የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በአለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (INTRPOL) አስተባባሪነት በምስራቅ አፍሪካ በባህር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።

በምስራቅ አፍሪካ በባህር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ የሬድ ሲ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት (Red Sea Initiative) ኃላፊዎች ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ለቀጠናው ብሎም ለአለም ስጋት የሆኑ የወንጀል አይነቶችን ለመግታትና በትብብር ለመስራት ፕሮጀክቱ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያና የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን ለመግታት ትላልቅ ስራዎችን እንደሰራችም በማንሳት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ እንደምታንቀሳቅስና በ2015 ዓ.ም የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረትን (EAPCCO) በሊቀ-መንበርነት በመረከብ የቀጠናው ሀገሮችን በማሳተፍ ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል ሚናዋን እንደምትወጣ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት፣ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከል ሰፊ ተሞክሮ ያላት በመሆኗ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ያላትን ትልቅ ልምድ ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ ታካፍላለች ሲሉ ለፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

Ethiopia and France agreed on their first military cooperation accord on Tuesday, a deal that includes helping the landlocked nation build a navy, as Paris seeks to boost economic ties in Africa’s second-most populous country.

ሕገ ወጥ የሰዎችና የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን እንዲሁም የተሰረቁና የጠፉ ሰነዶችን የመከላከል ዓላማ አድርጎ ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት በአለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (INTRPOL) አስተባባሪነት በአለም አቀፍ Martime ድርጅት (IMO)፣ በአውሮፓ ህብረት (EU) እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት መድሀኒትና ወንጀል ቁጥጥር (UNODC) በጋራ ይሰራል። በአፍሪካ ኢትየጵያን፣ ጂቡቲን፣ ሶማሊያን፣ ሱዳንን፣ የመንንና እና ኤርትራን በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡

የአቅም ግንባት፣ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም ኦፕሬሽን ለማከናወን የኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ጣቢያ ፣የሶማሊያ ቦሳሳ ወደብ፣የሱዳን ፖርት ሱዳን፣የየመን ኤደን ፖርት እንዲሁም የጅቡቲ ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ፖርት የተመረጡ መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል ፡፡

በፕሮጀክቱ ፕሮግራም መሰረት ስልጠናው በሚቀጥሉት ቀናት በኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ጣቢያ ላይ እንደሚጀመር ኃላፊዎች መገለጹን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያሳያል ሲል የዘገበው ኢፒድ ነው።

Leave a Reply