የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ ያለመከሰ የህግ ከለላ መብት እንዲነሳ ወሰነ።

ውሳኔው የተወሰነው በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ነው።

የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ኣስታውቀው ነበር።

“ያለመከሰስ መብት ይነሳልን” ጥያቄው የቀረበው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘና ዶክተር ሙሉቀን የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ ነው።

ጉባኤው በቀረበለት አስቸኳይ አጀንዳ መሰረትም ዶክተር ሙሉቀን የምክር ቤት አባል በመሆናቸው ምክንያት ያላቸውን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ መወሰኑን ከከንቲባ ጽህፈትን ጠቅሶ ፋና ዘግቧል።

Leave a Reply