በአንድ ኩንታል ገብስ የተሰራው ግዙፍ ገንፎ በበቆጂ ለዕይታ ቀረበ


በአንድ ኩንታል ገብስ የተሰራው ግዙፍ ገንፎ በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ በአርሶ አደሮች ፌስቲቫል ላይ ለዕይታ ቀርቦ መነጋገሪያ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ትልቁና በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ገንፎ በ100 ኪሎ የገብስ ዱቄት፣ በ10 ኪሎ ቅቤ፣ በ1 ኪሎ በርበሬ፣ በ1 ኪሎ ጨው እና በ100 ሊትር ውሃ እንደተሰራ ነው የተነገረለት።

ገንፎውን ለማብሰል 3 ኩንታል ኩበትእና 3 እስር እንጨት እንደፈጀም ተገልጿል።

በዛጎል በተንቆጠቆጠ ቆሬ በ20 ወጣቶች ጉልበት በመኪና ተጭኖ በበቆጂ አትሌቶች ማሰልጠኛ ሜዳ ለዕይታ መቅረቡን ከጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ የማህበራዊ ሚዲያ
ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፌስቲቫሉ ታዳሚዎች በ100 ኪሎ የገብስ ዱቄት የተሰራውን ገንፎ መቋደሳቸውም ተነግሯል።

ሁለተኛው የአርሲ አርሶ አደሮች ፌስቲቫል በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ተካሂዷል።

አርሶ አደሩ ለመኸር እርሻ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት ፌስቲቫሉ መካሄዱ የበለጠ መነቃቃትን እንደሚፈጥር የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሙሳ ፉሮ ገልጸዋል።

EBC

See also  አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ በማንኛው መልኩ ዝግጁ መሆናችውን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ

Leave a Reply