ብልጽግና “ተላላኪ” ያላቸውን ሊመነጥር ነው፤ መረጃው ተጠናቋል

ከትህነግ ጋር አብረው ሲሰሰሩ የነበሩ ባለሃብቶች ስጋት ላይ ናቸው

አገሪቱን እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ከነኮተቱ እንደማይቀጥል አቋም ከተያዘ በሁዋላ ” ተላላኪ” ያላቸውን የጠላት ሃይል ሊመነጥር መረጃና ምርመራ አካሂዶ መጨረሱ ተሰማ። ቀደም ሲል በግልጽ ውክልናና በጎንዮሽ “ባለሃብት” ስም ለትህነግ ሲነግዱ የነበሩ ስጋት ላይ መውደቃቸው ተሰምቷል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆን ለአዲስ አበባ ተባባሪ ዘጋቢያችን እንደጠቆሙት ብልጽግና “መንጥር” ዘመቻ ውስጥ ለመግባት የወሰነው የአገኢቱን የጸጥታ ተቋማት ደህንነቱን ጨምሮ ከባዶ አንስቶ ግዙፍ በሚባል ደረጃ አደራጅቶ በመጨረሱ ነው። “ሁለት ማሊያ ለብሰው በተለያዩ አግባቦች ትህነግን ሲያገለግሉ የነበሩ ብዙም ድብቅ አልነበሩም” ያሉት የዜናው ባለቤቶች ” ዛሬ አገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚሞክርን ማናቸውንም ሃይል ማክሰም የሚችል ሃይልና ዘመናዊ ክህሎትና ቴክኖሎጂ የሚጠቀም የደህነት ተቋም በመገንባቱ አሁን ላይ ድርጅቱን ለማጽዳት የሚያግድም ሆነ የሚያስፈራ ሃይል የለም” ሲሉ የጊዜውን መድረስ አመልክተዋል።

የሰላም ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ይህ ችግር እንዳለ በይፋ ማስታወቃቸው ይታወሳል። የአገሪቱ ከፍተኛው የአመራር ሃይል የሆነው ብሄራዊ የደህንነት መክር ቤትም ” አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚያሰጋ ሃይል የለም” ማለቱ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ሌቦችንና ባንዳዎችን መታገስ የማይቻልበት ደረጃ መደረሱን በይፋ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ከላይ ጀምሮ ብልጽግና ውስጥ ሆነው “ትህነግ ይመጣል” በሚል ሲነቀሳቀሱ የነበሩ በመንጥር ዘመቻው እንደሚካተቱ ታውቋል። እርምጃውም ለህዝብ በግልጽ እንደሚነገር ዜናውን ያጋሩን አመልክተዋል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ምስጋና አቅርቡ” ሲሉ ያቀረቡት ምላጃ ምክንያትም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለህዝብ እንደሚገልጽ እነዚሁ ክፍሎች ጠቁመዋል። የመንግስት የጸጥታ ተቋማት በጋር ታላቅ ስራ በመስራታቸው የጠላት ሃይልና ዕቅድ መከሸፉን የሚያሳይ ክፍለ ጊዜ ጨምሮ በርካታ የምስጋናው ብስራቶች ለህዝብ ይፋ እንደሚሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

በተመሳሳይ ዜና ከባንክ ዕዳ ጋር በንብረት ግዢ ስም ብር ለትህነግ ነጋዴዎች ሲያቀባብሉ የነበሩ፣ በግልጽ ውክልናና በጓሮ ስምምነት ለትህነግ ሲሰሩ የነበሩ ” ባለሃብቶች” መደናገጣቸው ተሰምቷል። መደናገጡ የተፈጠረው ትህነግ ካሁን በሁዋላ ወደ ማዕከላዊ ስልጣን የመመለስ አቅሙና ብቃቱ በመከኑ እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

See also  ዶ/ር ኮንቴ " እውነቱን እናውቀዋለን፣ ትህነግ ጨፍጭፎናል" በአፋር የሶስት ቀን ሃዘን ታወጀ፤ ትህነግ ተጨማሪ 8 የቤተሰብ አባላት ገደለ

ግንዘብ ባምስተላለፍ፣ ክፍያ በመፈጸምና አግሪቱ በአቅርቦት ችግር እንድትወጠር ከሚሰሩ ጋር ተሳትፎ ያላቸው በመንግስት የመረጃ ሃይሎች ታውቀዋል። እንደዜናው ሰዎች ከሆነ ስራቸውን የሚያውቁ በግልጽ ቀርበው ንስሃ የገቡ አሉ። አገር ወዳድ መስለው በዘመቻው ወቅት የወታደር ልብስ ለብሰው ሲፎክሩና ሲያስፎክሩ የነበሩ ” ለምድ ለባሽ” በሚል የሚጠሩ ዛሬ ላይ በስጋት መሆናቸው ታውቋል። ወታደር ሲመለምሉና ደመወዝ ሲከፍሉ የነበሩ ” ባለሃብት” የሚባሉ ስጋት ውስጥ ቢሆኑም መንግስት እስካሁን የውሰደው እርምጃ አለመኖሩን ከዜናው ባለቤቶች ለመረዳት ተችሏል።

Leave a Reply