ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደብረብርሃንን ባዶ ማድረግ- የትህነግ የዳግም ወረራ ምኞት! “በትግራይ ኑሮ ርካሽ ነው”

“ዛሬ” ይላሉ አቶ ሰለሞን ” ዛሬ ዞሮብናል። ዕቅዱ ባህር ዳርን፣ ጎንደርንና ደብረብርሃንን መዝረፍና አመድ አድርጎ መመለስ ነው” ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆነው አቶ ሰለሞን የእንዳ ስላሴ ተወላጅ ናቸው። አሜሪካ ልጆቻቸው ጋር ሰንብተው መመለሳቸውን ይናገራሉ። በአሜሪካ ቆይታቸው ከትህነግ ደጋፊዎችና የቅርብ ሰዎች ጋር በተደጋጋሚ ተገናኝተዋል። ተወያይተዋል።

እሳቸው እንደሚሉት በመጀመሪያው ወረራ ከተዘረፉትና ከወደሙት ከተሞች በተጨማሪ አሁን ላይ ዕቅድ የተያዘላቸው ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደብረብርሃን ናቸው። ትህነግ በከፍተኛ ቁጥር ሰራዊት መዘጋጀቱን የሚገልጹ ስብሰባዎች ላይ የሚሳተፉ እንደነገሯቸው ከሆነ የትህነግ የወረራ ዕቅድ የዘገየው ሸኔ በሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ ባለመቻሉ ነው።

በዝርፊያ ከተጋዘው በተጨማሪ ሰፊ መጥን ያለው እርዳታ እንዳለና በትግራይ የሚባለውን ያህል ችግር እንደሌለም አቶ ሰለሞን አመልክተዋል። እሳቸው ሰማሁ ሲሉ ይህንን ቢሉም የክልሉ ሃላፊዎች ግን የመድሃኒትና የምግብ ችግሩ አደገኛ ደረጃ መድረሱን ለቪኦኤ መናገራቸው ይታወሳል።

ለእረፍት ኢትዮጵያ ደርሶ የተመለሰ ዲያስፖራ በሚስቱ ቤተሰቦች አማክይነት የሰማውንና በአዲስ አበባ በሚታወቅ የዓለም ዓቀፍ እርዳታ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የልብ ወዳጁን ጠቅሶ እንዳለው በትግራይ ኑሮ ርካሽ ነው። ከአዲስ አበባ ጋር ሲነጻጸር ሰማይና ምድር ነው።

ከርዳታ ድርጅት ሰራተኛ ወዳጁ እንደሰማው ምክንያቱ ክልሉን የሚመራው ድርጅት እርዳታውን በተመጣጣኝ ዋጋ መልኩን እየቀየረ ለገበያ ያቀርባል። በብዛት ዳቦ ያመርታል። ለምግብ አቅርቦት ምንም ዓይነት በጀት ስለማያወጣ፣ ቀረጥ ተጨማሪ ወጪ ሳያስፈልገው በዕርዳታ የሚያገነውን ለገበያ ስለሚያቀርብ ገበያው ርካሽ ሊሆን እንደቻለ አመልክቷል። መድሃኒት ከፋርማሲዎች በርካሽ እንደሚገኝም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ ገፍተው ቢሰሩበት በርካታ መረጃዎች ማግነት እንደሚችሉ ያመለከትወ ዲያስፖራ የመቀለ ልጅ የሆነችው ጓደኛው በርካታ ጉዳዮች እንዳቻወተችው፣ ይሁንና ለጊዜው ለሚዲያ ሊያውለው እንደማይፈልግ አመልክቷል።

አቶ ሰሞን ባህር ዳር፣ ጎንደርንና ባህር ደብረብርሃን ባዶ ለማድረግ ያቀደው ትህነግ ወኪሎች እንዳሉት እንደሚያውቁ አመልክተዋል። በስም የሚያውቋቸው እንዳሉ ጠቅሰው በጥቅሉ ” ወያኔ አማራ ክልል ውስጥ የተከለው እግሩ አልተነቀለም” ሲሉ ወንድማዊ ማሳሰቢያቸውን አስተላልፈዋል። የአማራ ክልልም “የባንዳ ባንዳ” ሲል የሚጠራቸውና የመከላከያና የክልሉን ልዩ ሃይል ለማስኮብለል ብር የሚረጩትን መታገስ እንደማይችል አስታውቆ ወደ ዘመቻ መግባቱን አቶ ሰለሞን ” የዘገየ” ሲሉ ደግፈውታል። ጫጫታውም ” የሞት ጣር ድምጽ ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያን እንደሚወዱ፣ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ህይወት ያለ እንደማይመስላቸው የሚናገሩት አቶ ሰለሞን በቅርቡ በርካታ ጉዳዮችን ይፋ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።

መከላከያ ማናቸውንም ጥቃት በአጭር ጊዜና በፈጣን ኦፕሬሽን ማጠናቀቅ የሚያስችል ቁመና ላይ እንዳለ፣ የታጠቀው ዘመናዊ መሳሪያና አሁን ላይ ያለው አቋም ከትንኮሳ በፊት ደጋግምው እንዲያስቡ የሚያስገድድ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። በተመሳሳይ ትህነግ ሰፊ ሃይል መመልመሉና በወልቃይት በኩል ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀቱን መሪዎቹ እያመለከቱ ነው።

አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ዳግም ጦርነት እንደማይጀመር፣ ትህነግ ላለመረሳት ሲል ዜናውን እንደሚያስጮኸው እየተናገሩ ነው። በቀድሞው መጠን የሚዲያም ሆነ የአገራት ድጋፍ እንደሌለው የሚነገርለት ትህነግ “ከበባ ምስበር” በሚል ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ቢመለምልም በወልቃይት በኩል በቀላሉ እንደማይሳካለት በቂ ግንዛቤ ስላለው መጀመሪያ አማራ ክልልን በውክልና ማተራመስን ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንን እነዚህ ወገኖች ያምናሉ።

Leave a Reply