“አብይን አስወግደው አለኝ” – በቁጭት እየወጡ ያሉ ሚስጢሮች

ለውጡን ተከትሎ በዋና ተቃዋሚዎች አንደበት ይፋ እየሆኑ ያሉት ሚስጢሮች የበሻሻው መንደር ልጅ አብይ አሕመድ ” ኢህአዴግ ነበሩ?” ብሎ ለመጠየቅ ከበቂ በላይ ምክንያት ነው። ምስክርነታቸው ብቻ ሳይሆን ዘመቻው ሁሉ አብይ ለይቶ የሚያጠቃ መሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ነው።

“ዝም ብዬ ሶስትና አራት ዓመታት ኢንሳን መርቻለሁ” የሚሉት ብርጋዴር ጄ/ል ተክለብርሃን በአንድ ወቅት በተካሄደ ወ/አረጋይ በአንደበታቸው የተናገሩትንና አስፋው አብርሃ ወደ አማርኛ የመለሰው ቪዲዮ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ጀነራሉ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም ጠርተው “መለስ አስወግደው” ሲለኝ ” እንዳይፈናፈን አድርገን እንቆጣጠረዋለን” ማለታቸውን በቁጭት ሲገልጹ በማስረጃ ቀርቧል። ቪዲዮዎቹን እዚህ ላይ ሊንኮቹን ተጭነው ይመልከቱ። https://t.me/wlkayi

“በኢትዩ ኤርትራ ጦርነት ወቅት አቢይ አህመድ ኦሮሞ ስለነበረ መከላከያ ሲግናል መምሪያ ውስጥ ኦፕሬተር አድርገን መደብነው። ከግምባር ከተመለሰ በኋላ ነበር የመደብነው። በጣም ጥሩ የሆነ የኮሚኒኬሽን ችሎታ ነበረው።እኔ በአቢይ ችሎታ እደነቅ ነበር። ያኔ አቢይ ተመልሶ ሲግናል ከተመደበ በኋላ አንድ ፅሑፍ አምጥቶ ‘አሳትምልኝ’ አለኝ።እራሴ ሃላፊነቱን ወስጄ ፅሑፉን ብቀበለውም በወቅቱ መከላከያ ውስጥ ገንዘብ ማግኘት ከባድ ስለነበረ ገንዘቡን አልፈቀዱለትም። በ2002 ዓ.ም ከእንግሊዝ አገር እንደተመለስኩ ከመለሰ ዜናዊ ጋር ተገናኝተን ነገሮችን ከገመገምንና ከመከርን በኋላ መለስ ዜናዊ …”ይሄ ልጅ ኦሮሞ ስለሆነ አደገኛ ነው፤ አስወግደው አለኝ” ይላሉ ጀነራሉ።

  • እኔ ግን ” ወደ ኦሮሞዎቹ ሄዶ ወደ ላይኛው እርከን ከወጣ ችግር ይፈጥርብናል።ሳናባረው እዚሁ ከኛ ጋር እንዳይላወስ አድርገን ኩርምት ብሎ እንዲቀመጥ በማድረግ contain እናደርገዋለን ” አልኩት።
  • መለስ ዜናዊ ግን ” ኖ ኖ ምክንያት ካገኘህለት ዝም ብለህ ብቻ አስወግደው” አለኝ ።
  • እኔም ” ምክንያት እማ ሞልቷል ብዬ 4 እና 5 ምክንያቶችን ጠቅሼ አቢይን አባረርኩት “
    -አቢይ በዚህ ተበሳጭቶ አልቃቅሶ ወጣ። ጀነራሉ ይህን አስከትለው ሌለም ሌላም እያሉ ይቀጥላሉ

አብይ አሕመድ አምቦ ስብሰባ ተቀምጠው፣ በቤተ መንግስት ከኦሮሞ አባቶችና ታዋቂ ሰዎች ጋር ሲወያዩ ” ነዲ ገመዳን ውለድ” በሚል ወጥረው ያዘዋቸው ነበር። በነገራችን ላይ ነዲ ገመዳ ኦነግ ውስጥ ከነበሩ አስተዋይ፣ የረጉ፣ በርካቶሽን ከምስራቅ ሃረርጌ ሞት የታደጉ፣ ሰዎችን እኩል የሚያዩ ቀለም የገባቸው ሰው ነበሩ። እሳቸውንና ሌሎችን ስም በመጥራት የት እንደደረሱ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ ስለነበር አብይ አሕመድ አምቦ ላይ ያደረጉት ንግግር እምባ አራጨ።

አብይ አህመድን ስልጣን በያዙ ማግስት በሰኔ ለማሰናበት ሙከራ ተድርጉል። ገና መቀመጫቸው ያልጠነከረው አብይ አሕመድ በጠዋቱ የግድያ ሙከራ ማስተናገዳቸው ብቻ ሳይሆን ለውጡን ባልተቀበሉ ቅሬቶች መፈንቅለ መንግስትም ተሞክሮባቸዋል። ከመካከል እምቢ ሲል ከክልል ማፍረስ ለመሞከር በአማራና በሶማሌ ክልል መንግስት ለመፈንቀል ተሞክሮ አሳዛኝ ሪኮርድ ተመዝግቧል። ይህን ሁሉ አልፈው ባዶውን ቤት ገንብተው ወደ ህግ ማስከበር የተሸጋገሩት አብይ በቀጣይ ትግሉ እነደሚቀንስላቸው ቢነገርም ” ኢትዮጵያዊ ” መሆናቸው የእግር እሳት የሆነባቸው ከውስጥና ከውጭ ተናበው የሚያደርጉትን ዘመቻ ገዝግዝ ህዝብ እይነጥፈው እንደሚሄድ በግል አምናለሁ። ምስክሩም ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ በሁዋላ “ተምስገን፣ አረፍን” የሚለው ድምጽ ጎልቷልና ….

የኦነግ አመራሮች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ሲል ቀድመው መረጃ በመስጠት ሕይወታቸውን አደጋ ውስጥ እየከተቱ መረጃ ይሰጡ እንደነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ተንፈሱ። የስብሰባው መረጃ የደረሳቸው ጉዳዩን እሳቸውን ለማራከስ ሊጠቀሙበት ሲሞክሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ግልጽ ባለ ቋንቋ ” አድኖናል” ሲሉ ዝርዝሩን ጉዳይ አንስተው መሰከሩ።

በወቅቱ ንጉስ ብቻ አገር እንደሚመራ ወይም መሪ መሆን “ንግስና” እንደሆነ የሚያውቁት የአብይ አሕመድ ጀዝመኛ እናት ዓላማ አስታጠቀው ” ንጉስ ትሆናለህ” በሚል ታላቅ ህልም አንጸው ያሳደጉት ልጃቸው ኢህአዴግን ቢቀላልቀልም “ያመኑ” ኢህአዴግ እንዳልነበሩ እየተሰማ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቃላችውን፣ ኮቴያቸውን፣ ስራቸውን፣ ቀለማቸውን፣ ያደጉበትን መንደርና አካባቢ እያመላከቱ ሲያበሻቅጡዋቸው የሚውሉትና እሳቸው ” የማታ እንቁራሪቶች” የሚሏቸው እናታቸውን ሲዘልፉ ይሰማል።

ሃብታሙ አያሌው ” ቤተሰብና ሚስት ስላለውና የሚጻፈው ሁሉ አየር ላይ ውሎ ነገ ለቤትሰብ አሳፋሪ ታሪክ፣ ለልጆች መሸማቀቂያ እንዳይሆን ብዙ ከመሳፍ እቆጠባለሁ” አንዱ የአብይን ጀግና እናት ዘላፊ ነው። በእስር ቤት “ጥቃት” የተፈጸመበትና በመደፈሩ ሳቢያ ከገጠመው የስነልቦና ቀውስ ያልወጣው ሃብታሙ እኚህን ልጃቸውን “ትነግሳለህ” ብለው ዓላማ በማስጨበጥ ወደ ከፍታ የመሩ እናት የመስደብ ሞራሉ ከጤነኛ አዕምሮ የሚመነጭ እንዳልሆነ፣ ከተደፈረ ስለ ልቦናና ከተደረመሰ ማንነቱ የሚቀዳ መሆኑንን ብቻ ለመጠቆም እወዳለሁ። ስለ ኤርሚያስ አቃቂ አስተማሪ እያለ ትህነግ በመለመለው ማግስት ስለታጋዮች እያለቀሰ ሲያወራ የሚያውቁትን መምህራን ምስክር እንዲሰጡ ከመመኘት ውጪ ምንም አይባልም። ብሩክ የሚባለውና አንደኛዋ በስም ለመጠራትም የማይበቁ ልቅላቂ ጨዋዎች በመሆናቸው “እንደው ዝም” በማለት እነሱን ቁጭ ብለው በሚሰሙት ላይ በመሳቅ ወደ ጉዳዬ አመራለሁ።

አብይ አሕመድ እውስጥ ሆነው በስጋ፣ በልቡናቸው ራሳቸውን ለመሪነት ሲያንጹ እንደነበር ተነቅቶባቸው እንደነበር ስብሃት ነጋ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ ድምጹ የጠፋው ዳንኤል ብርሃኔ፣ በርካታ አክቲቪስት ነን የሚሉ የትህነግ ሰዎችና ትህነግ የሚከፍላቸው ወያኔ አማራና ኦሮሞዎች ወዘተ በተደጋጋሚ ምስክረነት ሲሰጡ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይህን አጭር ማስታወሻ ለመሳፍ ያነሳሳኝ ” አብይ አሕመድን በዚህ ደረጃ ለይቶ መደብደብ ለምን አስፈለገ” የሚለውና ” በተለያዩ ሚዲያዎች ” እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል የተጠናና ከማእከል የሚወርድ የጥላቻ ዘመቻ የመከፈቱን ሚስጢር ሳሰላስል ጀነራሉ በይፋ የተናገሩትን በመስማቴ ምን አልባትም ይህ ጉዳይ መነጋገሪያ ሊሆን የሚችል፣ በርካታ ጉዳዮችን የሚመዝ፣ በዚህ ደረጃ ከተጠሉና ከተነቃባቸው እንዴት እንዲወገዱ አልተደረገም? እንዴት ዓላማቸውን ለማሳካት ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮችን መመርመር …

አብይ አሕመድ ” የምናደርገውንና የምናስበው የሚገባቸው ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ የተናገሩትንና ” አምላኬ ምን እንዳደረገና ከምን እንዳወጣን ስለማውቅ አመስገናለሁ” ማለታቸው፣ ዘወትር ” እናቶች ጸልዩ” ሲሉ መማለዳቸው ለእኔ ዛሬ ላይ ብዙ እየነገረኝ ነውና ይህም በረጋ መንፈስ ቢሰላ ጥሩ ልምድና የዕምነትን ሃያልነት የሚያሳይ ሆኖ አገኘዋለሁ።

ጀነራሉ አብይን አስመልክቶ በንዴት ከሚናገሩት በላይ ያስገርመኝ “ወደ ውስጣችን (self reflection) ማየት ተስኖን ስለነበር ይሄን ሁሉ አመታት አብረን ስንኖር የኦሮሞ ህዝብ ምን እንደሚፈልግ እንኳን በጭራሽ አናውቅም ነበር።ዝም ብለን ነበር ብሔር ብሔረሰብ ስንል የኖርነው።በነገራችን ላይ መከላከያ ውስጥ ራሴን ያሳምመኝ የነበረው ይኼው የብሔር ብሔረሰብ የተዋፅኦ የምናምን ግምገማ ጉዳይ ነበር።የኦሮሞውን ፍላጎት አለማወቃችን ብቻ አልነበረም ችግራችን።ባጭሩ ኦሮሞን አናውቀውም ነበር። ከዛ በኋላ መጨረሻ ላይ አመፁ ተጀመረ — ያው እንደምታስታውሱት አፈር ድሜያችንን ግጠን ወደ መቀሌ …”

እዚህ ላይ ጀነራሉ ምርጥ ቁም ነገር አንስተዋልና በይፋ ምስጋና እቸራለሁ። ግን ከረፈደ ሆነ። በጎን ኦሮሚያ ውስጥ ነውጥ እንዲፈጠረ የሚያደርጉትን የይፋ ዘመቻና የጦር እርዳታ ስመለከት ሰነፍ ተማሪ መሆናቸውን ባመስገንኩበት ደረጃ ማስታወቅም አለብኝ። ጥሩ ገምግመው ከግምገማቸው ያልተማሩ፣ ለመናገር ያህል እንጂ ተመልሰው በቀድሞው መንገድ እየዳከሩ ናቸው። ኦሮሞ በፊት ምን እንደሚፈልግ ሃያ ሰባት ዓመት አያውቁም ነበር። ይህን ተረድተው አሁንም ባለማወቁ መንገድ የሰገሩ ነው። ኦሮሞ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ምን እንደተደረገበት፣ በማን እንደተደረገበት የማያውቅ ተላላ ሕዝብ መስሏቸዋል። ያስቃል። ደግመው ኦሮሞ ላይ ቂብ ሊሉ ይመኛሉ። የትኛውን እንደሆነ ባለውቅም ” መንጋ” ሲሉት የነበረውን ቄሮ “ኦሮሞን አጥፍተህ ትህነግን አንግስ” እያሉ በምናብ ያብዳሉ ……

ከጄ/ል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የተገኙ ቁምነገሮች ሲል ተርጓሚወ አስፋው አብርሃ የተወሰኑ ነጥቦችን ከቪዲዮ ተርጉሞ አስፍሯል።

የስራው ሁሉ መስፈርት የብሔር ተዋፅኦ በነበረበት ሰዓት ለስራ አስቸግሮን ነበር።በተደጋጋሚ ጊዜ መለስ ዜናዊም ይነቅፈኝ ነበር።ሌሎች ብሔሮችን ወደሱ(ወደ ኢንሳ) አታስገባ ይለኝ ነበር።ስለዚህ merit based የሆነ ቅጥር ለመፈፀም ከዚህ መስፈርት ውጪ (bypass) የሆነ አሰራር ተከተልን።ሌላ ህግ አወጣን።

  • በዚህ መሰረትም በMIT የተመረቁ 117 ትግሬዎችን እንዳሉ በሙሉ ቀጠርናቸው።ቋንቋና ትርጉም በሚፈልጉ የስራ ዘርፎች ላይ ደግሞ የተወሰኑትን ከተለያዩ ብሔሮች ቀጠርን።እናም ተቋሙን ትግሬዎች ነበር የምንመራው።
  • እኔ ራሴ የሹመት ወረቀት ሳይኖረኝ በdefault የኢንሳ መሪ ሆኜ ነው ሶስትና አራት አመታት የሰራሁት።
  • በምክትል ደረጃ አንድ ኦሮሞ ነበር።(አንድ ነው አይደል? ብሎ ቢኒያምን ይጠይቀዋል።
  • በግለሰብ ደረጃ እኔ ተቋሙ ውስጥ የነበሩት ኦሮሞዎች እንዲያድጉና እንዲበዙ እፈልግ ነበር።
  • ተቋሙ ውስጥ ጥቂት አማራዎችም ነበሩ።ግን አይመቹም ። ….አዎ አስቸጋሪ ነበሩ፤ አይመቹም !!

የአስፋው ማስታወሻ ብዙ ይናገራል። እንግዲህ የበሻሻው አብይ ከዚህ ትብታብ ውስጥ ነው የወጡት። ከዚህ ትብታብና ከዚህ ዋሻ ወጥተው ነው ” ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ” በሚል በኢትዮጵያ ፓርላማ ለመናገር የበቁት። አምላክ የለም በተባለበት ቤት ውስጥ በዕምነቱ ጽኑ ለሆነው የአገሩ ህዝብ እናቱን አንግሶ ” ኢትዮጵያና ህዝቦን ፈጣሪ ይጠብቅ” የሚል መሪ ሲነሳ አገር ተዓምር አለ። አገር ጉዳ አለ። አገር በደስታ አበደ። አገር ምን እየሆነ ሊረዳው በማይችለው ደረጃ ሰከረ። ” እኛ ነን አሸባሪዎች” ብሎ ይቅርታ የሚጠይቅ መሪ ሲነሳ ህዝብ በደስታ ዞረበት። በቅጽበት አኩራፊዎች ጉድጓድ መማስ፣ እዛም እዚህም ማንደድ፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ …. በታላቅ ጀዝም የተነሱት መሪ እሳት አጥፊ ሆኑ። ብዙ መከራ አለፈ። ኢትዮጵያ እንደ አገር ተፈተነች። መከላከያ ታረደ። ዓለም አደመ። ዓለም “ኢትዮጵያን” ጠላ። ኢትዮጵያ ላይ አድሞ ተነሳ። በኢኮኖሚ ከውስጥም ከውጭም ቦረቧሯት። በቅንጅት በሏት።

ከዛ ሁሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ ግምብ መከላከያ ገነባች። የፈረሰው ባህር ሃይል ተመለሰ። አየር ወለድ ዳግም ተወለደ።የነበልባል ጦርና ፈጥኖ ደረሻ ዳግም ተደራጁ። የጥቁር አንበሳ ካዴት ተመራቂዎች ተወለዱ። ምሁራን መከላከያን ከበቡ። አየር ሃይል መዘመኑን ጠላት በሚመሰክረው ደረጃ ይፋ ሆነ። ፖሊስና ደህነነቱ ተዋቀረ። ዘመናዊ የጸጥታ ማስጠበቂያ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ተቻለ። የረከሰውና የተዋረደው የኢትዮጵያ መከላከያ ከላይ እሰከታች ተበጀ። “ተሸጠ” የተባለው ህዳሴ አፈካ። በስቃይና ጣር ውስጥ የስንዴ ነዶ ሲውረገረግ ታየ!! ታዲያ …. ከዛ … ነገሩ ሁሉ ወለል ብሎ ታየኝ። አብይ አህመድን በደቦ፣ በድርጅት፣ በግርድና፣ ሲያበሻቅጡ መዋልና ማደር የተፈለገበት ሚስጢር እንደኔ ለገባችሁ ” የስንዴ ልመናን ተረት ለማድረግ እንነሳ” እላለሁ!!

Leave a Reply