ለተሰንበት ከጀግና በላይ ጎልታለች። ለተሰበት አንደዋላ አየተንሳፈፈጽ መሮጧ፣ በኣጨራረስ ብልህነቷ ኣድናቆቱ ልዩ ቢሆን በባህሪ ብሱል፣ ልቧ ቀናና ሩህሩህ መሆኗ ጎልቷል። ኣብራት ሩጫውን ስታከርና ከታጦዝ ለነበረችው እጅጋየሁ ታዬ ከምስጋና በሁዋላ ያሳየችው ፍቅርና ስሜት በውጢቱ ደስታ ላይ ልብ የሚያርስ ሆኗል።

የቀደመውን የፍጻሜ ኣነሳስ ችግር አርማ፣ ብልጠትን አክላ፣ አንደ ዋላ ተንሳፋ፣ በእልህና በጅግንነት ኢትዮጵያን ካነገሰች በሁዋላ ኣምላኳን ኣክብራ ያመራቸው ወደ እጅጋየሁ ታዬ ነበር። አየተዝለፍለፈች እጅጋየሁ ታዬን በንዴት በተቀመጠችበት ትራክ ላይ ተጠምጥማ አየሳመቻት ኣንድ ነገር ነግራታላች። የሆነ የመንፈስ ፍሬ ኣጉርሳታለች። ለተብረሃን ምን አንዳለች ባይሰማም ለእጅጋየሁ ታዬ ድካም በድል ስሜት አውቅናና ክብር ሰጥታለች።አንዲሁም ” ኣሸንፈናል” ብላታለች። ኢትዮጵያን በችሎታዋና በመላክምነት ኣንግሳ ትምህርትም ሰጥታለች።

ክስር የኢትዮጵያ ፕሪስ ድርጅት ያለፉ ውድድሮችን ኣካቶ የሻፈው ነው። የእለቱ የውድድር መርሃ ግብርም ኣለበት።

ከሦስት አመት በፊት በዶሃ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አቅሙና ብቃቱ እያላት በልምድ ማነስና በጥቃቅን የታክቲክ ስህተቶች የ10ሺ ሜትር ድል ከእጇ ወጣ። ከአመት በፊትም በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተመሳሳይ ወርቁን ተነጠቀች።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ18ኛው የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በታላቅ ተጋድሎ ወርቁን አጠለቀች። የውድድሩን አጨራረስ ከጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴና ኬንያዊው ፖልቴርጋት የሲድኒ ኦሊምፒክ ትንቅንቅ ጋር አመሳስለውታል።

በ10ሺ ሜትር ለራሷም ለኢትዮጵያም የውድድሩን የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች። ባለፉት አራት ዓመታት አቅሙና ብቃቱ እያላት ማሳካት ያልቻለችውን ወርቅ በማጥለቅም ቁጭቷን ተወጥታለች።

የርቀቱ የአለም ክብረወሰን በእጇ የሚገኘው ለተሰንበት ባለፈው የአለም ቻምፒዮና እንዲሁም ኦሊምፒክ በርቀቱ ወርቁን ያጣችው በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን ነበር። ለሶስተኛ ጊዜ ይህ ታሪክ የሚደገምበት እድል ሰፊ ነበር።

ይሁን እንጂ ለተሰንበት ካለፉት ስህተቶች ተምራ የጎደላትን የአጨራረስ ችግር አስተካክላ ወደ ቻምፒዮኖቹ አለም ብቅ ብላለች። በአለም ቻምፒዮና ከርቀቱ ፈርጥ እኤአ ከ2017 ከአልማዝ አያና ወዲህ በርቀቱ ወርቅ ያጠለቀች ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አድርጓታል።

በዚህ ውድድር ከቅርብ አመታት ወዲህ እየተዳከመ የመጣው የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቡድን ስራ ትልቅ ተስፋ እንዳላት ባስመሰከረችው ወጣት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ነብስ ዘርቶ ታይቷል። እጅጋየሁ ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ባትችልም ከለተሰንበት ጋር በመናበብ ለወርቅ ሜዳሊያው መመዝገብ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥታለች።

ለተሰንበት የርቀቱ አዲሷ ቻምፒዮን የሆነችው 30:09:94 በሆነ ሰአት ነው። በርቀቱ ታሪክ እጅግ አጓጊ የአጨራረስ ፉክክር በታየበት ለተሰንበት ሲፈንንና ኬንያውያን አትሌቶችን ጥርሷን ነክሳ ድል ስታደርግ በርካቶች የውድድሩን አጨራረስ ከጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴና ኬንያዊው ፖልቴርጋት የሲድኒ ኦሊምፒክ ትንቅንቅ ጋር አመሳስለውታል።

ያምሆኖ ያለፈው ቻምፒዮና አሸናፊዋ ሲፈን ያሰበችውን ማሳካት ባልቻለችበት ውድድር የ2015 የርቀቱ ቻምፒዮን ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ 30:10:02 በመግባት የብር ሜዳሊያውን ወስዳለች። ሌላኛዋ ኬንያዊት ማርጋሬት ቼሊሞ 30:10:07 በሆነ ሰአት ነሐሱን አጥልቃለች።

በቦጋለ አበበ

አራት አትሌቶች በማራቶን ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ለማምጣት ከቀኑ 10 ፡15 ላይ ይሮጣሉ።

በ18ኛው የኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ3ኛ ቀን ውድድር ዉሎ ኢትዮጵያውያን ከሚጠበቁበት የአትሌቲክስ ውድድር ዛሬ እሁድ ከቀኑ 10፡15 የሚከናወነው ማራቶን ይገኝበታል።

በዚህ ውድድር አትሌት ሌሊሳ ደሲሳ፣ሙስነት ገረመው፣ሰይፉ ቱራ እና ታምራት ቶላ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሮጡ አትሌቶች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2014 (አሚኮ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሊቱን በተካሄዱ የወንዶችና ሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች በሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች አልፈዋል፡፡

ጉዳፍ ጸጋይ 4፡01.28 ከምድብ አንድ 1ኛ፣ ፍረወይኒ ኃይሉ 4፡02.28 ከምድብ አንድ 4ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 4፡04.05 በሆነ ጊዜ ከምድብ ሁለት 2ኛ በመሆን አልፈዋል፡፡

በወንዶች ሳሙኤል ተፈራ (3፡36.35) እና ከፈጣኑ ምድብ ታደሰ ለሚ (3፡36.24) ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሲያልፉ፥ ሳሙኤል ዘለቀ (3፡40.77) ሳያልፍ መቅረቱን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply