ከመቀለ – ለትግራይ ዲያስፖራ “ለማን እንደምትጮህ እወቅ”

ሰሞኑንን በትግራይ የሃይደር ሆስፒታል በነዳጅ እጥረት ምክንያት ኤሌክትሪክ መቋረጡ ተገልጾ አስደንጋጭ ዜና በይፋ ከክልሉ ሃላፊዎች ተሰምቶ ነበር። ይህንኑ ዜና የተለያዩ ሚዲያዎች ተቀባብለው አቅርበውታል። ኤሌክትሪክ በመቋረጡ አዲስ የሚወለዱ ሕጻናትን ጨምሮ ሰለባ መሆናቸው ይፋ ሆኗል።

ሰሞኑንን አፋር ተገኝተው ወደ ትግራይ የሚላከውን ዕርዳታ ስርጭት የገመገሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተቀመጠው የነዳጅ መተን በላይ ወደ ትግራይ መላኩ አግባብ እንዳልሆነ፣ ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችም አብረው ከቀለብ ጋር ወደ ትግራይ እንዲገቡ መደረጋቸውን ጠቅሰው የዕርዳታ ድርጅቶች ከዚህ ተግብራቸው እንዲቆጠቡ፣ ጥበቃና ፍተሻው ግን ከወትሮው ሁሉ እንዲጠብቅ መመሪያ ምስጠታቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፕሬስ ሰክሬታር ቢለኔ ስዩም ትናንት ለውጭ ጋዜተኞች ሲያስረዱ ከ2 ቢልዮን ብር ብላይ ወደ ትግራይ መላኩን፣ መንግስት ነዳጅን ጨምሮ ዕርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ያላሰለሰ ጥረት እይተደረገ መሆኑንን፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፐሬዚዳንት ኦባ ሳንጆ የጀመሩትን የሰላም ጥረት ኢትዮጵያ በሙሉ ሃይሏ እንደምትደግፍ ይሁን እንጂ በትግራይ ሕዝብ ነሳ አውጪ በኩል ያለውን አቋም እንደማያውቁ ግልጽ አድርገዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የዳንኤል ብረሃኔ ወንድም ፍጹም ብርሃኔ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ከመቀለ “እንደምታውቁት ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በነዳጅ እጦት ምክንያት (የትግራይ መንግስት ነዳጅ የለኝም ስላለ) በጄነሬተር ሊሰጥ የሚችለውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደቆመ አሳውቅዋል በዚህ ምክንያት የሚጠፋው ህይወት መገመት አይከብድም” ሲል የችግሩን አሳሳቢነት ጠቅሶ፣ ጎን ለጎን ንቀትና ለህዝብ ጥላቻ መሆኑንን በመግለጽ የትህነግን ባለስልጣናት አግዟል።

” የባለስልጣኖች መኖሪያ ቤቶች ላይ ሙሉ ለሊት ጀነሬተር በርቶ የሚያድርበት ምክንያት ንቀትና ለህዝብ ያለን ጥላቻ ከመግለጽ ውጭ ሌላ ትርጉም ልኖረው አይችልም” ሲል ሆስፒታል ጨለማ ውጦት፣ ባለስልጣናት መብራት ሲጠቀሙ መመለከት አሳዛኝ እንደሆነ አስታውቋል።

“…የእነሱን ምቾት እንዳይጓደል ህጻናት በሕክምና እጦት ምክንያት ሊሞቱ አይገባም። ሙሉ ትግራይ አጨልሞ የባለስልጣናት ቪላ እንዲበራ የሚያስችል ሞራልና ህሊና ያለው አመራር የህዝብን ችግር በፍጥነት ለመፍታት ተግቶ ይሰራል ብልህ ማመን የዋህነት ነው “ ሲል ሃሳቡን የቋጨው ፍጹም ብርሃኔ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የተቃውሞ ድምጽ ማሰማቱ ይታወሳል።

የትህነግ መሪዎች በቂ ዕርዳታ እንዳላገኙ፣ የነዳጅ ችግር መኖሩን፣ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ ኡአደርጋሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የዓለም አቀፉን የምግብ ድርጅት ጨምሮ በበጎ ተግባር የተሰማሩ ድርጅት ሃላፊዎች በይፋ መንግስት የርዳታ እህል እንዲገባ ያሳየውን ፈቃደኛነት ሲያደንቁ ተሰምቷል።

በየብስና በምድር ከፍተኛ መተን ያለው እርዳታ መግባቱን መንግስት አሃዝ ጠቅሶ ቢገልጽም ከትግራይ ባለስልጣናቱ ከሚፈለገው አንጻር በቂ እንዳልሆነ ይገልጻሉ። የሚገባውን እህል ለወታደሮቻቸውና ለመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም ለዘመቻ ጥሪ ልጆቻቸውን ላቀረቡ ቤተሰቦች እንደሚሰጡ የሚያሳዩ መረጃዎችና የቪዲዮ ማስረጃዎችም እየወጡ ይገኛሉ።

በትግራይ ከፍተኛ የደህንነት ችግርና የጸጥታ ስጋት ከፍተኛ ቀውስ መሆኑንን፣ በርካታ ወታቶች ታጣቂ በመሆናቸው ለዝርፊያ ሲባል በገሃድ ግድያ እንደሚካሄድ ቢቢሲ ነዋሪዎችንና ባለስልጣናቱ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

Leave a Reply