አማራን ለይቶ የተካሄደው ጭፍጨፋ – ክልሉ የጀመረውን የህግ ማስከበር ስራ መስመር ለማሳት መሆኑ ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩባቸው መንደሮች የተፈጸመው ጥቃት አማራ ክልል እያካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ለማስተጓጎል ሆን ተብሎ በቅንጅት የተፈጸመ ስለመሆኑ መረጃ መገነቱ ተሰማ።

ለኢትዮ12 መረጃ የሰጡ እንዳሉት በሚከበረው ፋኖ ስም በኢመደበኛ መልኩ የተደራጁና ክልሉ “ተልዕኮ ፈጻሚ” የሚላቸው ሃይላትን ለማረቅ የተጀመረው የህግ ማስከበር ከ3500 በላይ እንዲከዱ የተደረጉ የመከላከያና የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውሰው፣ ይህ መሆኑ በተልዕኮ ሰጪዎች ዘንዳ ከፍተኛ ስጋት ማንገሱን አመልክተዋል።

በአማራ ክልል የታሰበው ሁሉ መክሸፉ ያበሳጫቸው “ተልዕኮ ሰጪዎች” በኦሮሚያ ክልል ካላቸው የትግል አጋር ጋር መክረው ከወትሮው በተለየ ቁጥሩ የበዛ የአማራ ተወላጆችን እንዲገደሉ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። መረጃ ሰጪዎቹ እንደሚሉት ይህ ጭፍጨፋ ከተፈጸመ በሁዋላ “የአማራ ተቆርቋሪ ነን” የሚሉ አክቲቪስቶች ” ፋኖ ሆን ብሎ እንዲለቀም የተደረገው አማራን ለማስጨረስ በተቀመጠ ዕቅድ መሰረት ነው” በሚል ህዝብ የህግ ማስከበሩ ላይ ብዥታ እንዲፈጠርበትና እንዲቃወም ለማድረግ ቅስቀሳ እንደሚጀምሩ ዕቅድ መኖሩን አመልክተዋል።

ክልሉ ሰሞኑንን 3 ሺህ 746 እንዲከዱ የተደረጉ የመከላከያ ፣ የልዩ ኃይልና የፖሊስ አባላት መያዝቸውን፤ ከ8 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል። ሕዝቡም አንጻራዊ ሰላም ማግኘቱና ከኢመደበኛ ሃይላት ዘንዳ የሚጣልበት ግብር፣ መዋጮና ጫና መገላገሉ ገልጿል። የህግ ማስከበሩ እንዲቀጥል የጠየቁ አካባቢዎችም አሉ።

አማራና ኦሮሞ እንደ ክልል እሳትና ጭድ እንዲሆኑና ወደ ለየለት ግጭት እንዲገቡ ለማድረግ በአማራ ላይ ሆን ተብሎ የሚፈጸመው ግድያ በርካቶችን ያበሳጨ፣ ያሳዘነ፣ እንድሁም “እስከመቼ” የሚል ጥያቄ ያስነሳ ሆኗል።

መንግስት በየትኛውም አገር ሁሉንም መንደር መተበቅ እንደማይችል ቢታወቅም በኦሮሚያ ክልል ያሉ የአማራ ተወላጆች ተደራጅተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለምን እንደማይደረግ የበርካቶች ጥያቄ እንደሆነ የሚገልጹ፣ አሁንም ብቸኛው አማራጭ ይህና ይህ ብቻ መሆኑንን ያስረዳሉ።

ሰሞኑንን የክልሉ ገናና ብዙሃን እንዳሉት ለትህነግ ሊተላለፍ ነበር የተባለ ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል። ኮሚሽኑ እንዳለው ህግን ለማስከበር በተወሰደው እርምጃም በክልሉ ሕገ ወጥ ተኩስን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎች መቀነሳቸውን ግልጿል። ይህ በሆነ ማግስት ነው ከጋምቤላው ነውጥ በቀታይ ይህ አስደንጋጭ እልቂት የተሰማው።

የአማራ ክልል ባለፈው አንድ ወር ባካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ12 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ግልጾ፣ እነዚህ ተጠርጣሪዎች በፋኖ ስም የሚነግዱ እና በተለያዩ ኢ-መደበኛ ቡድኖች ተደራጅተው በግድያ፣ በዘረፋ እና በአስገድዶ መድፈር እና አሸባሪ ከተባሉ ቡድኖች ተልዕኮ ወስደው ክልሉን በማናጋት ወንጀሎች የተጠረጠሩ መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃኑ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነርን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 746 የመከላከያ፣ የልዩ ኃይል እና የፖሊስ አባላት ሲሆኑ፣ ከ8 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። የክልሉ መገናኛ ብዙኃን – አሚኮ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሶ እንደዘገበው ተጠርጥረው በፖሊስ ከተያዙት ውስጥ ከ3 ሺህ 750 በላይ የሚሆኑት በዋስትናና በማጣራት ከእስር ተለቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ለህወሓት ሊተላለፍ ነበር ያለው ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙን ኮሚሽኑ አክሏል። በተወሰደው እርምጃም በክልሉ ሕገ ወጥ ተኩስን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎች መቀነሳቸውን አመልክቷል።

ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊት በክልሉ ያሉ ሁኔታዎችን በሰላም ለመፍታት ጥረት መደረጉንና አለመቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰው፣ በክልሉ የተካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻም ሙሉ በሙሉ በክልሉ ልዩ ኃይል መከናወኑንም አመልክተዋል። በዚህም ሕዝብ እፎይታ ማግነቱንና መደሰቱን ግለጸዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆን እያንዳንዶቹ ክልሎች የህግ ማስከበሩን ዘመቻ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይፋም አድርገው ነበር። ይህ በሆነና ይህ በተሰማ ቀን ዕድሜ ነው ይህ አስደንጋጭ እልቂት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው።

በእልቂቱ ሕሳናት፣ አረጋዊያን ሲቶችና ደካሞች በጅምላ መገደላቸውን የአይን ምስክሮች ቁጥር እየጠቀሱ አመልክተዋል። አሃዙ እያደር እንደሚጭምር፣ አሁን ላይ መከላከያና የክልሉ ልዩ ሃይል ህዝቡን እየጠበቀ መሆኑ ተመልክቷል።

ባለፈው አንድ ወር የክልሉ መንግሥት የሚያካሂደውን ዘመቻ በመቃወም አልፎ አልፎ እንቅስቃሴ ቢኖርም ሰፊ ድጋፍ አግኝቶ ሊቀጥል እልቻለም። በስፋት የሚሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በአማራ ክልል ሕዝብ ኢመድበኛ በሆኑ አደረጃጀት መማረሩ፣ አሁን ላይ አንጻራዊ እፎይታ ማግኘታቸውን እያስታወቁ ነው። አካሄዱ ላይ ያሉ ችግሮች እንዲስተካከሉና ህግ ማስከበሩ በጥንቃቄ እንዲካሄድ ምክርና ማሳሰቢያ የሚሰጡም አሉ።

ከቀናት በፊት የ360ው ኤርሚያስ ” ስም እጠቅሳለሁ” በማለት ጎንደሬን ” ስኳድ አቋቁሜያለሁ እያልክ 200ና 300 ሺህ ዶላር የውሰዳችሁ ሌቦች” በሚል ለይቶ ሲሳደብ እንደነበር ይታወሳል። ኤርሚያስ ” እናውቃችኋለን” እያለ የተሳደባቸውን አካሎች ስም አልተቀሰም። ስኳድ ሲያቋቁሙ ምን ያህል እንደተከፈላቸው ሲናገር ክፍያውን ማን እንደፈጸመና ስኳዱ ምን ለመፈጸም ክፍያ እንደወሰደም አልገለጸም። በብስጭት ለመሳደቡ ምክንያት የሆነው የህግ ማስከበሩ በርካታ ዕቅዶችን በማፍረሱ እንደሆነ ግምታቸውን የሰጡ አሉ።

Leave a Reply