ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጦር በሚል ስያሜ የሚጠራውና የኢትዮጵያ ፓርላማ “አሸባሪ” ሲል ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር አብሮ የፈረጀው ሸኔ በቄለም ወለጋ ጥብቅ ይዞታው እንደነበር የሚነገርለትን አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቆጣጠሩ ተሰማ።
በቄለም ወለጋ ዞን ቡድን እንደ መነሻና መደራጃ ሲጠቀምባቸው ከነበርይት አካባቢዎች ሸበልና ዋራባቦ አካባቢዎችን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መነጠቁን ያመለክቱት ስማቸውን የሸሸጉ የአካባቢው አመራር ናቸው። ሸኔ ግን ይህን አስመልክቶ የተናገርረው ነገር የለም።

እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተጠቀሱትን አካባቢዎች መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የቡድኑ የመረማመጃ ኮሪደሮች ተዘግተዋል። መረማመጃዎቹ የተዘጉበት ሸኔ ሃይሎቹን ማውጣት አልቻለም።

ይህን ተከትሎ ሸኔ ሃይሎቹን ለማስወጣትና የመንግስትን ሃይል ለማሳሳት ይቻለው ዘንዳ በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ለመሰነዘርና ማቀዱን፣ የተዘዋወረባቸውን አካባቢዎችም እንደተጣጠራቸው በማስመሰል አቅጣጫ ለማስቀየር ፍላጎት መያዙን የመንግስት የጸጥታ መዋቅር እንደደረሰበት የዜናው ሰዎች አመልክተዋል።
መረጃው የደረሰው የመንግስት ጦር ይህንኑ እቅድ የሚያበላሽና በቡድኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ የሚያስችል ልዩ ኦፕሬሽን ማዘጋጀቱ ታውቋል። ስለ ኦፕሬሽኑ ዝርዝር መረጃ ከማቅረብ የተቆጠቡት ክፍሎች፣ በቅርቡ ለየት ያለ ዜና ሊሰማ እንደሚችል ጠቁመዋል።

የጦርነት ውሎው ይህን ቢመስልም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሲል የሚጠራው ነፍጥ ያነገበ ድርጅት “ለሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ ይደረግ” ሲል መግለጫ ማውጣቱን የትህነግ አመራሮች በቲውተርና በፌስቡክ ገጻቸው አራብተዋል። ” አማራና አፋር ክልልን ዘርፎ፣ አውድሞ፣ የጅምላና የተናጠል ግድያ ፈጽሞና ክብረነክ ተግባራትን አከናውኖ የነበረው ትህነግ ይህ ዜና ዶክተር አብይን ለማጠልሸት እየተጠቀሙበት ነው” በሚል ድርጅቱ በአማራ ደም እንደቆመቀረ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

የጥቃቱ ጠማቂ አቀናባሪና፣ ድጋፍ ሰጪ እንደሆነ ጠቁመው ትህነግን የሚከሱ “እንደ ትህነግ ሞራል አልባ፣ አይነ ደረቅና ይሉኝታ ቢስ የፖለቲካ ድርጅት አልነበረም። አይኖርም” ሲሉ በጭፍጨፋው ልባቸው የተነካ አመልክተዋል።

በክፍያ ለትህነግ እንደሚሰራ የሚነገርለት ማርቲን ፕላውት በቲውተር ገጹ በአማርኛ “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የኦሮሞ ሕዝብ፣ የአማራ ተወላጆችን ጨምሮ በኦሮሚያ ውስጥ ለሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ተወላጆች ጥበቃ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳሰበ” ሲል በማይበው፣ ትርጉሙን ባማይረዳውና በማይጽፈው ቋንቋ መረጃ አሰራጭቷል።

የማርቲን ፕላውትን ይህን መረጃ ያዩ በዘራቸው ተመርጠው የሚጨፈጨፉ አማሮች ሆን ተብሎ በመናበብ ግፍ እንደሚፈጸምባቸው አንዱ ማሳያ እንደሆነ አመልክተዋል። አክለውም ” በአማራ ደም ውስጥ ልዩ የፖለቲካ አጀንዳ እንደሚራገብ ያለጥርጥ የሚያሳምን፣ ምንም ብዥታ የሌለው የቅንጅት ስራ ነው” ብለዋል። ትህነግና መንግስት ሸኔ የሚለው አካል በገሃድ አብረው እንደሚሰሩ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ትህነግ ወደ ሸዋ መተጋቱን ተከትሎ የሸኔ ሃይ አዲስ አበባን እንደሚከብ ዕቅድ የነበረ ቢሆንም ይህ ባለመሆኑ ትህነግ በሸኔ ላይ ክፉኛ ተቆጥቶ እንደነበር አንዳንድ መረጃዎች ሲሰራጩ እንደነበር ይታወሳል።

ኦነግ ሸኔንና የሽብር ተግባራቸውን ተቀናጅተው ይፈጽማሉ ፕሮፖጋንዳውንም እንዲሁ።

Leave a Reply