ራሱን “ የአዲስ አበባ ከተማ ባለአደራ ነኝ” በሚል ሰይሞ የሚንቀሳቀሰው ባልደራስ ጭብጡን የሳተ ዜና በማሰራጨት ዜጎች ብሄር ለይተው አንዲጫረሱ ግፊት አያደረገ መሆኑ በስማቸው ዜና የተሰራባቸው ክፍሎች ኣስታወቁ። ባልደራስ ስማቸውን ጠቅሶ አየተገደሉና ቢታቸው አየተቃጠለባቸው አንደሆነ የጠቀሳቸው ክፍሎች መገረማቸውን አመልክተዋል።

በግብጽ ሙሉ ድጋፍ አየተደረገለት የትህነግን አላማ በሚያራምደው የ360 ሚዲያ ባለቤት ኤርሚያስ ዋቅጅራ ምክትል ሊቀመንበርነት የሚመራው ባልደራስ “ በአጣዬ በቅርብ ርቀት የሚገኙ መንደሮች በሸኔ አየተቃጠሉ ናቸው” ሲል በቲውተር ገጹ አራብቷል፤ ሲቀጥልም “ በኣርሶ ኣምባ፣ ሞላሌ፣ዘንቦ፣በርጊቢ፣ሺሰማን በኦሮሞ ብልጽግና በሚደግፈው ሸኔ እየተቃጠሉ ናቸው” ሲል ምንጭና የዜናውን ባለቤት ሳይጠቅስ የረጨው ዜና እልቂትን የሚጋብዝና ከተፈጠረው ጉዳይ ጋር ግንኙነት የሌለው አንደሆነ የኣካባቢው ምስክሮች ኣመልክተዋል።

የባልደራስን መሪ አስክንድር በተደጋጋሚ አስሮ ሲያሰቃየው የነበረውን የትህነግ አላማ በሚደግፍ መልኩ ባልደራስ በኦፊሳል የቲውተር ገጹ ላይ ያራባው ወሬ ““ክፍፍሉ ተጀምሯል። ዋናው አስፈላጊ ነገር የተጀመረውን ክፍፍል እንዴት እናሰፋዋለን የሚለው ነው” ሲሉ የትህነጉ ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት የወለጋውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከተናገሩት ጋር የተያያዘ ሆኗል።

የተደመጡት የቀድሞ የትህነግ ጀነራል አበበ ተከለሃይማኖት ” [ኦሮሞና አማራ] እርስ በርስ እንደሚገዳደሉ እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን?” ሲሉ ጠይቀው እንዴት እርግጠኛ መሆን እንዳለባቸው ማብራራታቸውን ተከትሎ ባልደራስ ኦሮሞና አማራን ለማጫረስ ሆን ብሎ ያሰራጨው ዜና ሽብር አንደሆነ ታዛቢዎቹ አመልክተዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ምክንያት የተለመደው የአርሶ ኣደሮች የግጦሽ መሬትና የሰብል ጉዳይ አንደሆነ ምስክሮች ነግረርውናል። ከኣጣዬ ያነጋገርናቸው “ግጭቱ የተለመደ ኣካባቢያዊ ግጭት አንጂ አንደተባለው በኦነግ የተከሰተ ግድያም ሆነ ቃጠሎ አይደለም” በማለት ለዋናው ስቱዲዮ ተናግረዋል።

ከብቶች ማሳ ውስጥ ገብተው ሰብል መብላታቸውን ተከትሎ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጤ ቀበሌና በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ አርሶ አምባ ቀበሌ ግጭት መከሰቱን ምስክሮቹ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ባልደራስና ጉዳዩን ሳያጣሩ ለዩቲዩብ ገበያ አንዳራገቡት የተቃጠለና አየተቃጠለ ያለ ቤትም ሆነ በማንነታቸው የተገደሉ ሰውዎች ስለመኖራቸው አስካሁን በመረጃ የተደገፈ ዜና የለም።

መጠነኛ የተኩስ ልውውጥ አንደነበር ያመለከቱት የአካባቢው ምስክሮች “ችግሩ እንዳይስፋፋ የአማራ ልዩ ሃይልና ፌደራል ፖሊስ በጣምራ አየሰሩ መሆኑንን ገልጸውልናል። ችግሩ ከተከሰተ በሁዋላ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ለተጠየቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ኣለመግባባቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ኣካባቢዎቹ ወደተለመደው ሰላማዊ አንቅስቃሴ መግባታቸው ተመልክቷል። አጋጣሚውን በመጠቀም አንዳንድ የሽፍታ አመራሮች ሁኔታውን ለማባባስ ጥረት አድርገው አንደነበርም ታውቋል።

የኣካባቢው ነዋሪዎችም ይህንኑ ተረድተው ራሳቸውን አረጋግተው አንዲቀመጡ የመንግስት ሃላፊዎች ኣሳስበዋል። የባልደራስ ሊቀመንበር ኣክቲቪስት፣ ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች የሚባለው አስከንድር ኣሜሪካ ተቀምጦ “ህልም ኣለኝ” ሲል አንደ ሴሪላንካ ህዝብ መንግስትን አንዲገለብጥ በቲውተር ገጹ ኣስፍሯል፤ አስክንድር ይህን ያለው ድርጅቱ በይፋ የኣማራ ቤት አየነደደ ነው ሲል ከመግለጹ በፊት ነው።

Leave a Reply