“አንዳንድ መገናኛዎች አልሸባብ ለምን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ አንደገባ እያወቁ ነገሩን ሊያዞሩት ከጅለዋል” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። ቢቢሲ ኣማርኛ አልሸባብ የኢትዮጵያን ድንበር ለመሻገር የውሰነው በሶማሌ ክልል የደበቀው መሳሪያና የተጠረጠሩ አባላቱ ስለተያዙበት መሆኑንን መግለጽ ስልታዊ የሚዲያ ቅሸባ አንደሆነም እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።

ትህነግ ሰላማዊ ዜጎችን ሲወር ሚዛን የሳተ መረጃና የፕሮፓጋንዳ ጦርነት ሲያካሂድ የነበረውን ሮይተርስን ጠቅሶ አዲስ አበባ የሚቀመጠው ቢቢሲ አማርኛ ” አንድ የአልሻባብ ታጣቂዎች አዛዥ የቡድኑን ህዋስ በኢትዮጵያ ውስጥ ለማቋቋም ወደ የኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ መገደሉን ኣንድ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ገለጹ” በማለት ነው። አኚህ የልዩ ሃይል አባል በስምና በሃላፊነት በይፋ የተገለጹ ኣይደሉም።

“የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በክልሉ በኤልከሬ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ሂሎ ማዶው በተባለ መንደር ውስጥ ባካሄደው አሰሳ በጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የተለያዩ አይነት የጦር ማሳሪያዎችን አግኝቷል።የአልሻባብ አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፣ አልሻባብ የሰነዘረው ጥቃትም ከዚሁ ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አኚሁ በስም ያልተጠቀሱ የልዩ ሃይል መናገራቸውን ያትታል።

የአልሸባብ ሽንፈኛ ሃይል ድንበር ጥሶ በቀጥታ ወደ ኦሮሚያ ክልል በማምራት ከሸኔ ጋር ለመቀላቀል እቅድ እንዳለው አስቀድሞ ሆርን አፌርስ አስታውቆ ነበር። በዘገባው ትህነግ ምንም እንኳን የዲዛይኑ ባለቤት ቢሆንም ራሱን ሸሽጎ ሁለቱን በማቀናጀት የነደፈው እቅድ አስቀድሞ በመንግስት የጸጥታ መዋቅር የሚታወቅ ስለመሆኑ ያመላክታል። አሸባሪው ሃይል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አንደገባም ተከቦ የተመታው በዚህ ቅድመ መረጃ መነጻ ስለመሆኑ በተከታታይ የወጡ መረጃዎች ያመልክታሉ።

የመንግስትና የሶማሌ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮዎች በየፊናቸው አንዳሉት ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የተደመሰሰው የአልሸባብ ሃይል የተማመኑበትን ሁሉ አንገት አስደፍቷል፤ አቶ ጊታቸው ረዳ የሚባሉት የትህነግ አፈ ቀላጤ ደጋግመው አንዳሉት ኢትዮጵያ በሶማሌ ካሰማራችው አራት ሺህ ሰራዊት ውስጥ ሁለት ሺህ የሚሆኑት ከአሚሶም ፈቃድና ቁጥጥር ውጭ ራሱን ችሎ የሚሰራ መሆኑንን፣ በሰላም አስከባሪው ሃይል የማይታዘዝ እንደሆነ መስክረው ነበር። የአሚሶም ሃላፊዎችም አቶ ጌታቸው ራሱን ችሎ የሚቀሳቀስ ነው ያሉትን ሃይል ” ለዘመቻው ችግር የፈጠረና የማይታዘዝ” ሲሉ ሪፖርት አቅርበውበት አንደነበር ይታወሳል።

በዚህ ብቻ ሳይሆን ትህነግ በቀጥታ የምኪያዘው የአልሸባብ ስባሪ ሃይል አንዳለው፣ ይህንኑ ሃይል የሚያደራጁ የሚታወቁ የትህነግ ሰዎች መሆናቸው ብስም ተጠሶ፣ ከዚያም በላይ የኣውሮፓንና የአሜሪካን ካዝና ለመጎብኘትና ለማስፈራራት “ሲያሻው” ተነስ፣ ሲያሻው “ተኛ” የሚለው ሃይል አንደሆነ ሰፊ መረጃዎች አሉ። ሄርመን ኮሆንም “እንደ ትህነግ ያታለለን የለም” ሲሉ በስተመጨረሻ በገሃድ በአሚሪካ ሬዲዮ በገሃድ አንደመሰከሩበት ይታወቃል።

የሱዳን ወቅታዊ ቁመና ቅጭት የተቀየረበት ትህነግ በክረምት አንደሚያጠናቀቀው የገለሸውን ጦርነት ለምን አንዳዘገየው ደጋፊዎቹ ወጥረው በያዙበት፣ በመቀለ የተቃውሞ ሰልፎች መጀመራቸውና “መረረን” የሚሉ ድምሾች ባየሉበት፣ የትግራይ ዳያስፖራ “አንቅጩን ነገሩን” አይነት አቋም በያዘበት በኣሁኑ ሰአት ትህነግ በሶማሌ በኩል ያስነሳው አክራሪ ሃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከበረሃው አሸዋ ጋር መመሳሰሉን ምስክሮች መንግስት ይፋ ኣድርጓል። ሮይተርስ በየሰአቱ የሚጠቅሰው አልሸባብ ራሱ ሊያስተባብል በማይችለው ደረጃ ተከቦ እየተደመሰሰ ያለው አልሸባብ ከጀርባውም በሶማሌ ሃይል ኣቀባበል ተደርጎለት አንዳይሆን ተደርጎ መመታቱ ታውቋል።

ሶማሊያ ሂርሸበሌ ክልል ቶሮቶሮው በተባለ አካባቢ በነበሩ የአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ የአየር ድብደባ ተፈጸመ የቡድኑ መሪ የሆነው አቡበከር ጨምሮ ሌሎች 14 የታጣቂ ቡዱኑ አባላት እንደተገደሉ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

በተያያዘ በሶማሊያ ባይ ዞን ዶልል እና ኢዳሌ የተባሉ ቦታዎች የነበሩ ቁጥራቸው 200 የሚሆኑ የቡድኑ ታጣቂዎች የአየር ድብደባውን

በመፍራት ከሶማሊያ ዲንሶር ከተማ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ጫካማ ቦታ አካባቢ እንደሄዱ ተገልጿል።

የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በፈፀመው ወረራ የቡድኑ አባላት ላይ ያልገመቱት ጉዳት ከመድረሱ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ፈርፈር እና አፍዴር አካባቢዎች የገቡት የቡድኑ ታጣቂዎች ከሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ግንኙነታችው በመቋረጡና ታጣቂዎቹ ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባለመታወቁ ምክንያት በቡድኑ አመራሮች ደረጃ ጭንቀት ተፈጥሯል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሽህፈት ቤት የሚከተለውን ኣስፍሯል።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል

በአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ላይ እየተወሰደ የሚገኘው የተቀናጀ እርምጃ በአኩሪ ድል ታጅቦ ቀጥሏል!

ከቀናት በፊት “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ገብቶ በነበረው የአሸባሪው አልሸባብ ታጣቂ ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ አብዛኛው የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ ሸሽተው ተደብቀው የነበሩ 25 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይም እርምጃ ተወስዷል።

በደረሰበት የተቀናጀ የማጥቃት እርምጃ የተበተነው ጥቂት ሃይልም የያዘውን ከባድ መሳሪያ መጨረሱንና ባገኘበት ቦታ ለመደበቅ እየሞከረ ይገኛል። እስካሁንም የሽብር ቡድኑ ይዞት ከመጣው 4 የረጅም ርቀት መገናኛ ሬዲዮ ውስጥ ሶስቱ ተማርከዋል።

ፌርፌር በተባለው አካባቢ በኩል ገብቶ ከነበረው የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ውስጥም በ85ቱ ላይ እርምጃ ተወስዶ ሸሽተው ወደመጡበት ሲመለሱ በነበሩትም ላይ የጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ፌደራል ሃይል የማያዳግም እርምጃ ወስዶባቸዋል።

እስካሁንም ድንበር ጥሶ ከገባው ታጣቂ ሃይል ውስጥ ከ209 በላይ የሚሆኑት በክልሉና በፌደራል የጸጥታ ሃይሉ የተቀናጀ እርምጃ መደምሰሳቸው ታውቋል። በክልሉ ህዝብና ሚሊሻ እርምጃ የተወሰደበትና የተማረከውን የሽብር ቡድኑ አባላት ትክክለኛ ቁጥርም እየተጣራ ይገኛል።

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በሶማሌ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረው የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በክልሉ ልዩ ሃይል አኩሪ ተጋድሎና በፌደራል የጸጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥረት ከፍተኛ የሰው ሃይልና የንብረት ኪሳራ ደርሶበታል።

ይህ የሽብር ቡድን በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ከሌላኛው የሽብር ቡድን ከሸኔ ጋር ለመገናኘት አልሞ የነበረ ቢሆንም ይህ እቅዱ ሙሉ በሙሉ መክሸፉ ተረጋግጧል።

በተቀናጀው የመልሶ ማጥቃት የተበታተነውና ተቆርጦ የቀረውን የሽብር ቡድኑ ሃይል ላይ የሚወሰደው የማጽዳት ተልእኮ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ይቀጥላል።

የሽብር ቡድኑ ይዞት የመጣውን የሽብር ተልእኮ ሙሉ በሙሉ በማክሸፍና አሁንም ገብቶባቸው ከነበሩት አካባቢዎች በማጽዳቱ ሂደት ከጸጥታ ሃይሉ ባሻገር የአካባቢው ህዝብ አስተዋጽኦና መስዋእትነት ከፍተኛ የነበረ ሲሆን ይህ ቡድን ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ እስኪጠናቀቅም ህዝቡ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Leave a Reply