የኡጋንዳ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ካሂንዳ ኦታፍሬ በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢ ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ ያሰሙት ንግግር የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡

ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ ባሰሙት ንግግራቸው ላይ “ድሆች ገነት አይገቡም” ማለታቸውን ኡጋንዳ ኒው ቪዥን የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ድሆች ገነት የማይገቡት ሁሌም ፈጣሪን በድህነታቸው ስለሚያማርሩ ነው የሚሉት ሚኒስትሩባለጸጋ መሆን ክብር ነው ሲሉም መናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ተማሪዎች ከድህነት ለመውጣት ጠንክሮ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል እንደ ሚዲያው ዘገባ፡፡

ፈጣሪ የሰጣችሁን መንገድ ሳትጠቀሙ ቀርታችሁ ባለጸጋ ባትሆኑ በድህነታችሁ ፈጣሪያችሁን አታማሩ ያሉት ሚኒስትሩ ተማሪዎች በርትተው እንዲሰሩ አበረታተዋል ተብሏል፡፡

በኡጋንዳ 75 በመቶ ዜጎቿ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች ሲሆን የስራ አጦች ቁጥርም ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አክሏል፡፡(AL ain)

Leave a Reply