ሁለተኛው ተርባይን ሀይል ማመንጨት ጀመረ ! ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ብቻ መመራት እንዳለበት ኢትዮጵያ አስታወቀች

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ሀይል ማመንጨት ጀመረ የሰላም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻ እንደሚካሄድ ኢትዮጵያ በድጋሜ አስታወቀች::

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመር ማብሰሪያ ሥነ ስርአት እየተካሄደ ነው።

በዛሬው እለት ስራ የሚጀምረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን፥ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል።

ባለፈው የካቲት ወር ዩኒት 10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

የሰላም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻ እንደሚካሄድ ኢትዮጵያ በድጋሜ አስታወቀች::

በመንግስትና በህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር በአፋሪካ ህብረት ብቻ መመራት እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬዉ እለት አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬዉ ዕለት በሰጡት መግለጫ ድርድሩ ሊመራ የሚገባው በአፍሪካ ህብረት ነው ብለዋል።

ከአፍሪካ ህብረት ውጭ የሚቀርብ የእናደራድር ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት እንደሌለው ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርድሩን በገንዘብና በቴክኒክ መደገፍ እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደር መለስ፣ ከዚያ ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ነው ያሉት።

ድርድሩን የሚመሩት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦሊሰጉን ኦባሳንጆ የአደራዳሪ ኮሚቴዎችን ከአፍሪካ አገራት ማካተት እንደሚችሉም ተነስቷል።

See also  የወያኔ አዲሱ የፖለቲካ ስልት!- ለአማራ

Leave a Reply