በኖርዌይ ከመዋጮ ገንዘብ ዝውውር ጋር ተያይዞ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ነገ ውሳኔ ይሰጣል

  • አሁን ባለው ህጋዊ ምንዛሬ ተጠራቀመ የተባለው 11.3 ሚሊዮን ገደማ ብር ለጊዜው ታግዷል

በኖርዌይ የስታቫንገር ፍርድ ቤት መጠኑ ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ ዘውውር ሳቢያ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ክስ መመሰርቱና ተከሳሾች የመከራከሪያ ምላሽ መስጠታቸው ተሰማ። ከተለያዩ ሰዎች ተሰበሰበ የተባለው 11.3 ሚሊዮን ገደማ ብር ለጊዜው ታግዷል። ነገ የፍርድ ውሳኔ እንደሚሰማም ታውቋል።

በኖርዌይ ያልተለመደ ወይም ተደጋጋሚ የገንዘብ ዝውውር ሲፈጸም የአገሪቱ ባንክ ለፖሊስ ጉዳዩ እንዲታይለት ይጠይቃል። በዚሁ መነሻ ክስ መመሰረቱን ሂደቱን እየተከታተሉ ያሉ አመልክተዋል። ብሩ ተሰበሰበ የተባለው ለኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ቢሆንም በገንዘቡ አሰባሰብ በኩል በተከሳሾች መካከል ስምምነት እንደሌለ አንድ የኮሚኒቲው አባል ለኢትዮ12 አመልክቷል።

የፍርድ ሂደቱ ከመተናቀቁ በፊት በክሱ የተካተቱትን ስም መዘርዘር ባይቻልም፣ ክስ የተመሰረተባቸው የኦሮሞ ተወላጅ መሆናቸው ናቸው። ገንዘብ በማዋጣት የተሳተፉት ተከሳሾች ያዋጡት ለልማት እንደሆነ በመግለጽ ቃላቸውን ሰጥተዋል። በዚህም ሳቢያ እርስ በርስ ስምምነት አለመኖሩ ታውቋል።

ፍርድ ቤቱ በሁለት ቀጠሮ ክስ የማዳመጥ፣ የክስ መከላከያ ምላሽ የመስማት ተግባሩን ባለፉት ሁለት ቀጠሮዎች አከናውኗል። በአገሪቱ አሰራር መሰረት ሶስተኛ ቀጠሮ ውሳኔ የሚሰጥበት እንደሆነ ታውቋል። በዚህ አግባብ ቀጠሮው ለነገ መሆኑን ለሰሌዳው ለመረዳት ተችሏል።

ይህን ዜና የሰሙ መንግስትን፣ በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ” በድን” ሲሉ አውግዘውታል። በከፍተኛ ሪፎርም አዲስ የተመደቡት ዲፕሎማቶች ፍጹም የደነዘዙና ዜጎች ሊረዱዋቸው ሲፈልጉ እንኳን ፈቃደኛነት የጎደላቸው መሆናቸውን አመልክተዋል። በኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሰባራ እንደሆነ የሚነገርለት የብልጽግና መንግስት ይህን ጉድለቱን ባለማረሙ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ጉዳይ ላይ መተኛቱን ገልጸዋል።

መንግስት ሸኔ የሚለው፣ ኮሚኒቲው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ሲል የሚጠራው ሃይል ብቻ እንደሚታወቅ ጃዋር መሃመድ መናገሩ ይታወሳል። በቅርቡ “የምስጋና ፕሮግራም” በሚል የተለያዩ አገራትን እያካለለ ያለው ጃዋር ” በህግ የተመዘገቡት ኦፌኮና ኦነግ አሉ። የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት አለ” ጃዋር ተናግሯል። ጃዋር ይህን ያለው በቅርቡ በወለጋ የተጨፈጨፉትን ነጹሃን አስመልክቶ ” ኦነግ ሸኔን ታወግዛለህ” ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ነው። ጃዋር በዚሁ ምላሹ ” በኦሮሞ ስም አማራን የሚገል ሃይል የለም። ኦነግ ሸኔ ብሎ ነገር የለም” ብሏል።

See also  መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ

Leave a Reply