የቤት እጣ አወጣጡ ሂደት ላይ በተፈጠረው ኢፍትሀዊነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጡ።
በአዲስ አበባ የቤት እጣ አወጣጡ ሂደት ላይ የተፈጠረውን ፍትሀዊ ያልኾነ አካሄድ አስመልክቶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሐምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ የማጥራት ሂደቱን ሲያከናውን የነበረው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እንዳብራሩት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብን ሃብት ለመጠበቅ ያደረገውን እንደ ተቋምም እንደ ግለሰብም ላደረገው ጥረት ላመሰግን እፈልጋለሁ ብለዋል።
ዶ/ር ሹመቴ ያነሷቸው ዋና ዋና ሃሳቦች፦
👉 ኢንሳ እንዲህ አይነት ስራዎችን እንዲመራ የህግ ሃላፊነትም ስላለበት ስራውን መርቶ እዚህ ደረጃ አድርሷል ብለዋል፡፡
👉 ሲስተሙ ከኑሮው ቀንሶ ተቸግሮ ሲቆጥብ የኖረውን ማህበረሰብ መብት እንዲያጣ የሚያደርግ በመሆኑ ሲስተሙ ተአማኒነት የሌለው ነው፡፡
👉 ሰው ነው ቴክኖሎጂን የሚገነባው ፤ ነገር ግን ፍትህን ያጓደለ ሲስተም ሆኖ ነው ያገኘነው፡፡
👉 ሲስተሙ የመልማት አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያልጠበቀና ሶስቱን አካላት ፤አልሚውን፤ ተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የቀላቀለ እንዲሁም ለምዝበራ ያጋለጠ ነው ብለዋል፡፡
👉 የዳታው አጠቃቀም ከእጅ ንክኪ ነፃ እንዲሆን የሚፈለግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እጅ በዝቶበት የነበረ መሆኑ ታይቷል፡፡
👉 ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር በደረስንበት ደረጃ ተዓማኒ ያልሆኑ ነገር ሲገኝ አቁመን እንዲጣራና እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ እንደሚገባና ሁልጊዜም ይህንን ማድረጋችንን መቀጠል እንዳለብን
👉 በተጨማሪም የአመራር ስነምግባርን ሟሟላት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ሰዎች የተሰጣቸውን የማገልገል እድል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡
አቶ በሃይሉ አዱኛ ከኢንፎርሜሽንና ደህንነት ኤጀንሲ አጠቃላይ የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን
👉 አጠቃላይ ሲስተሙ ፕሪፌሽናል በሆነ መንገድ የተሰራ አይደለም፡፡
👉 የሲተም አዘረጋግ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ አለመሆኑና የሚና ክፍፍል የሌለበት አሰራር መተግበሩ በማጥራቱ ታይቷል፡፡
👉 ሁሉም በአንድ ሰው የተሰራ ነበር፡፡ በአንድ ላፕቶፕ ከስራው ጀምሮ እስከ እጣ ማውጣቱ ድረስ ተከናውኖበታል፡፡
👉 እጣው የወጣበት እለት ጭምር ኢንተርኔት አክሰስ ሲደረግ ነበር፡፡
👉 የጥራት ፍተሻ እንዲደረግ የተጠየቀው አካል ራሱ ማንዴቱ የሌለው መሆኑም ታይቷል፡፡
👉 የተተገበረው እጣ አወጣጥ ሶፍትዌር የተሻለ አማራጭ የነበሩትን ጭምር ያልተጠቀመና መረጣው መንገድ ችግር ያለበት ነው፡፡
👉 የማበልጸግ ሂደቱ በሚከናወንበት ወቅት ከኢንተርኔት ጋር አክሰስ የተደረገ ሲሆን ይህም ፈፅሞ ተአማኒነቱን የሚያሳጣው መሆኑ
👉 የተወዳዳሪዎች ዳታ እና ከባንክና ከቤቶች ተገኘው የአያያዝ ችግር ያለበትና ለቅየራ የተጋለጠ ነበር፡፡
👉 የዳታ ዝርዝሩም ለ5 ቀናት በሰው እጅ ስር ነበር፡፡
👉 ሲስተሙን ያለማው ሰው ለሌሎች የፈጠረው ዩዘር መጠቀሚያ በሚገባ ሲስተሙን እንዳያውቁ የሚከለክል ነበር፡፡
👉 ይህ ግለሰብ በኮምፒውተሩ ስህተቱን ሪፖርት እንዳይደረግ ሚያደርግ ድብቅ ሶፍትዌር ጭኖ ነበር፡፡ በኋላ ግን አጥፍቶታል፡፡
👉 የኮምፒውተሩ የድርጊት ሂደት ዝርዝር በሚታይበት ወቅት ያለፉት 8 ቀናት ኖርማል የነበረ ሲሆን በመጨረሻዎቹ ቀናት ግን ዳታ ማጥፋ የመጨመርና ማዛወር ስራ መሰራቱን ተረጋግጧል፡፡
👉 ይህ ግለሰብ የኮምፒውተሩንም የሰዓት አቆጣጠር ሆነ ብሎ አንድ ቀን እንዲዘገይ በማድረግ ሁሉም ነገር ቀደም ብሎ እንደተፈፀመ እንዲደረግ በጥንቃቄ አከናውኗል፡፡
👉 በአጠቃላይ ለውድድር ብቁ ናቸው ተብሎ የተገለፀው 79 ሺህ ያህል ሰዎች የነበሩ ሲሆን ሲስተሙ ግን በድብቅ ያጋጃቸው ሰዎች 172ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ፡፡
👉 ከዚህ ውስጥ ደግሞ ገንዘብ ቀድመው አውጥተው የተዘጉ ፤የአመዘጋገብ ችግር ያባቸውና ብቁ ያልሆኑ ጭምር ተካተውበታል፡፡
👉 ሲስተሙ የሚፈልገውን አካል እጣ እንዲያወጣ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
👉 ከባንክ የወጣው ዳታ ውስጥ የሌሉ አሸናፊዎች ተገኝተዋል፡፡
👉 አጠቃላይ ሲስተሙ ከብልጸጋ እስከ ትግበራ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ችግር ያለበት ስለሆነ በዚህ አይነት መንገድ የወጣ እጣ ኦፊሽያል አድርጎ መቀበል አዳጋች መሆኑን በምክረሃሳብ ደረጃ ቀርቧል።
(አሚኮ)