ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ምክንያት የተፈጠሩ 70 ደሴቶችን መጠቀም ትችላለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ነሐሴ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ካበረከታቸው 70 በላይ ደሴቶች መጠቀም እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ሶስተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ማጠናቀቂያ አብስረዋል።

የሶስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ባበሰሩበት ወቅት እንዳሉት በህዳሴው ግድብ ምክንያት 70 ደሴቶች ተፈጥረዋል።

ከ40 በላይ የሚሆኑት ደሴቶች እያንዳንዳቸው ከ10 ሄክታር በላይ ቦታ የያዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከ800 ሄክታር እሰከ 2000 ሄክታር በላይ ደሴት መኖሩን ጠቅሰው፣ ዝቅተኛው ደሴት 5 ሄክታር የሚይዝ ነው ብለዋል ።

እያንዳንዱ ደሴት ላይ ሪዞርቶች ቢገነቡና ውሃ ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ቢካተቱ የሚኖረውን የቱሪስት መስህብ አንስተዋል።

“በማንኛውም ግዜ ጎብኚዎች በዚህ ስፍራ መተው ሊዝናኑ ሊያዩ ግዜያቸውን በደስታ ሊያሳልፉ የሚያስችል ከፍተኛ ብቃት አለው” ሲሉም ተናግረዋል።

“አባይ የኛ የፈጠራ ውጤት አይደለም አባይ የፈጣሪ ስጦታ ነው የፈጣሪን ስጦታ በአግባቡ እንድንጠቀምበት በአግባቡ እንድንገለገልበት ታስቦ የተሰጠን ነው” ብለዋል።

Leave a Reply