ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበ

የወሎ ፋኖ ዛሬ እምድብ ስፍራው ደርሶ ከመከላከያ በተሰጠው የግዳጅ ቀጠና ስራውን ሊያከናውን ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው ክልሉ ከፌደራል ጋር በመሆን ፋኖን እያሳደደና እያጠፋ እንደሆነ በስፋት በተቃውሞ በሚቀርብበት ወቅት ነው።

“በእነ ጀኔራል ሀሰን ከረሙ ፤ ሞገስ ከበደ ፤ ሻለቃ ደምሌ አራጋው ፣ ምስጋን ደስየ ፣ ሙሃመድ ጎብየ ፤ የወርቄው ትንታግ በላይ እያሱ ፣ ሰይድ አፋሩ እና ሰለሞን ሰማው ፣ የሚመራው የወሎ ፋኖ ምርቃቱን ጨርሶ በትላንትናው እለት መከላከያ ሰራዊቱ በሰጠው የግዳጅ ቀጠና ወደ ወሎ ግንባር በዚህ ገብቷል።” ሲሉ በምስልና በድምጽ አስደግፈው መረጃውን ያሰራጩት ወገኖች የሚታወቁ የአማራ ክልል ኢትዮጵያዊ አክቲቪስቶች ናቸው።

ጀኔራል ሀሰንና ሙሉ አመራራቸው ከመከላከያ ከሰራዊቱ፣ ልዩ ሃይልና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር ተናበው እየሰሩ እንደሆነ በስልክ እንዳረጋገጡ ተጠቅሶ ይፋ የሆነው ቪዲዮ በድምጽ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መረጃ ሆናኡል።

ትህነግ ለዳግም ወረራ ዝግጅት እያደረገና ጦርነት እንደሚከፍት በይፋ ባስታወቀበት በአሁኑ ወቅት በመላው አማራ ክልል “መሬት አንቀጥቅጥ” የተባለ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲካሄድ ጥሪ ተላልፎ ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል። ዛሬ ፋኖ በኢትዮጵያ ባንዲራ ተሞሽሮ ” አገሬን” የሚል መፈክር በታተመባቸው አይሱዙ የጭነት መኪኖች ወደ ወሎ ግንባር ሲያመራ የታየው ሃይል በክፍተኛ ሞራል ላይ ሆኖ መገኘቱ በርካቶችን አነጋግሯል። ሰላማዊ ስልፉን ሲጠሩና ሲያስተጋቡ የነበሩት ወገኖች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

ቀድሞ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት “የተከበሩ” አቶ ክስርስቲያን ታደለም ሆኑ ሌሎች የወሎን ፋኖ አስመልክቶ እስካሁን በይፋ በአሉታዊ ጎኑ አስተያየት ሲሰጡ አልተሰማም። የክልሉ መሪ ሰሞኑንን በሰጡት መግለጫ ” ፋኖ የአማራ የክብር ስም የቁርጥ ልጅ ነው ማንም ቀና ብሎ አያየውም። በፋኖ ስም የሚነቀሳቀሱና በሌብነት የተሰማሩትና ወንጀለኞችን ነው ወደ ህግ የምናቀርበው” ማለታቸው ይታወሳል።

Leave a Reply