ሠራዊቱ በህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ገለጹ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በታላቁ ህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ግዳጁን እየተወጣ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ተናግረዋል።
ምክትል አዛዡ እንደገለጹት ሜካናይዝዱ ሰፋፊ ግዳጆችን በመፈጸም ከመተከል እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ስምሪቱን በማጠናከር ፀረ ሽምቅ እና ደፈጣ ውጊያዎችን በማካሄድ ጭምር የቀጣናውን ሰላም በጀግንነት አረጋግጧል ነው ያሉት።
ሜካናይዝዱ በመተከል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በስፍራው ተሰማርተው ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በስኬት እየፈፀመ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ምክትል አዛዡ “በፀረ ሰላም ኃይሎች መሠረተ ቢስ ሐሳብ ሳንገታ ሕብረ ብሔራዊነታችንን አጠናክረን በቀጣናው አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ምን ጊዜም ዝግጁ ነን” ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በምዕራብ ግዳጅ ቀጠና ተልዕኮውን እየፈፀመ ያለው የሠራዊት ክፍል ከውስጥም ይሁን ከውጭ በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን መመከትና መቀልበስ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አስተማማኝ ዝግጁነት መፍጠሩን የዕዙ ምክትል አዛዥ ተናገሩ።
ጀነራል መኮንኑ በአውደ ውጊያ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በየ ደረጃው ያለ አመራር ቅንጅት፣ ቁርጠኝነትና ጠንካራ አመራር ሰጪ መሆን የማይተካ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።
አትሌቶቻችን በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና በደረጉትን ትንቅንቅና ተጋድሎ ያስመዘገቡትን ድል በመጥቀስ ኢትዮጵያ አዲሱን በጀት ዓመት በድል ጀምራለች ያሉት ምክትል አዛዡ ድሉን በሁሉም የስራ መስክ በማስቀጠል የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ አንስተዋል።
ጠላት ሀገርና ህዝብን ሊያዋርድ አቅሙን አሟጦ ሲፍጨረጨር በመጠንከራችን ጠላትን ከፍላጎቱ በታች ማድረግ ችለናል። በዚህ ሂደት በየ ደረጃው ያለ አመራር ሚና የማይተካ እንደነበር በመጥቀስ አመራሮች አቅማቸውን በቀጣይነት አዳብረው የክፍሎቻቸውን አቅም በማሳደግ ለተሻለ ግዳጅ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ምክትል አዛዡ አክለውም አመራሮች የሚመሩትን ሰራዊት የማድረግ አቅምና የዝግጁነት ደረጃ ለማሳደግ የሚያግዙ የመሪነት ክህሎትን የሚያዳብሩ ተግባራትን ማከናወን አለባቸው ብለዋል።
Defense fb