አልሸባብ በታሪኩ በየትኛውም አካል ይህን መሰል ጥቃትና ኪሳራ ገጥሞት አይውቅም። የውጊያው አውድና የኦፕሬሽኑ መሃንዲሶች እንዳሉት አልሸባብ ይህን ያህል ሃይልም አሰልፎ አያውቅም። በውክልናና በቅጥረኛነት ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከተነሱ የንግዴ ልጆች ጋር መክሮ ሊያጠቃ የመጣው የአልሸባብ ሃይል እንዳይሆን ሆኖ የበረሃ አሸዋ ውስጥ የተቀበረው በኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች መሆኑ ለጥፋት ሃይሎች ሁሉ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

ከትህግ ጋር ግንኙነት እንዳለው ማስረጃ የሚቀርብለት ይህ አልሸባብ በዚህ ደረጃ ይመታል፣ የደመሰሳልና ይማረካል ብለው ያልገመቱ ወዳጆቹ እሱን በሶማሌ ክልል አስርገው በቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል ከሌላው የጥፋት ሃይላቸው ሸኔ ጋር በማበር ጥቃት ለመሰንዘር ዕቅድ እንደነበራቸው መንግስት ሙሉ መረጃ እንደነበረው ማስታወቁ አይዘነጋም። ይህ “የትህነግት ሌላው የንግድ ተቋም ወይም ኤፈርት” የሚባል አሸባሪ ሃይል ዳግም ኢትዮጵያ ክልል ለመግባት እንዳያስብ ሆኖ መመታቱን የሶማሌ ክልል መሪ አቶ ሙስጣፌ ዛሬ ረፋዱ ላይ አስታውቀው ነበር።


አልሸባብ የትህነግ – ሌላው ኤፈርት

የፔንታጎን ሽብርተኛን በስውር የመርዳት ታሪክ
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ መሰል ታጣቂዎችን እንደ ጫና ካርድ  መጠቀም አለም የሚያውቀው ነው። ህወሃት በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የሽብር ድርጅት ዝርዝር ውስጥ third tier terrorist ድርጅት ተብሎ የተቀመጠ ነው። ይህን አሸባሪነቱን እንደመዘገበች ነበር አሜሪካ ደርግን ለመጣልና ህወሃት ተላላኪ መንግስት ይሆንላት ዘንድ የፈቀደችው። አሜሪካ ከህወሃት በተጨማሪ አልሸባብን ቦኮ ሀራምን እንዲሁም በሶሪያ አልቃኢዳን አጋሯ አድርጋለች። ይህ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጠ ሀቅ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት ባራክ ኦባማ የሶሪያ አልቃይዳ በሺር አልአሳድን ለመጣል የሚታገል ለዘብተኛ አማፂ moderate rebels ናቸው” ሲሉ ነው ቃሉን ለወጥ አርገው ያመኑት።  How Boko Haram Become a Silver Lining for


ሙስጣፌ ይህ ኦፕሬሽን መክሸፉን ተከትሎ በጎጃም ውስን ሃብታሞች የሚረዱና ከትህነግ ጋር ግንኙነት ባላቸው “የስም አማራ” ነን ባዮች የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲፋፋምባቸው መክረሙን የሚጠቁሙ “ድሉ ለህዝብና ለቀና ዜጎች ብዙ ትርጉም አለው” ብለዋል።

ከስር የተማረከውን ተዋጊና ከባድ መሳሪያ እንዲሁም ዝመናዊ አሜሪካ ሰራሽ መገናኛዎች ይመልክተቱ

የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ ሃያ አራት ሲፈለጉ የነበሩ የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ የቡድኑ ተዋጊዎች መደምሰሳቸው ሲገለጽ በዋናናት የተነሳው የሶማሌ ክልል ሕዝብ ከጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር ስምምነት እንደሌለውና ጸረ ሕዝብ ሃይሎችን መሸከም እንደማይችል ነው። የአገር መከላከያና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አዛዦች ለሶማሌ ሕዝብ ክብርና አድናቆትን ችረዋል።

ኢዜአ ሃያልፊዎችሁን ጠቅሶ ዘግይቶ ዜናውን ከማሰራጨቱ በፊት ኢትዮ 12 የኢትዮጵያን አየር ህያል ሚና በመጥቀስ በክልሉ ፕሬዚዳንት መረጃ ላይ በመንተራስ ዜና አቅርባ ነበር። ዜናው ብ እንዳረጋገጠው የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ እስካሁን ባለው ሂደት ሃያ አራት የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ የሽብር ቡድኑ ተዋጊዎች መደምሰሳቸውን ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡ ድሽቃን ጨምሮ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና የጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል መሃመድ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ከሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት ያደረገው ሙከራ በፀጥታ ኃይሉና በሕዝቡ የተቀናጀ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።

ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሹ የውጭ ጠላቶች የውስጥ ባንዳዎችን በመቅጠር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ እቅዳቸው እንዳሰቡት አልሳካ ሲላቸው በአሁኑ ወቅት አልሸባብን ከኋላ በመደገፍ ከንቱ ሙከራ ማድረጋቸውንም ነው ያብራሩት፡፡ ይህም ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋዎችን ተጠቅማ ለመልማት የጀመረችውን ተስፋ ሰጪ ሥራ ለማደናቀፍ ያለመ ሙከራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም አልሸባብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተወሰነ ኃይሉን በ16 ተሽከርካሪዎች በመጫንና የተወሰነውን ደግሞ ጨለማን ተገን አድርጎ በእግር ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ በማስገባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሩን ነው የገለጹት፡፡

ነገር ግን የመከላከያ ሰራዊቱ ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ጋር በመቀናጀት በወሰደው እርምጃ ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ የሽብር ቡድኑ አመራሮችን ጨምሮ ተዋጊዎቹ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል ነው ያሉት፡፡

የኢፌዲሪ አየር ኃይል የተመረጡ ኢላማዎችን ነጥሎ በመምታት የሽብር ቡድኑ ለረዥም ጊዜ እጠቀምበታለሁ ብሎ ያዘጋጀውን የሎጂስቲክስና ጦር መሳሪያ ክምችት ያወደመ ሲሆን፤ የሽብር ቡድኑን አመራሮችም መደምሰስ ችሏል፡፡

በዚህም የሚከተሉት የሽብር ቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸው ተገልጿል:-

1) ፉአድ መሐመድ ከሊፍ -የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊ

2) አብዱልአዚዝ አቡሙስ -የአልሸባብ ቃል አቀባይ

3) አብዲኑር ኢሴ -የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበር አዋሳኝ ኃላፊ

4) ሸክ ለአብ ሶማሊያዊ -የደቡብ ምስራቅ ሎጂስቲክ ኃላፊ

5) አቡ ሙሳ – ምክትል አፈጉባኤ

6) አሊ መሃመድ ሃሰን – የአልሸባብ ማዕከላዊ ኮሚቴ አማኒያት ሁለተኛ ሰው

7) አደም -ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የሽብር ቡድኑ ምክትል አዛዥ

) ሙክታር ጋብ – ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል

9) አሚር አብደላ (መሃመድ አብዱላሂ) – ሞርጋቤ ካምፕ የአልሸባብ ስልጠና ኃላፊ

10) ኢንጂነር ጀሃድ ስሬዋን (ሙጃሂድ ፈይሰል) – በብሉፍላይ ካምፕ የማሠልጠኛ ኃላፊና የፈንጅ ኃላፊ

11) ሼክ ሁሴን በርደሌ – የባይና ቦከል ዞን ቀረጥ ሰብሳቢ

12) ሼክ ሃሰን ኑኖ -የታችኛው ሸበሌ ጀበሃ ዘመቻ ኃላፊ

13) ያሲን ደሬ – አሚር

14) ሳላህ ደሬ – የባይ ዞን የአልሸባብ ትምህርት ኃላፊ

15) አቡሠላም – የቦኮል ዞን የአልሸባብ ሰብሳቢ

16) ሃምዚ አቡዱላሂ – የባይ ዞን መረጃ ኃላፊ

17) አብዱላሂ ሃጅ – የባይና ቦኮል ዞን ወታደራዊ አዛዥ

18) ሙክታር ቦሮ – አሚር

19) አብዱረሽድ ጋቦ- አሚር

20) አብዱኪም ገዱደ- አሚር

21) ሙክታር ጋብ – የቀጣና ዘመቻ ኃላፊ

22) አዩብ ዳውድ – አሚር

23) አሊ አደን—አሚር

24) ሃሰን መሃመድ–አሚር ናቸው።

እንደ ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ ገለጻ፤ የጸጥታ ኃይሉ ያከናወነው ኦፕሬሽን የመከላከያ ሠራዊት፣ የአየር ኃይል እንዲሁም የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይልና ሕዝብ ጀግነነትን በተግባር ያረጋገጠና ኢትዮጵያን ለመድፈር የሚሞክሩ ኃይሎች ደጋግመው ማሰብ እንዳለባቸው ትምህርት የሰጠ ነው፡፡

የክልሉ ነዋሪዎች የጸጥታ ኃይሉን ደጀን ሆነው በመደገፍ ረገድ አኩሪ ተግባር ማከናወናቸውንም አብራርተዋል፡፡አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ በውስጥ ያዘጋጃቸው ሴሎችን የማጥራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል መሐመድ አህመድ የሽብር ቡድኑ አቶ፣ የድ፣ ኤልበርዴና ወሻ በተባሉ የጠረፍ አካባቢዎች ጥቃት ለመፈጸም መሞከሩን ተናግረዋል።

በወቅቱ የመከላከያ ሰራዊቱና ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በጀግንነት በመዋጋት የኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል ነው ያሉት፡፡ በዚህም የአልሸባብ 24 ቁንጮ አመራሮችን ጨምሮ 813 የሽብር ቡድኑ ተዋጊዎች መደምሰሳቸውን ጠቅሰው፤ አልሸባብ በዚህን ያህል ቁጥር በአንድ ጊዜ ኮር አመራሮቹ ሲገደሉበት ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ሊሆን እንደሚችልም ነው የጠቆሙት፡፡

የሽብር ቡድኑ ተዋጊዎቹን ወደ ኢትዮጵያ አስርጎ ለማስገባት የተጠቀመባቸው ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎች መውደማቸውንም ተናግረዋል፡፡ ድሽቃን ጨምሮ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም እንዲሁ፡፡

አጠቃላይ በኦፕሬሽኑ የሶማሌ ክልል ሕዝቦች የየትኛውም የጥፋት ቡድን ተባባሪ አለመሆናቸውን በተግባር ያሳዩበትና የጸጥታ ኃይሉም አገሩን ለመጠበቅ ሁሌም ዝግጁ መሆኑ በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑንም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የምርኮኞች አያያዝን የተከተለና ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤ እያደረገልን ነው– “የተማረኩ የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት” ENA

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የምርኮኞች አያያዝን የተከተለና ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤ እያደረገላቸው መሆኑን “የተማረኩ የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት” ተናገሩ።

በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይሎች ተደምስሷል።

የሽብር ቡድኑ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በሶማሌ ክልል ጸጥታ ኃይል በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ምርኮኞች መካከል ከዘጠኝ ወር በፊት ቡድኑን የተቀላቀለው አብዱላሂ ሀሰን አብዲ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ተልዕኮ በመቀበል ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ ወቅት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል።

በኮህሌ ወረዳ ሕዝብ ውስጥ ሰርጎ ገብቶ የተያዘው አብዱላሂ ጀማል ሮብሌ እና ቡድኑን ከአምስት ዓመታት በፊት የተቀላቀለው አያልኔ መሐመድ አህመድ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ እጅ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሽብር ተልዕኮ ይዘው ቢመጡም ባልጠበቁት መልኩ ቢማረኩም የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የምርኮኛ አያያዝን በተከተለ አግባብ እንክብካቤ እያደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋልን በፀጥታ ኃይሉ እንገደላለን የሚል ስጋት እንደነበራቸው ጠቅሰው፤የጠበቃቸው ግን በተቃራኒው ፍጹም ርህራሄ የተሞላበት የምርኮኛ አያያዝ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለቀናት በረሃብና በውሃ ጥም ቢቆዩም የኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይሎች የተራቡትን አብልቶ፣የታረዙትን አልብሶና የታመሙትን እያሳከመ፣ የንጽህና ግብዓቶችን እያሟላ በጥሩ እንክብካቤ እንደያዛቸው ነው ያረጋገጡት።

በጸጥታ ኃይሉ ሥር በመሆናቸውም ምንም አይነት ስጋት እንደሌላቸው ነው የተናገሩት።

የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና የጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል መሃመድ አህመድ ምርኮኞችን በአግባቡ መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

የአሸባሪው ቡድን አባላት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሰርገው ቢገቡም የኢትዮጵያ መከላከያና የክልሉ ልዩ ኃይል ወታደራዊ ዲሲፕሊን ያላቸው በመሆኑ ዓለም አቀፍ ምርኮኛ አያያዝን ደንብን በጠበቀ አግባብ እንደተያዙ ገልጸዋል።

በዚህም በጸጥታ ኃይሉ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ከ100 በላይ ምርኮኞች ሰብዓዊነት በተሞላበት አግባብ እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል።

Leave a Reply