“የጥፋት ሃይሎችና” ገንዘብ ተያዘ ፤ በቀናት ውስጥ ከ200 በላይ ሰርጎ ገቦች ተይዘዋል

“በሰቆጣ ከተማ ለአሸባሪው ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ” ሲል የአስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ሃያ ሰርጎ ገብ የተባሉ አብረው መያዛቸውም ታውቋል። ሕዝብ ነቅቶ እየተቆመ ነው።

“ከአሸባሪው ሕወሀት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል” ሲል አስተዳደሩ መናገሩን ያመለተው ኢዜአ ነው።

የአስተዳደር የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሸጌ መንግስቴ ከግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተደረገ የተቀናጀ ጥረትም ነው ለትህነግ የሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር የተታዘው። ገንዘቡን ለሽብር ቡድኑ ሊያደርሱ የነበሩ 20 ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኀይሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አመልክተዋል።

በሌላ በኩል “ከአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በከተማ አስተዳደሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተመልክቷል። ፖሊስ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ኀላፊ አመልክተዋል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ግብረ ኀይል ከግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሰውና ተሽከርካሪ የሰዓት እላፊ እገዳን ጨምሮ የተለያዩ ገደቦችን መጣሉ ይታወቃል።

ከትናንት በስቲያ በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አሥተዳደር ለአሸባሪው ሕወሀት ሊተላለፍ የነበረ ሶስት ሚሊዮን ብር በጋሪ በረት ውስጥ ተበይዶና ተሸሽጎ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በሕዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ መግለጹ የሚታወስ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተመሳሳይ ዜና በአማራ ክልል የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ከሁለት መቶ በላይ ሰርጎ ገብ የተባሉ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን አመልክቷል።

Advertisements

Leave a Reply