የፔንታጎን ሽብርተኛን በስውር የመርዳት ታሪክ
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ መሰል ታጣቂዎችን እንደ ጫና ካርድ  መጠቀም አለም የሚያውቀው ነው። ህወሃት በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የሽብር ድርጅት ዝርዝር ውስጥ third tier terrorist ድርጅት ተብሎ የተቀመጠ ነው። ይህን አሸባሪነቱን እንደመዘገበች ነበር አሜሪካ ደርግን ለመጣልና ህወሃት ተላላኪ መንግስት ይሆንላት ዘንድ የፈቀደችው። አሜሪካ ከህወሃት በተጨማሪ አልሸባብን ቦኮ ሀራምን እንዲሁም በሶሪያ አልቃኢዳን አጋሯ አድርጋለች። ይህ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጠ ሀቅ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት ባራክ ኦባማ የሶሪያ አልቃይዳ በሺር አልአሳድን ለመጣል የሚታገል ለዘብተኛ አማፂ moderate rebels ናቸው” ሲሉ ነው ቃሉን ለወጥ አርገው ያመኑት።  How Boko Haram Become a Silver Lining for

ሽብር እስከመቃብር

አልሸባብ አንደ ኤፈርት ሁሉ  የትህነግ ዋነኛ የቢዝነስ ድርጅቱ  ነው። “እንዴት ሆኖ?” ይህንኑ እውነታ በማስረጃና መረጃ ማሳየት ይቻላል። “የአፍሪካን ቀንድ አደጋ ላይ የሚጥሉ የጸጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ መደበኛ የውይይት መድረኮች ላይ ከህወሓት ጋር ይሰሩ በነበሩ ሰዎች እንዲመራ ማድረግ አደገኛ ነው። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህጋዊውን የኢትዮጵያ መንግስት ለማፍረስ ሲታገል ከታወቁ የአሸባሪ አካላት ጋር የስራ ግንኙነት እንዳለው ስለሚታወቅ ከነሱ ጋር መስራት በሶማሊያና በአጠቃላይ ቀጣናው ላይ አደጋ ነው” ሲሉ የሶማሊያ የድህንነት ሹም በይፋ መናገራቸው አንዱ ማሳያ ነው።

አልሸባብን የደመሰሰው ሰሞነኛ ጥጋቡ

የሶማሊያው የቀድሞ ደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ፋአድ ያሲን ስለ አልሸባብ ሰሞንኛ ጥቃት የሰጠው መግለጫ ምን ይላል? ሰውዬው አልሸባብን ብቻ ሳይሆን ለአልሸባብ ጉልበት የሚያውሱትንም ለአመታት ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም ይመስላል “የሶማሊያ መንግስታዊ መዋቅር ንቅዘተ-ትህነግ ገጥሞታል” ሲል የደመደመው።

ትህነግ በቪላ ሶማሊያ ሳሎን ላይ አንደ ዘንዶ ተጠምጥማ ስትከውነውና አየከወነችው ያለው ሴራ ለሀሰን ሼክ ሞሀሙድ መንግስትም ሆነ ለቀጣናው የሽብር እርሾ የመሆኗ ምስክር ነው። “ሰሞኑን አልሸባብ በሶማሊ ክልል የሰነዘረው ጥቃት ከትህነግና ሌሎች የትህነግ ጋላቢዎች ፈቃድ የተፈፀመ ነው”  ይላል የደህንነት ሹሙ መረጃ። ቀደም ሲል ጀመሮ በአፈጣጠር አንድ አምሳል የሆኑትና ተናበው ሲንቀሳቀሱ የኖሩት እኒህ አሸባሪዎች፣ ዛሬ ላይ “ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር” ተብሎ በተገለሸ ኦፕሬሽን አመድ የሆኑበትን ጥቃት ለመሰንዘር የተነሱት ወቅቱን አስልተው ነው።

በኢትዮጵያ ሰሜንና ሰሜን ምእራብ አቅጣጫ የምእራባዊያን የጫና በሮች መዘጋታቸው ትህነግና አልሸባብ በሽብር ቀጠሮ እንዲገናኙ ጥርጊያ የከፈተ ሰሞነኛ ተጨባጭ ነው። የሙስጠፌ ልዩ ፖሊስ አባላት በአጭር የቀጩት የሽብር ፕሮጀክት ለሶስተኛ ወገን የውጭ ሀገራት የጫና deterrence ተልእኮ ያነገበም አንደነበር ማንም ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል።

አሜሪካ፡ የወታደራዊ ጫና ፖሊሲ

የዘርፉ ጠበብት እንደሚገልፁት ከአሜሪካ አራት የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ስትራቴጂክ ምሰሶዎች መካከል የመከላከያ ዲፕሎማሲ አንዱ ነው። ይህ ስትራቴጂ በወታደራዊና የደህንነት ጡንቻ ብርቱ ጫና የማሳደር deterrence መሆኑ ነው። ይህ ዘዴ ፋታ በማይሰጥ የዲፕሎማሲ አካሄድ እና ወታደራዊ ዲፕሎማሲን እያቀላቀለ ይተገበራል። ለስትራቴጂክ ጥቅማቸው ወሳኝ ሀገራት ውስጥ የሚፈጠሩ የቀውስ ክፍተቶች ሳያመልጧቸው ለጥቅማቸው የማዋል በደም የተፃፈ ፖሊሲ ነው። ከላይ የተጠቀሱት አሜሪካ በውጭ ሀገራት የጣልቃገብነት እና የጫና ስልቶች በአብዛኛው ግራጫ ጦርነት Hybrid war በተባለው ቀጥተኛ ያልሆነ የወታደራዊ ተሳትፎ አይነት የሚገለፅ ነው። ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት ያስተናገደችውም ይህንኑ አሜሪካ መራሽ ዘመቻ ነበር።

ግራጫ ጦርነት – Hybrid War

ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ ከሁለኛው የአለም ጦርነት ወዲህ በስፋህ እንጀመሩት የሚነገርለት ቀጥተኛውን ወታደራዊ ተሳትፎ  መንግስታትን ከማስወገድ ይልቅ “ግራጫ” ጦርነት ወጪ እና ተጠያቂነትን በመቀነስ አዋጪ ሆኖላቸዋል። በዚህ  የጦርነት አይነት የውክልና ጦርነት፣ ዲፕሎማሲያዊ ጫና፣ በምርጫ ጣልቃ መግባት፣ የሀሰት ዜና ማሰራጨት የመሳሰሉት ስልቶች ይጠቀሳሉ። በነዚህ መንገዶች “ጠላታችን ነው” ያሉት አገር የማይንበረከክ ከሆነ፣ በቀጥታ ጦር ሊያዘምቱ ይችላል። ግራጫ ጦርነት በሶስት ዋና ዋና ስልቶችን ማለትም Divide, Demoralize እና Distract በሚሉ 3D ገፅታዎች ይተገበራል።

1. Divide; ማህበረሰብን በብሄር በሃይማኖት በቋንቋ ወዘተ… በተቻለ መጠን መከፋፈፈልና በአንድነት በርትቶ እንዳይቆም የሚደረጉ ዘመቻዎችን ይይዛል።

2. Demoralize; የሽንፈት ስነልቦና ለመፍጠር ታላሚው ጦር እየተሸነፈ፣ እየከዳ ተስፋ እየቆረጠ ወዘተ በማለት ኢ-ሞራላዊ ተግባራትን ያካተተ ሲሆን የማህበረሰቡን የሞራል ልዕልና መሸርሸርና ማላሸቅ ዋነኛ ግቡ ነው፡፡

3. Distract ማህበረሰቡ ተረጋግቶ እንዳያስብ የውሸት ትርክቶችን ያለመታከት በመንዛት ከዋናው አጀንዳው ውጪ እንዲባዝንና ሃሳብን ብትንትን ማድረግ የሚሉት ናቸው።

የኢትዮጵያ የቅርብ ወራት ተሞክሮ፣ ምን ያልተፈጸመ ነገር አለ?

ህወሃት በሰሜን እዝ ላይ የተጠና የክህደት ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ዋሽንግተን በቅሽበት የገለፀችው አቋሟ የመደበኛው የትብብር ፖሊሲ መገለጫ ነበር። ይኸው አቋም ይፋ የሆነው መሰል የፀጥታ ስጋቶችንና ሉአላዊነትን የሚዳፈር ወንጀል ኢትዮጵያ የህግ የማስከበር ርምጃ መውሰዷን የሚደግፈው በማይክ ፖምፒዮ መግለጫ ነበር። ህወሃት በሶስት ሳምንታት ውስጥ ተሸንፎ ሰራዊቱ መቀሌ ለመቆጣጠር በዙሪያዋ ከበባ ሲጀምር ግን ዋሽምግተን የጫና ካርዷን መዘዘች።

መደበኛውን የዲፕሎማሲ አካሄድ በማፍረስ የረጂም ጊዜ አጋር በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ወደማሳደር ተሻገረች። ትህነግ የሰራውን ሀገራዊ ቁስሉ በመጎርጎር ለመጠቀም ቆርጣ ተነሳች። ህወሃትን በመሳሪያ፣ በደህንነትና በወታደራዊ የሳተላይት መረጃ ድጋፍ አይዞህ ትለው ጀመረች። የአውሮፓ አጋሮቿን አስከትሏ ፀረ ኢትዮጵያ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፈተች። ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የዲፕሎማሲ መድረክ ትነጠል ዘንድ ሌሎች ሀገራትንም መጫን ቀጠለች። በኢኮኖሚ የጫና ካርዷ ብድሯን ማገድና እንደ አጎዋ ካሉት ትብብሮች ኢትዮጵያን አገደች። በሌላ በኩል አጋጣሚውን ለትርፍ ለማዋል እንደ ኢቲዮ ቴሌኮም ባሉ ተቋማት ጨረታ የአዛዥነት ሚና ለመጫወት ሞከረች፤ ሰብአዊ መብት ተረገጠ፤ ርዳታ ያለፍተሻ ከነ ጉዳጉዱ ይግባ ወዘተ የሚሉ ቅጥ ኣንባሩ የጠፋ የጫና ካርዶችን መዘዘች። 

በወታደራዊው የጫና ካርዷ Gunboat ዲፕሎማሲ በሚሉት ስልት ጂቡቲ ያለው ጦር ሰፈሯንና የጦር መርከቦቿ ሲያንዣብቡ በምእራባዊ ሚዲያዎች በማሳየት ስነልቦናዊ ጫና ተጠቀመችበት። ከዚሁ ጎን ለጎን የህዳሴ ግድቡን ድርድር፣ የኢቲዮ ሱዳን የድንበር ግጭትን እንዲሁም ህወሃት የባህር በር ይሰጠው የሚል ጫና አከታተለች።

ኢትዮጵያ ያስተናገደቻቸውን የግራጭ ጦርነት Hybrid war መልኮች በተከታዮቹ ማሳያነት ማስቀመጥም ይቻላል፡፡

–  ጦርነቱን ያለቀለትና ያበቃለት፣ ወይም ወራሪው ሃይል ከድል ዋዜማ ላይ መቃበረቡ ይኸውም ሊበሰር ቀናት የቀሩት የማስመሰል ፕሮፓጋንዳዎች

–  ጦርነቱ በድል ሊቋጭ ከጫፍ የደረሰ በማስመሰል ተተኪ መሪዎችን የማጨትና መሰል የወደፊት አጀንዳዎች ላይ ማውራትና መምከር

–  የሉአላዊ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚወስደውን ርምጃ ዘር ማጥፋት አስገድዶ መድፈር የሰብአዊ መብት ረገጣ ወዘተ እንደሆነ አስመስሎ በአለም አቀፍ ሚዲያዎቻቸው ሌት ተቀን መለፈፍ

–  በወራሪ ሃይል የተያዙትን ሆነ ያልተያዙ ከተሞችና አካባቢዎችን በፎቶና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ደጋግሞ

 በማስተጋባት የፍርሃትና ሽብር ስሜት መፍጠር

–  ለሉአላዊው ሰራዊት ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታት ላይ የዲፕሎማሲ ጫና ማሳረፍ። በዚህም መንግስትን ከአለም ለመነጠልና ተስፋ ለማስቆረጥ መስራት

–  የሀገሪቱ መሪ እንዲሁም ከፍተኛ ባለስለጣናት ከሀገር እንዲወጡ መወትወት፣ ማግባባት፣ መደለል እንዲሁም ሊሰደዱ በዝግጅት ላይ ናቸው የሚሉ  መረጃዎችን እየፈጠሩ መንዛት

–  የሶማሊያው የደህንነት ዋና ዳይሬክተር መግለጫ

የሶማሊያው የደህንነት አለቃ “አልሸባብ የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የፈፀመውን

ጥቃት እንዲህ በቀላሉ መመልከት አይገባም።” ሲል የተናገረውም ቡድኑ እየተጋለበ የመምጣቱን እውነታ በማገናዘብ ነበር። ፋሃድ ያሲን በሶማሌ-ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በሰጡት መግለጫቸው በሶማሊያና በአፍሪካ ቀንድ እንደ አጠቃላይ የሚስተዋሉ የብሄራዊ ደህንነት ፈተናዎችን እንዴት በብቃት መቋቋም እንደሚቻልም ባለ 5 ነጥብ ምክረ ሀሳባቸውንም አካፍለዋል። “ህወሀት በሶማሊያ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ ገብቷልና አደጋ ላይ ነን” ይላል። ስለሆነም ብሔራዊ አመራሩ ለሶማሊያ ደህንነትና ለመላው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላም የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ ያደርግ ዘንድ እመክራለሁ ብለዋል፦

1. የሶማሊያ መንግስት አልሸባብን ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።

2. በጉጉት የሚጠበቀውን የሶማሊያ ካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት በአስቸኳይ መስጠት፣

3. የሶማሊያ ብሔራዊ የደኅንነት ኮሚቴ ጠንካራ መመሪያዎች ለማስተላለፍ የሚያስችል አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት።

4. የአፍሪካ ቀንድን አደጋ ላይ የሚጥሉ የጸጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ መደበኛ የውይይት መድረኮች ላይ ከህወሓት ጋር ይሰሩ በነበሩ ሰዎች እንዲመራ ማድረግ አደገኛ ነው። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህጋዊውን የኢትዮጵያ መንግስት ሲታገል፣ አንዳንዶች ደግሞ ከታወቁ አሸባሪ አካላት ጋር የስራ ግንኙነት እያላቸው ከነሱ ጋር መስራት በሶማሊያና በአጠቃላይ ቀጣናው ላይ አደጋ ነው!

5. ኢትዮጵያ ረዥሙን የመሬት ድንበር የምንጋራት ሀገር በመሆኗ በደኅንነትና ሽብርተኝነትን በመዋጋቱ ረገድ የሁለትዮሽ ትብብር ወሳኝ ስትራቴጂ መሆን አለበት። ሽብርተኝነትን ከሚያራምዱ አካላት ጋር ያለን ግንኙነት በእኛ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲያሳድር መፍቀድ አይገባም።

የፔንታጎን ሽብርተኛን በስውር የመርዳት ታሪክ

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ መሰል ታጣቂዎችን እንደ ጫና ካርድ  መጠቀም አለም የሚያውቀው ነው። ህወሃት በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የሽብር ድርጅት ዝርዝር ውስጥ third tier terrorist ድርጅት ተብሎ የተቀመጠ ነው። ይህን አሸባሪነቱን እንደመዘገበች ነበር አሜሪካ ደርግን ለመጣልና ህወሃት ተላላኪ መንግስት ይሆንላት ዘንድ የፈቀደችው። አሜሪካ ከህወሃት በተጨማሪ አልሸባብን ቦኮ ሀራምን እንዲሁም በሶሪያ አልቃኢዳን አጋሯ አድርጋለች። ይህ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጠ ሀቅ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት ባራክ ኦባማ የሶሪያ አልቃይዳ በሺር አልአሳድን ለመጣል የሚታገል ለዘብተኛ አማፂ moderate rebels ናቸው” ሲሉ ነው ቃሉን ለወጥ አርገው ያመኑት።  How Boko Haram Become a Silver Lining for

Emperialism in Africa” በሚል የተሰናዳ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ ሌላው ማጠናከሪያ ነው። በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር የምእራባዊያን ኢምፔሪያሊዝም በናይጀሪያ እግሩን ለመትከል የበረከት ያህል ነበር የሆነለት።

ኔቶ ሊቢያ ላይ ያደረሰው ጥቃት ተከትሎ ፈረንሣይ እና አሜሪካ በማሊ እና ኒጀር ይዞታቸውን አስፋፉ። ይህም ከሰሃራ በታች ያለውን ትርምስ ወለደ።” በወታደራዊ ደረጃ አፍሪካ በፍጥነት የአሜሪካ አህጉር እየሆነች ነው። የሰሜን አፍሪካ ታጣቂዎች፣ በአሜሪካ ቦምቦች፣ መሳሪያዎችና ገንዘብ የተደገፉት እንደ ናይጄሪያው ቦኮ ሃራም ያሉትን ጨምሮ አሰልጥነዋል፤ አስታጥቀዋል።

ይህን ተከትሎም 300 የናይጄሪያ ልጃገረዶች ሲታገቱ አሜሪካ “ሰብአዊ” ጣልቃገብነት በሚባለው ዘዴዋ እጇን ለማስገባት የወሰደባት ከወር ያነሰ ጊዜ ብቻ ነበር። የሚገርመው አሜሪካ መራሹ AFRICOM ከናይጄሪያ ወታደራዊ ሃይል ጋር የነበረው ልዩ ግንኙነት በሚስጥር ቆይቶ save our girls በሚል አለማቀፍ ዘመቻ ሲጀመር ግን ነገሮች ይገላለጡ መጀመራቸው ነው።

ከዚህ ወቅት ጀምሮ AFRICOM የናይጄሪያውን ሬንጀርስ ሻለቃ የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ሲያሠለጥን እንደቆዬ በድንገት ይፋ ሆነ። በመጨረሻም ኒውዮርክ ታይምስ ሳይቀር የአሜሪካ ጦር ከናይጄሪያ ሴቶች መታገት በፊት ባሉ አመታት ጀምሮ ሚስጥራዊ ወታደራዊ ስልጠናና ዘመቻ ሲያደርግ እንደነበረ ይፋ አደረገ።

አሜሪካ አልሸባብን በአሸባሪነት ፈርጃ በአንድ በኩል ቡድኑን በተለያዩ ክንፎች እየመደበች በትጥቅ ስንቅና ስልጠና ስትደግፍ እንደነበር እንዲሁ ፀኃይ የሞቀው ሀቅ ነው። ለአብነትም የአሜሪካው ፔንታጎን የቀጠረውና ብላክዋተር የተሰኘው ወታደራዊ ተቋራጭ የሶማሊያ ሚሊሻዎችን በድብቅ መደገፉ ከ2011 ወዲህ ይፋ ሲደረግ ቆይቷል። ይህ ብላክ ወተር የተባለው ወታደራዊ ተቋራጭ በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ታጣቂዎችን በደገፈበት ታሪኩ በተመሳሳይ ነው በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ የተሳተፈው። Mint Press Institute ይፋ ባደረገው

ሪፖርቱ ውስጥ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቀድሞ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣን “የባህር ላይ ወንበዴዎችን ለመዋጋት ከሚለው አላማ በተጨማሪ በፑንትላንድ ይገኝ ለነበረው የሶማሊያ አደገኛ የሽብር ቡድን ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በብላክ ወተር በኩል ከአሜሪካው ፔንታጎን ቀርቦላቸዋል።” ማለታቸውን አስነብቧል። “በአውሮፓ ህብረት የሚሰለጥኑ የሶማሊያ ታጣቂዎች በወር 100 ዶላር ያገኛሉ፤ ከአሜሪካው ወታደራዊ ተቋራጭ ግን በወር 300 ዶላር በስልጠና ወቅት እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ በወር 500 ዶላር እንደሚቆረጥላቸው ለሚንት ፕሬሥ የተናገሩት ስማቸውን መግለፅ  የአሜሪካ ያልፈለጉ ሌላ የአሜሪካ መንግሰት ባለስልጣን ናቸው።

አሜሪካ በቅርቡ በሶማሊያ ካደረገቻቸው ስውር ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች፣

የአሜሪካ ልዩ ዘብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለመግባት በሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም አመሻሹን የአሜሪካ ደህንነተ መረጃ ቋት አሳውቋል። በወቅቱ የኒውዮርክ ልዩ ብሄራዊ ዘብ አባላት የሆኑ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሊሰፍሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቁጥራቸው አንድ ሺህ ከሚሆኑት አባላቱ መካከል፣ የተመረጡ ወታደሮች የሚሰፍሩት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኬኒያ ውስጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡ አሜሪካ ከአስራ ሁለት አመታት በፊት

የአፍሪካ ቀንድን ለመቆጣጠር በሚል ጅቡቲ ውስጥ ያቋቋማቸው የሌሞኔር ካምፕ አንዱ የወታደሮቹ መስፈሪያ ሲሆን፤ በኬኒያና ሶማሊያ ግን የት ቦታ እንደሚሰፍሩ፣ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ መሆኑ ከመጠቀሱ ውጪ ቦታው በወታደራዊ ሚስጥርነት ተይዞ እንደሚቆይ ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ እስከ ደብረሲና አስታጥቃ የሸኘችው ህወሃት ተሸንፎ ተመለሰ። ቀጥሎም ቸሰብአዊ መብትና መከላከያው አስገድዶ ደፈር የምትለዋ ጫና ከፍ ተደረገች። ይህ ሁሉ ኢትዮጵያን ከማስጨነቅ ያለፈ ጥቅም አላመጣም። ይልቁንም ለአሜሪካ ተቀናቃኝ ሃያላን በለስን እያስገኘላቸው ነበር። አሁን ላይ በመለዮ ለባሹ አልቡርሃን በኩል የተነፋፋው ጎማ ተንፍሷል። ህወሃት በኢትዮጵያ ሰሜንና ሰሜን ምእራብ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የኤርትራ ደህንነት ጉዳይ መሆኑ ቀብሩን ይበልጥ አፋጠነው። አልቡርሃን በመጨረሻ ሲዘረር ከኢትዮጵያ ጋር ትከሻ መላካቱን ገታ አድርጎ የገላባት መንገድን እስከመክፈት ሁኔታዎች ግድ አሉት። የጫና አማራጮች ተንጠፍጥፈው ማለቅ ሲጀምሩ ለትግራይ መልሶ ግንባታ ህወሃትን ገሸሽ በማድረግ የ300 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ ማእቀፉን ከመንገስት ጋር ገቢራዊ ለማድረግ ስምምነት ሲፈረም ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ያሰማው የአቤቱታና የርግማን አይነት የሚዘነጋ አይደለም። ይሁንና የኢትዮጵያን መንግስት የውጪ ፖሊሲ ለመጠምዘዝ የተለያዩ ካርዶች አሁንም ጥቅም ላይ መዋል ነበረባቸው። ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ድንበሮች አማተሩ። ፋርማጆን የማንሳት ምኞቷ በሀሰን ሼክ ፕሬዝዳንታዊ ድል እፎይ ብላ ሳትጨርስ ሐሰን ሼክ ወደ አስመራ ማቅናታቸውን የታዘብነው። ለወራት ፕሮፓጋንዳ የነዙበት የሶማሊያ ጦር በኢትዮጵያ ጦርነት ተሳትፏል የሚለው ሀሰት በሞቃዲሾው መሪ የአስመራ ጉብኝት ተጋለጠ። ሀሰን ሼክ በተቃራኒው አከስመራ ትብብሩን ለማጠናከር ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር ፊርማቸውን አኖሩ። አሁንም ሌላ አማራጭ ለዋሽንግተን የግድ ነበር። ይኸውም የህወሃትን ሽብር ከአልሸባብ ቡድን ጋር ማዛነቅ። አልሸባብ የፈፀመውም ህወሃት ከምእራባዊያን ተውሶት ነገር ግን አሁናዊ ቁመናው ሊሸከመው የከበደውን የቀናት የሽብር ተልእኮ ነበር። አሁን ላይ ህወሃት ከመንግስታዊ አሸባሪነት ወደ ሰፈር ወንበዴነት ተቀይሮ ጫካ ውስጥ ወደነበረበት አነሳሱ ተመለሰ ማለት ነው።

ሶማሊያ የህወሃት ሽብር ማህፀን እስከ መጨረሻ ቀብር

የሶማሊያ መንግስት ለወረራ ሲዘጋጅ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነፍጥ አንስተው የሚዋጉትን ድርጅቶች የወረራው አካል አደረጋቸው፡፡ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ መንግስት ለመመስረት ኢትዮጵያን ሲወጋ የነበረውን የሕወሓት መሪ መለስ ዜናዊ፤ ኦሮሞን ነፃ እንዲያወጣ ሶማሊያ የፈጠረችውን ነፃ አውጭ ድርጅት የሚመራውን ዋቆ ጉቱን እና የሲዳማ ነፃ አውጭ ተብሎ በሶማሊያ የተመሰረተውን ድርጅት የሚመራው ወልደአማኑእል ዱባለ ምሽጋቸው ሞቃዲሾ ነበረች። እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ሀገሮች የሚዘዋወሩት በሶማሊያ ፓስፖርት የነበረ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል(ሻ/ፍቅረስላሴ ወግደረስ፤ እኛና አብዮቱ)። ደርግ ገና ስልጣን ከመያዙ ድንበሬ አዋሽ ወንዝ ነው ብሎ እስከ “ድሬዳዋ ኤይር ፖርት” የደረሰውን የሶማሌ ጦር እየተዋጋ ወደ ነበረበት እንድያፈገፍግ ሲያደርግ መለስ ዜናዊ እና የህወሃት ባለስልጣናት ዚያድ ባሬ በሰጣቸው የሶማሌ ፓስፖርት እና “ጊዚያዊ ዜግነት ” ኢትዮጵያን ለሚወጋው የሱማሌ ጦር ድጋፋቸውን መስጠት ብቻም ሳይሆን የስለላ ድጋፍም ያገኙ እንደነበር ይታወቃል።

ከአገር አማን መጽሄት የተወሰደ

Leave a Reply