“ፍትሃዊ የውሃ ድርድር የሚለው አያዋጣንም ፣ ድርድር አያዋጣንም ሀገሪቷን ማተራመስ አለብን» ሲሉ ታዋቂው ግብጻዊ ፓለቲከኛና የፓርላማ አባል በይፋ ኢትዮጵያን ማተራመስ እንደሚገባ ይፋ ካደረጉ በሁዋላ የህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ሙሌት መጀመሩ ተሰማ። በተቀናጀ መልኩ በውስጥና በውጭ አገራት ኢትዮጵያ ላይ ዝመቻው በተከፍተበት ወቅት ሶስተኛው ሙሌት መጀመሩ አነጋግሯል።

የኤል ጋህድ ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር ፣በግብጽ ካሉ ጉልበተኛ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ እንደሆን የሚነገርለት አይማን አብድልአዚዝ ኑር ” በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ማተራመስ እንጂ መደራደር ዋጋ እንደሌለው መናገሩ፣ ግብጽ ከኢትዮጵያ የሽብር ሃይሎች ጀርባ ስለመኖሯ ማረጋገጫ ሆኖ ተደርጓል።

ለተለያዩ የሚዲያ ክፍሎችና አክቲቪስት ለሚባሉ በተዘጋጀ ጉብኝትና ነጻ ውይይት ” ሶስተኛውን ሙሌት እናቆመዋለን ብንል ሁሉም ነገር ጸጥ ይላል። ይህ ግን አይታሰብም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መናገራቸውን በቦታው የነበሩ ሰሞኑንን አስታውቀው ነበር።

በሱዳን፣ በዩጋንዳ እንዲሁም በሩዋንዳ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ሬክ ማቻርን በመገንጠል ግብጽ የምትላላካቸውን አገራት ድጋፍ አስተባብራ ኢትዮጵያ ላይ የጀመረችውን ጫና በገሃድ ባጠናከረችበት ወቅት ነው የህዳሴው ሶስተኛውን ሙሌት የተጀመረው።

“ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላምን ማረጋገጥ፣ ተቻችሎና ተስማምቶ አስተማማኝ ቀጠናዊ ሰላም በጋራ የማስፈን መርህ በመከተል የሰላም አማራጮችን ሁሉ እንከተላለን። መንግስት ለሰላም የሚዘረጋውን እጅ እንደግፋለን ነገር ግን መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ መንገድ ትተው ሊዋጉን ለሚከጅሉ ሃይሎች በአጭር ጊዜና በማያዳግም ሁኔታ በምንወስደው ወታደራዊ እርምጃ አገራችንን ዳግም የምናስከብርበት ዝግጅት ማጠናቀቃችንን ለሚመለከተው ሁሉ እናሳውቃለን” ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የ8ኛ ደቦል ዕዝ የሜዳይና አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ካስታወቁ በሁዋላ የህዳሴው ግድብ እንዲሞላ መደረጉ ማናቸውም ዓይነት ሴራ ግድቡን በተያዘለት ዕቅድ መሰረት ከመሙላት የሚያግድ ሃይል እንደሌለ አመላካች ሆኖ ተወስዷል።

Leave a Reply