በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ እና ይበር ሜዳሊያዎችን በወንዶች ማራቶን አግኝታለች።

ኢትዮጵያን የወከለው ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2:05:35 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥልቋል።

ሌላው በውድድሩ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ ሙስነት ገረመው የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

በዚህም በወንዶችን ማራቶን ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያውን ጠቅልላ ወስዳለች።

ትናንት ምሽት በሴቶች 10ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ በለተሰንበት ግደይ የመጀመሪያዉን ወርቅ ማግኘቷ ይታወሳል።

እንኳን ደስ አለን‼️

Leave a Reply