መንግስት በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ከማያምኑ ጋር እንደማይሰራ ይፋ አደረገ

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊገባው እንዳይገባው” አሉ ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣ ደግመው “ ህብረተሰባችን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም።አሁን ባለንበት ሁኔታ የመንግስት አጠቃላይ የጸጥታ መዋቅር በውስጡ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም አካል የሚሰነዘር ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ የመቀልበስ የተሟላ ቁመና እና ብቃት አለው”

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ይህንን ያሉት በመላው አገሪቱ ” ሕዝብ በቀጥታና በተደጋጋሚ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ተጀመረ” ስለተባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለፋና በሰጡት ማብራሪያ ነው።

“መንግስት ኢትዮጵያን ከሚያፈርሱ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ከማይቀበሉ፣ ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጎላ ከሚሰሩ ኃይሎች እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ከማይሰብኩ ኃይሎች ጋር አብሮና ተባብሮ አይሰራም” ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚናፈሱ የድርድር አሉባልታዎች ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ንግግራቸው ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ብሎ ራሱን ለግማሽ ክፈለዘመን የሚጠራው ቡድን በኢትዮጵያ አንድነት፣ኢትዮጵያን በብሄርና በሃይማኖት ለመበታጠስ የሚሰራ አሸባሪ ቡድን ተብሎ በመሰየሙ መንግስት እንደማይደራደረው ይፋ አድርገዋል

“መንግስታችን የሰላም፣ የዲሞክራሲና የልማት መንግስት ነው” ያሉት ዶክተር ለገሰ፣ ምንም እንኳን መንግስታቸው የሰላም መንግስት ቢሆንም ሕግና ስርዓትን የማስከበር አቅሙ የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱንና ቁርጠኛነቱም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የቁርጠኛነቱን መገለጫ ሲያመላክቱ “መንግስት ኢትዮጵያን ከሚያፈርሱ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ከማይቀበሉ፣ ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጎላ ከሚሰሩ ኃይሎች እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ከማይሰብኩ ኃይሎች ጋር አብሮና ተባብሮ አይሰራም” ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚናፈሱ የድርድር አሉባልታዎች ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ንግግራቸው ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ብሎ ራሱን ለግማሽ ክፈለዘመን የሚጠራው ቡድን በኢትዮጵያ አንድነት፣ኢትዮጵያን በብሄርና በሃይማኖት ለመበታጠስ የሚሰራ አሸባሪ ቡድን ተብሎ በመሰየሙ መንግስት እንደማይደራደረው ይፋ አድርገዋል። ይህ የመንግስት መርህ መሆኑም ተመልክቷል።

“ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ወንድማማችነት፣የሕዝቦች ብልጽግና እና ክብር ፣ የሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት በፍጹም ለድርድር የሚቀርቡ አይደሉም” ሲሉ ዶክተር ለገሰ የመንግስታቸውን ቀይ መስመር፣ የሕዝብን ፍላጎት አንተርሰው በግልጽ አስቀምጠዋል። ” ኢትዮጵያን ሊበትን ነው፣ የኦሮሙማ መንግስት ነው …” የሚል ትችት የሚሰነዘርበት መንግስት ” በኢትዮጵያ አንድነት ከማያምኑ አካላት ጋር አልነጋገርም፤ አብሬ አልሰራም” ሲል በገሃድ ማስታወቁ በአብዛኞች ዘንዳ መነጋገሪያ ሆኗል። ሚኒስትሩ ይህን ብለው ሲያበቁ “በዚህም ህብረተሰባችን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም” በማለት ነው።

ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ መንግስት አስተማማኝ ቁመና እና ብቃት ላይ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀስ አካል ላይ እርምጃ ለመውሰድ መንግስት የተሟላ ቁመና እና ብቃት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

መንግስት በትላልቅ ከተሞች ከህብረተሰቡ ጋር በርካታ ውይይቶች ማድረጉን አውስተው÷ በውይይቶቹም በየአካባቢው የሚፈጸም የተደራጀ ዝርፊያ፣ ግድያ ፣ መፈናቀል እና ስጋት ህብረተሰቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው ሕዝቡ አንስቷል ብለዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች መንግስት በአፋጣኝ መቅረፍ እንዳለበት ህብረተሰቡ በአንድ ድምጽ ሊባል በሚችል መልኩ አጽንኦት ሰጥቶ መግለጹንም ነው ዶክተር ለገሰ የተናገሩት ፡፡

ሕግ የማስከበር ሥራው ከህብረተሰቡ የቀረበ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ለገሰ÷ ሥራውም ከፌደራል እስከ ክልል የተቀናጀ ሆኖ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሕግ የማስከበር እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡

በዋነኛነት በኦሮሚያ ክልል አሸበሪው ሸኔን ማዕከል በማድረግ ከዚሁ ቡድን ጋር ትስስር ያለው የአልሸባብ የሽብር ቡድን እንደዚሁም ቀደም ብሎ ሽብርተኛው ህወሓት የፈጠራቸው ትስስሮች እና ኦሮሚያ በሚጎራበትባቸው የደቡብ፣ የሲዳማ እና የሶማሊያ አካባቢዎች ላይ ሕግ የማስከበር እርምጃው እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ÷ በአዲስ አበባ ከተማ በጣም በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀ፣ ለውንብድና የተሰለፈ እና ለዝርፊያ የተዘጋጀብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ሥራ ውስጥ የገባ ኃይል መኖሩን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

በአማራ ክልልም በተለያዩ አካባቢዎች በክልሉ ተከስቶ በነበረው እና የሽብር ቡድኑ ህወሓት በፈጠረው ጦርነት በተለያየ ምክንያት በነፍስ ግድያ ከእስር ቤት ያመለጡ፣ የመንግስትና የግለሰብን ሀብት ዘርፈው ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠባቸው እንዲሁም በተለያየ የሽፍትነት ሥራ ላይ የተሰማሩ፥ ነገር ግን እራሳቸውን ፋኖ በሚል ስም በማደራጀት ከመንግስት የጸጥታ አካል ትይዩ የተደራጁ እና ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት የሆኑ ኃይሎችን በመለየትና በእነዚህ ቡድኖች ላይ የሕግ ማስከበር ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዋነኛነት ቁልፍ አካባቢዎች ተብለው የተለዩ ቦታዎች ላይ በተወሰደ ሕጋዊ እርምጃ አካባቢዎቹ ነፃ መውጣታቸውንና ህዝቡም መደጋጋት መቻሉን ነው ዶክተር ለገሰ ቱሉ ከፋና ጋር በነበራቸው ቆይታ የጠቆሙት።

በዚህም ህብረተሰቡ በተጋጋ ሁኔታ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሶ ምርት ወደማምረት ተግባሩ እንዲገባ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆናቸውን ጠቁመው÷ የምርት ግብዓቶች እንዲቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሕግና ስርዓትን በማስከበር ህብረተሰቡን ወደ ምርት ተግባር የመመለስና የህብረተሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች መፍታት የመጀመሪያውና ትልቁ የመንግስት ሥራ እንደሆነ የፋና ዘገባ ያስረዳል።

Leave a Reply