የስንዴ አብዮት!! ኦባሳንጆ [ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ነች] ሲሉ መመስከራቸው ብስጭት ፈጠረ

የተባበሩት መንግስታት ከአስራ አምስት ጊዜ ላላነሰ ስብሰባ የተቀመጠለት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መቀመጫ የሆነውን መቀለን ረግጠው በተመለሱ ማግስት ባሌ ሲናና ወረዳ መታየታቸው ብስጭት መፍተሩ ተሰማ። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ልማት ላይ መሆኗን መመስከራቸው የስንዴን አብዮት ጉልበት ያሳየ ነው ተብሏል።

ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስር አብይ አህመድ በመሩት “ጉብኝት” የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በሲናና ወረዳ በ3 ሺህ 200 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማውን የሥንዴ ማሳ መጎብነታቸው የተዘገበው በመንግስት መገናኛዎች ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክና የዓለም ባንክ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃለ የገቡለትን የስንዴ እርሻ ኦባሳንጆ ” ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን” ሲሉ ምስክርነታቸውን አሰምተዋል።የስንዴ ፖለቲካ አስቀድሞ የገባቸው አብይ አሕመድ በቅርቡ ለፓርላማ ” ስንዴ ኤክስፖርት ማድረግ እንጀምራለን” በሚል ሲናገሩ ማታ ማታ “የዛሬ” እያሉ የሚተቹ ሲሳለቁባቸው ነበር። ከተቅላይ ሚኒስትሩ እግር እገር ስር እየተከተሉ ስራቸውን ሊያቆሽሹ የሚሞክሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማታ የሚጮሁ እንቁራሪቶች ብዙ እንደሚመስሉ፤ ግን ሲያጠምዷቸው ከሶስት እንደማይበልጡ የሚናገረውን ምሳሌ ጠቅሰውላቸው እንደነበር አይዘነጋም።

“ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘው ስራ አበረታችና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር ነው” ሲሉ ምስክረነታቸውን እዛው ማሳው ላይ ሆነው የሰጡትይ አደራዳሪ፣ “ይህን ማለታቸው ከድርድሩ ጋር ምን ያገናኘዋል” በሚል ቁጣቸውን የገለጹባቸው ድምጻቸውን ያሰሙት ወዲያው ነው።

ስለጀመሩት ድርድር ልክ ዶክተር ለገሰና አምባሳደር ዲና እንዳሉት የጦርነቱ ሁኔታ መሻሻሉን፣ ሰብአዊ እርዳታ በብዛት መግባቱን፣ በጥቅሉ መሻሻል መታየቱንና ይህን መሻሻል ወደ ሚጸና የተኩስ አቁም ስምምነት ለማሸጋገር እንደሚተጉ፣ ነገር ግን ጊዜ እንደሚወስድ ከመግለጽ ውጪ ሌላ የተለየ አስተያየት አልሰጡም። ባንክና ኤሌክትሪክ መስለ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ቀደም ሲል ጀምሮ ሲሰማ የነበረውን ከመሰረታዊ መግባባት በሁዋላ ሊተገበር የሚችል አሳብ በድጋሚ ገልጸዋል። ኦባሳንጆ ለቢቢሲ ይህን ብለው ሲያበቁ በስንዴ ማሳ ውስጥ የአገሪቱ የደህንነት ሹም ባሉበት መታየታቸው ” በአፍሪቃ ቀነድ ዙሪያ መክረናል” ላሉት ክፍሎች በሽታ እንደሆነ ተሰምቷል።

Africa has what it takes to feed itself, ADB chief tells G7 development ministers

Ethiopia no longer imports wheat, thanks to climate resilient technology from the African Development Bank’s TAAT program Ethiopia’s wheat production skyrockets to 2.6 million metric tons, plans to export to Kenya, Djibouti in 2023 Amid a looming…

“የአፍሪካ ሀገራት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉም ይህ ምስክር ነው” ሲሉ ለአገር ውስጥ ሚዲያዎች ያስታወቁት ኦባሳንጆ፣ ይህ አስተያየታቸው ከተሾሙበት ሃላፊነት የስራ ድርሻ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለው ጠቅሰው ነቀፌታ ሰንዝረዋል። ትህነግም ደስተኛ እንዳልሆነ ቢሰማም በኦፊሳል ኦባሳንጆ ማሳ ጎብኝተው ” በሶፍ ኦማር ዋሻ ውስጥ ከቀረጻና ሳተላይት እይታ ውጪ ሆነው መሜስጠራቸው ሴራ ነው” ሲል አልተሰማም።

አፍሪካ በምግብ ምርት ራሷን ትችላለች። ኢትዮጵያን ተመልከቱ የስንዴ ምርቷን በታላቅ እመርታ ወደ 2.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አሳድጋዋለች። በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ስንዴ ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር እንደምትሆን እርግጠኞች ነን። የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ግብርና እመርታ ደጋፊ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል።
አኪንውሚ አዲሳን የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

በ42 ሺህ 901 ሔክታር መሬት ላይ ተንጣሉ እስክስታ የሚወርደውን የስንዴ ነዶ ሲጎበኙ ” የደህንነት አለቃው አቶ ተመስገን ምን ይሰራሉ? ስንዴና እሳቸውን ምን አገናኛቸው” ሲሉ የጠየቁ ነገሩ ሌላ እንደሆነ፣ ለዓለም እንዲተላለፍ የተፈለገው አሳብና ዜናም የተለየ እንደሆነ ይገምታሉ።

ኦባሳንጆ በተሾሙበት የስልጣን ማዕቀፍ መቀለ እንደሆኑ በተገለጸ ማግስት ከኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የደህንነት ሹም ጋር ማሳ እየጎበኙ መነጋገራቸው በትህነግ ላይ እየላላ የሄደ ጉዳይ መኖሩን እንደሚያሳይም የገለጹ አልታጡም። በተቃራኒ ግን ትህነግ ገና ከጅምሩ ” አልጣሙኝም” ያላቸውን ሰው ያወግዛል የሚል ግምት የሰጡ አሉ። እነዚህ ክፍሎች የቀድሞውን የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት “ቺምፓንዚ” ሲሉ የትህነግ ደጋፊዎች መሳደባቸውንም ያስታውሳሉ።

የአፍሪካና የዓለም ባንክ አይናቸውን እንዳጠገበው የመሰከሩለት የስንዴ እርሻ ይበልጥ ሜካናይዝድ እንዲሆን፣ በሌለኦችም አካባቢዎች እንዲሰፋ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በገለጹበት ቅጽበት፣ ኦባሳንጆ ” በኢትዮጵያ ከጦርነቱ ዜና በተለየ በልማት ላይ የሚሰራዉ ስራ ጎልቶ የወጣ ነው” ማለታቸው የአብይን መንገድ ስልትና ስሌት ሲረግሙ ለነበሩ ራስ ምታት፣ ለአድናቂዎቻቸው ደግሞ ” ልክ ነኝ” የሚል ምላሽ የሚያሰጥ ሆኗል።

 • ባልደራስ የሱዳን ልሳን – የሱዳን የውስጥ ቀውስ ማስተንፈሻ ዜና ያራባል
  ባልደራስ ሆይ መንግስትን መቃወም፣ ለስልጣን መሮጥና ኢትዮጵያ ይለያያሉ። ባልደራሶች! በቀላሉ አትገመቱ! ዜናውን ለሚዲያ ተውት! ባልደራስ በርካታ ጉዳዮችን በፌስቡክ ገፁ ይለጥፋል። በአዲስ አበባ ጉዳይ ብዙ ያከናውናል፣ ይሰራል የተባለው ፓርቲ በተቃራኒ የሚያስገምቱትን ተግባራት መፈጸም መለያው ሆኗል። የተራ የ “አክቲቪስት”…
 • በአፋር የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  ከጋላፊ እስከ ሰርዶ በየመንገዱ ዳር ተደብቆ የቆዩት 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተጨማሪም አንድ ቦቴ ጫካ ውስጥ ነዳጅ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ ዘመቻ ከተጀመረ ጌዜ ጀምሮ በየቦታው ተደብቀው የቆዩ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡…
 • ኢራን እና አርጀንቲና “ብሪክስ”ን ለመቀላቀል ማመልከቻ አስገቡ
  ኢራን እና አርጀንቲና የ “ብሪክስ”ን ቡድን ለመቀላቀል ማመልከታቸው ተሰምቷል፡፡ ኢራን እና አርጀንቲና ቡድኑን ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረቡት ባሳለፍነው ሣምንት በተካሄደው የ“ብሪክስ ፕላስ” ጉባዔ ላይ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ በ“ብሪክስ ፕላስ”…
 • ብልጽግናና የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
  የብልጽግና ፓርቲ እና የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ እና በቅርቡ የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ሊዩ ጂያንቾኦ የዌብናር ውይይት አድርገዋል፡፡ በአፍሪካ…

Leave a Reply