢሮዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት አካቷል።

ጥናቱ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ ደረቅ ወደቦች እንዲሁም ባቡር ፕሮጀክቱ ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ያላካተተ ሲሆን አሁንም ድረስ በወራሪው ኃይል ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎችን አለማካተቱ የጥናቱ ክፍተት ተደርጎ ተነስቷል።

ጥናቱ ሰፊ ምክረ ሀሳቦችን የያዘ ሲሆን የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት እንዳሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አፋጣኝና ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ስነ ልቡናዊ ስትራቴጂዎችን በመንደፍና በመተግበርና ማኅበረሰቡን ከገጠመው የከፋ ችግር ማላቀቅ እንደሚገባው አስቀምጧል።

የአማራ ሕዝብም እየደረሰበት ካለው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንዲጠበቅ ህጋዊም ሆነ ፖለቲካዊ ከለላ የሚያሻው መሆኑን ያመላከተው የጥናቱ ምክረ ሀሳብ ለወደፊቱም መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከፍተኛ ርብረብ ማድረግ እንደሚገባ ተብራርቷል።

አማራ ማስ ሚዲያ

Exit mobile version