ቅዱስ ሲኖዶስ ኦርቶዶክስ የአስታራቂነት ሚናዋን እንደምትወጣ ገለጸ

በሀገሪቱ የተከሰተውን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት እና ዜጎች በሀገራቸው ተረጋግተው መኖር እንዲችሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአስታራቂነት ሚናዋን እንደምትወጣ ገለጸች።

ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

የጉባዔውን ቆይታ አስመልክቶም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፓትርያርኩ በመግለጫቸው ሲኖዶሱ በቤተክርስቲያኗ እና ሀገራዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መምከሩን እና ውሳኔዎችን ማሣለፉን አብራርተዋል።

ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያስተዳድሩ ቅዱሳን አባቶችን የሰየመው ሲኖዶሱ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶሱ ፀሐፊ አድርጎ መሠየሙን ብፁዕነታቸው አብራርተዋል።

ሲኖዶሱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተለይም በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች እየተፈፀመባት ያለውን የስርአተ አምልኮ መስተጓጎል ችግር አስመልክቶ በጥልቀት መወያየቱን ገልጸዋል።

በቤተክርስቲያኗ እና አገልጋዮቿ ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ እንዲቆም እና አጥፊዎች ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸውም ቤተክርስቲያኗ ጠይቃለች።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው ለችግሩ መፍትሄ ለማፈላለግ ከሲኖዶሱ ጋር መወያየታቸውን በመግለጫቸው ገልጸዋል።

የክህነት አሰጣጥን አስመልክቶ ምልአተ ጉባኤው መምከሩን እና ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል፡፡

ከቤተክርስቲያኗ ተገልሎ የነበር ግለሰብ በጠየቀው መፀፀት ምህረት እንደተደረገለትም ብፁዕነታቸው አስገንዝበዋል። በትግራይ ክልል ስለ አለው የቤተክርስቲያኗ ሁኔታም ቅዱስ ሲኖዶሱ መወያየቱን በመግለጫው አብራርተዋል።

በሀገራቸው በተከሰተው የሰላም መደፍረስ ለተጎዱ ወገኖችም ቤተክርስቲያኗ እንድትደግፍ መወሰኑንም አቡነ ማቲያስ በመግለጫቸው ገልጸዋል።

(አሚኮ)

  • “ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
    ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የዓለም መገናኛዎች ርዕስ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ለቆ የመውጣቱ ጉዳይ ነው። የሶማሊያ ባለሥልጣናት ስለጉዳዩ የተነገራቸው አንዳችም ነገር እንደሌለ መግለጻቸው፣ አልሸባብም የሠራዊቱን እግር እግር እየተከተለ የተነጠቃቸውን ወረዳዎች መቆጣጠሩና ኢህአዴግ ጉዳዩን ያስተባበለበት አግባብ ጎልጉል የመረጃ አቀባዮቹን እንዲያነጋግር መነሻ ሆኗል። እንደ መረጃ ሰዎቹ ከሆነ በስም ተለይቶ ባይገለጽም ህወሃት በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ድርጅት ጋር … Read moreContinue Reading
  • Landlocked Ethiopia to Rebuild its Navy
    France agreed to support Ethiopia to build a naval force, yet it would take years for Ethiopia to procure the ships and train the forces required for a fully-fledged navy. Ethiopia plans to rebuild its navy, 27 years after it became landlocked following the independence of Eritrea and the disbandment … Read moreContinue Reading
  • Ethiopia and Eritrea Have a Common Enemy
    Abiy Ahmed and Isaias Afwerki are racing toward peace because they both face the same threat: hard-liners in the Tigrayan People’s Liberation Front. By Bronwyn Bruton Ethiopia’s new prime minister, Abiy Ahmed, made headlines across the world with his surprise move last month to resolve his country’s two-decade-long fight with Eritrea. The nation of Eritrea … Read moreContinue Reading
  • “አእምሮዬ አልዳነም!”
    “በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … Read moreContinue Reading
See also  አብን በክልሉ ክተት አወጀ - " ተፈጥሯዊ ራስን የመከላከል መብትህን ተጠቀም" ብሏል፤ የክልሉ መንግስት ይጠበቃል

Leave a Reply