አልሻባብ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰነው የሶማሊያዋ የድንበር ከተማ ጥቃት ሰንዝሮ ያሰበውን ሳያሳካ መደምሰሱን አስታወቀ። ነዋሪዎች በበኩላቸው አልሸባብ በስፍራው ካሉ የጸጥታ ሃይሎች ጋር መዋጋት እንዳልቻሉና የተማረኩ እንዳሉ አመልክተዋል። መከላከያ ከ150 በላይ የአሸባሪው ሃይሎች መደምሰሳቸውን ይፋ አድርጓል።

አልሻባብ ከአንድ ሳምንት በፊት በዚህችው የድንበር ከተማ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ጋር መዋጋቱና ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን መንግስትና ክልሉ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ቢቢሲ የዛሬውን ዜና ገልብጦ አቅርቧል። አልሸባብ ጥቃት መፈጸሙን ጠቅሶ ከዜናው ግርጌ መደምሰሱን አንድ ባለስልጣን እንደነገሩት አመልክቷል።

ይህ በግብጽና በትህነግ የሚመራ ቡድኑ ዛሬ አርብ ጠዋት ለኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው አቶ ላይ በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት የሰነዘረው የኢትዮጵያ አየር ሃይል በስንቅና ትጥቅ ማከማቻው ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ካወደመ በሁዋላ የተረፈው ሃይል ተሰባስቦ ነው። ምስክሮች እንዳሉት ቡድኑ ሲደመሰስ በርካታ መሳሪያና ንብረት ጥለው የፈረጠጡትን የኢትዮጵያ አየር ሃይል እየለቀማቸው እንደሆነ አመልክተዋል።

ዛሬ ወደ አቶ ዘልቆ ጥቃት የመፈጸም ዓላማ የነበረው የአልሻባብ ታጣቂ ኃይል፤ ያሰበው ሳይሳካ ሽንፈት እንዳጋጠመው ያመለከተው መከላከያ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮቹ መገደላቸውን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሽብር ቡድኑንን እግር በግር እየተከታተል እየደመሰሰ መሆኑንን ያመለከተው የመከላከያ መግለጫ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ማናቸውም ሃይሎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መከላከያ ዝግጁ መሆኑንን አመልክቷል።

Leave a Reply