የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ የሚሸምተውን ነዳጅ በከፊል አገደ

የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ከሩሲያ ከሚሸምቱት ነዳጅ ሁለት ሶስተኛውን ለማገድ ከስምምነት ደርሰዋል። ውሳኔው ከሩሲያ በባሕር የሚጓጓዘውን ነዳጅ ብቻ የተመለከተ ነው። የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ሚሼል እና የጀርመን መራሔ-መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ሩሲያ ለውጊያ ከዘመተችበት ዩክሬን እንድትወጣ ጫና ያሳድራል ብለው ተስፋ አድርገዋል።

የአውሮፓ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ትናትና ዛሬ ለሁለት ቀናት እዚህ ብራስልስ ተካሂዶ፤ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ስብሰባው የተጠራውና ያተኮረው በዩክሬን ላይ ለመወያየት ሲሆን፤ በዚህም  ኮሚሽኑ በሩሲያ ላይ ያቀረበው ስድስተኛው ማዕቀብ፣ የሀይል አቅርቦት፣ የመከላከያና በጦርነቱ ምክኒያት ሊከሰት በሚችለው የምግብ ዕህል ዕጥረት ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። 
ከሶስት ወር በፊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት መክፈቷን ተክትሎ፤ የአውሮፓ ህብረት ሩሲያን አውግዞና ዩክሬንን ደግፎ መቆሙ የሚታወስ ሲሆን፣ እስካሁንም ህብረቱ ለዩክሬን በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ኢሮና የመሳሪያ እርዳታ እንዳደረገና እያደረገም እንደሆነ ነው የሚታውቀው። ያአውሮፓ ኮሚሺን ለመጀመሪያ ግዜ ለጦር መሳሪያ መግዣ እንዲሆን አንድ ቢሊዮን ኢሮ እርዳታ መለገሱ ተገልጿል፤ አባል አገሮች ጀርመንን ጨምሮ፤ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችን ለዩክሬን ልከዋል ወይም በመላክ ላይ ናቸው። ። በዚህ በኩል 27ቱ የህብረቱ አገሮች አንድነት ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል።  

ሩሲያን ከማውገዝ አልፎም ልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎችን በመውሰድም የህብረቱ አገሮች ከዩክሬን ጋር ክወታደራዊ ተሳትፎ በመለስ ያላቸውን ተሳትፎና አጋርነት አሳይተዋል። በሩሲያ ላይ የተላለፉት  አምስት ማቀቦች ባንኮችንን፤ ኩባንያዎችን፤ መገናኛ ብዙሀንን፤ የፓርላማ አባላትንና ፕሬዝዳንት ፑቲንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችንና የጦር መሪዎችን የሚያካትቱ ናቸው፡ የማዕቀብ እርምጃዎቹ አላማ ሩሲያን በኢኮኖሚ በማዳከምና ከአውሮፓና ዓለማቀፉ ህብረተሰብ በማግለል እንድትቀጣና ከዩክሬንም ተገዳ እንድትወጣ ለማድረግ እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሯል።; 

ዩክሬን ሩሲያ ጥቃት የሰነዘርችባት አፍቃሪ የአውሮፓ ህብረት በመሆኗና ወደ ኔቶና የአውሮፓ ህብረትም ለመቀላቀል ያላትን ፍላጎት በመቃወም እንደሆነ ስትገልጽ ቆይታለች። ሩሲያ ደግሞ ዩክሬን ብዙዎቹ የአውሮፓ ህብረት አገሮች አባል ለሆኑበት ለስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪድን ድርጅት ኔቶ በማደርና መሳሪያም በመሆን ለደህንነቴ ስጋት ፈጥራብኛለች በማለት ነው የምትሟገተው። ባንዳቸው ወይም በሁለቱም ምክኒይቶች ይሁን፤ ጦርነቱ ግን በአውሮፓ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የሰው ልጆች እልቂትና ውድመት አድርሷል፤ እያደረሰም ነው።  
የአውሮፓ ህብረት የዚህ አስከፊ ጦርነት ሰለባም እየሆነ ነው።  እሳክሁን አምስት ሚሊዮን የዩክሬን  ስደተኖችን ተቀብሏል። ለዩክሬን የሚሰጠው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ የህብረቱን ኢኮኖሚ እንደጎዳውና የዕድገት እቅዱንም እንዳዛነፈው እይተገለጸ ነው፡፤ በሩሲያ ላይ የሚጣለው ማዕቀብም በአባል አገሮች ኢኮኖሚና ንግድ ላይ የራሱ የሆነ ተጽኖ እንደሚያሳድር የታወቀ ነው።

በተጨማሪም አባል አገሮች ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ  የመከላከያ ወጪያቸውን እያሳደጉና  ጦራቸውንም በተሻለ ሁኒታ እየገነቡ መሆናቸው አዲስ ክስተት ነው ። ይህ ሁሉ የፖሊስና የትኩረት አቅጣጫ ለውጥ፤ በኮቪድ ወረርሺን ክፉኛ ተጎድቶ የነበረው ኢኮኖሚ ገና ሳያገግም የመጣ በመሆኑ፤ አባል አገሮችን ለከፋ ችግር አጋልጧቸዋል እየተባለ ነው። ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በመቃወም መንግስቶቻቸው ለዩክሬን የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ሲጠይቁ የነበሩ የህብረቱ ዜጎች፤  ዛሬ ይበልጥ ወደ ውስጥ በማየት መንግስቶቻቸው ባሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ችግሮች እንዲያተኩሩ እየጠየቁ  ሲሆን፤ ይህም መነግስታቱ በሚወስዱቸው እርምጃዎች ላይ ተጽኖ ይኖረዋል ። ካንድ ወር በፊት ኮሚሽኑ በሩሲያ ላይ ለስድስተኛ ግዜ እንዲተላለፍ የቀረበው የማዕቀብ እርምጃ ሲያወዛግብ የቆየውና የህብረቱንም አንድነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባውም በዚሁ ጦርነቱ ከዩክሬን አልፎ በህብረቱ አገሮች ላይ በፈጠረውና እየፈጠረ ባለው የኢኮኖሚ ጫናና የኑሮ ውድነት ምክኒያት ነው። ስድስተኛው ማዕቀብ ከሁሉም ባላይ የሩሲያን ነዳጅና ጋዝ መግዛት ማቆምን የሚጠይቅ ሲሆን፤ ይህ ግን እንደሀንጋሪ ላሉ ብዙውን የነዳጅ ፍጆታቸውን በሩሲያ ላይ ላደረጉት አገሮች ቀላል አልሆነም። በመሆኑም በተለይ 65 ከመቶ የሚሆነውን ነዳጅና ጋዝ ከሩሲያ የምታገኘው  ሀንጋሪ  ማዕቀቡ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጥ የሚይደርግ ነው በማለት አግዳው ቆይታለች።

ትናትናና ዛሬ የተካሂደው ልዩ ስብሰባ የተጠራውና ያተኮረውም  በዚሁ ስድስተኛው ማዕቀብ ውሳኔና ትግበራ ላይ እንድነበር ታውቋል። ለአንድ ወር ያህል ሲያከራክር የቆየው ማዕቀብም አገሮች ያቀረቡትን ሀሳብ ከግምት  ባስገባ አሰራርና ቀመር ተስተካክሎ መወሰኑ ተገልጿል። የካውንስሉ ፕሬዝድንትና የስብሰባው መሪ ሚስተር ቻርለስ ሚሸል በሰጡት መግለጫም መሪዎቹ በዩክሬን ላይ በተያዙ ሁለት አጀንዳዎች በተሳክ ሁኒታ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውን ነው የተናገሩት። “ ዋናውና የመጀመሪያው አጀንዳ ፤ ለዩክሬን መደረግ ስላለበት ድጋፍ ነው። የገባነውን ቃል ተግብርዊ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎን ለመውሰድ ተስማምተናል። ዩክሬን የገንዘብ ድጋ የሚይስፈልጋት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ለዚህም የ9  ቢሊዮን ኢሮ  ድጋፍ በጉባኤው ጸድቁል” ብለዋል። በሩሲያ ላይ የሚወሰደውን እርምጃ  በሚመለክትም ሚስተር ሚሼል፤ ` ወደ  አውሮፓ የሚገባውን የሩሲይ ነዳጅ ለማቆም ከስምምነት ተደርሷል ነው ኡአኡት። ውሳኔው የሩሲያን ሁለት ሶስተኛ ነዳጅ የሚመለከትና ሩሲያንም ለጦርነት የምታውለውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያሳጣት ነው ብለዋል። 

ቀደም ሲል የዩክሬኑ መሪ ቮሌድሜየር ዘለንስኪ በቪዲዮ ለጉቤው ባደረጉት ንግግር፤  ሩሲያ እየወጋችን ያለችው እናንተ በነዳጅ ግዥ በቀን በምትከፍሏት አንድ ቢሊዮን ኢሮ ነው በማለት የህብረቱ አገሮች የርስ በርስ ፍትጊያቸውን አቁመው  የሩሲያን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ወደ ደህብረቱ እንዳይገባ እንዲያደርጉ አሳስበው ነበር፡፤ ይሁን እንጂ ይህ የዩክሬኑ መሪ ጥያቄ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግንቷል ማለት አይቻልም፡፤ ቀደም ሲል በተለይ እንደሀንጋሪ የመሳሰሉ የባህር በር የሌላቸው አገሮች ከሩሲያ የሚገዙትና በባንቧ የሚደርሳቸው ንዳጅና ጋዝ በምንም አይነት እንዳይቆም ወይም ደግሞ ሊላ የሀይል አማራጭ  ህብረቱ እንዲያቀርብላቸው ያቀረቡት ጥያቄ፤ ለግዜው መልስ ያገኘ  ነው የሚመስለው። ያሁኑ ማዕቀብ በባህር ሊገባ የሚችለውን እንጂ ወደ ሀንጋሪ የሚመጣውንና ከዚያም ወደ ስሎቫኪያ የሚደርሰውን አይመለከትም።  

የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ኦርባን በነዳጅ ላይ ሊጣል በታሰበው ማዕቀብ ላይ ይህን ሁሉ ውዝግብ የፈጠረው ኮሚሽኑ እንደሆነ በመጥቀስ ሲናገሩ ተሰምተዋል። “በአስቸጋሪ ሁኒታ ላይ ነው ያለነው፡፤ ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክኒያት ኮሚሽኑ የሚወስደው እርምጃ ሀላፊነት ያለበት እለመሆኑ ነው። ባለፈው ስብሰባ  አባል አገሮች ያልተስማሙበት የነዳጅና ጋዝ የውሳኔ ሀስብ መቅረብ እንደሌለብት ተስማምተን የነበር ቢሆንም ኮሚሽኑ ግን ማንንም ሳይማክር ይህን ሀሳብ አቀረበ በማለት ኮሚሽኑን ተችተዋል  ።  
በጥያቄያቸው መሰረትም ወደ ሀንጋሪ የሚመጣው ደቡባዊ የነዳጅ ማስተላለፊይ መስመር እንዲቀጥልና በባህር የሚመጣው ነዳጅና ጋዝ ብቻ እንዲቆም ከስምምነት ተደርሷል። የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቮንዴር ለየን ይህን ሲይብራሩ፤ “የስሜናዊው የነድጅ መስመር  ለጀርመንንና ፖላንድ ነዳጅ  የሚያቀርብ ሲሆን፤ የድቡቡ መሰመር ደግሞ ለሀንጋሪና ለሎራቫኪያ የሚያቀርብ ነው፡፤ በስሜኑ መስመር ነዳጅ የሚያገኙት ጀርመናን ፖላንድም እስክ እዚህ አመት መጨረሻ እንጂ እንደሚያቆሙ የገለጹ በመሆኑ በአመቱ መጨርሻ 90 ከመቶ የሚሆነው ከሩሲያ የሚመጣው ነዳጅ ይቆማል” ብለዋል። ወደ ሀንጋሪና ስሎቫኪያ ስለሚገብው ነዳጃም ወደፊት ውይይት እንደሚደረግ ወይዘሮ ቮንዴር ሌየን ቢጠቅሱም  እስከ መቼ ድረስ  ሀንጋሪና ስሎቫኪያ ከማዕቀቡ ነጻ ሆነው እንደሚቆዩ ግን አልገለጹም።  የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ሚሼል እና የጀርመን መራሔ-መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ሩሲያ ለውጊያ ከዘመተችበት ዩክሬን እንድትወጣ ጫና ያሳድራል ብለው ተስፋ አድርገዋል።

ልዩ ጉባኤው በሌሎችም የዩክሬን ጉድዮች ውሳኔዎችን አሳልፏል። ከሁሉም በላይ የዩክሬን መንግስት ለሰራተኖቹና ጡረተኖች ደመወዝ ለመክፈልና መስረታዊ አገለግሎቶችን ለመስጠት እንዲችል  የሰባቱ ባለጸጋ አገሮች ከሚስጡት ድጋፍ በተጫማሪ በአውሮፓ ህብረት በኩልም የ9 ቢሊዮን ኢሮ የገንዘብ እርዳታ ለመስጠት ከስምምነት ተድርሷል ተብሏል። እንዲሁም የሚሰጡትን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክሮ  ለመቀጠልና፤ ዩክሬን የዕህል ምርቷን ወደ ውጭ እንድትልክ ሁኒታዎችን ለማመቻቸት ጥረት ይደረጋልም ተብሏል። በተጨማሪም ለዩክሬን  መልሶ ግንባታ ጉዳይ ውይይት እንደተደረገና ኮሚሹ ሌሎች ባለድርሻ አክላትን የሚያሳታፍ አለማቀፍ መድረክ የሚፈጥር መሆኑን ከጉባኤው የወጣው መግለጫ ያሳያል። 

ይሁንና የውሮፓ ህብረትም ሆነ የመዕራቡ አገሮች በአጠቃላይ፤ ለዩክሬን በሚስጡት እርዳታም ሆነ በሩሲያ ላይ በሚያስተአላልፏቸው የማዕቀብ ውሳኔዎች፤  ጦርነቱን ማስቆም አለመቻላቸው እያነጋገረ ነው። በመስረቱ በሩሲያ ላይ የሚወሰዱት እርምጃዎች ሩሲያን በማዳከም ጦርነቱን መሸክም እንዳትችል ማድረግና፤ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ለማስገደድ ነው ቢባልም፤ ይህ ግን ሊሆን እንዳልቻለ ነው እሳክሁ የተረጋገጠው። ሩሲያ በማዕቀቡ  እንዳልተሽመደመችና ይልቁንም ቻይናንና ህንድን የመሰሉ አዲስ ደንበኖችን እንዳገኝችና፤  በማእቀቡ ምክኒያት ባሻቀበው የነዳጅ ዋጋም፤  ተጠቃሚ እየሆነች እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፤ በመሆኑም በሩሲያ ላይ በሚወስዱት የማቀብ እርምጃዎች ብቻ ሩሲያን ከዩክሬን አስገድዶ ማስወጣትና በካባቢውም ሰላም ማስፈን አስቸግሪ እንድሆነ  እንደሚቀጥል ነው በብዙዎች የሚታመነው፤  ጦርነቱ ሲራዘምና የሚያስከትለው ችግር እየሰፋ ሲሄድ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት አገሮችም በሩሲያና ዩክሬን ላይ ያሳዩት አንድነት ሊሸርሸር ወይም እንደእሳክሁኑ ላይቀጥል ይችላል ነው የሚባለው ። 

ገበው ንጉሴ  እሸቴ በቀለ

DW listen AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

Leave a Reply