“የኢትዮጵያ መንግስት ሰላም ሰላም በሚል የሚለምነው ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ነው” ሲሉ ዶክተር ደብረጽዮን መናገራቸው፣ “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ነኝ” ሲል ራሱን የሚጠራው ሃይል ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በግልጽ ማረጋገጫ መስጠቱን የሚያሳይ እንደሆነ ተመለከተ።

ከትግራይ ህዝብ እጅግ መቸገሩንና ሰላም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባው በስፋት በሚወተወትበት በአሁኑ ወቅት፣ የትግራይን ክልል እያስተዳደሩ ያሉት የትህነግ መሪ ዶክተር ደብረጽዮን የሰላም ምላጃውን ማጣጣላቸው ኢትዮጵይ እንድትፈርስ ካላቸው ዕቅድ ጋር በተያያዘ መሆኑን ማረጋገጣቸው በወልቃይት አቅጣጫ ጦርነት ለመጀመር እቅድ መኖሩንም አመልካች እንደሆነ የተናገሩ አሉ።

በትግራይ በተካሄደ መድረክ ደብረጽዮን በትግርኛ ” የሚለምኑን ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ነው” ብለዋል። ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የጦርነት ሙሉ ዝግጅት አድርጎ መጨረሱንና ወላቅይትን በሃይል በክረምት እጁ እንደሚያስገባ ለወዳጆቹና ደጋፊዎች አስታውቆ የነበረው ትህነግ እስካሁን ለምን ጦርነት እንዳልጀመረ አላስታወቀም።

ላለፉት 27 ዓመታት ከፍተኛ የነዳጅ ክምችትና መሳሪያ ቀብሮ ኤርትራን ለመውረር ሲዘጋጅ እንደነበር የተነገረለት ትህነግ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሙሉ ዕቅድ እንዳለው በተለያዩ ጊዜያት ምልክት ቢሰጥም ደብረጽዮን በይፋ እንዳሉት ግን በቅርቡ የተናገረ አመራር የለም። በገደማዳሜና በውስጥ ለውስጥ ወይም በትህነግ የሚዲያ ካድሪዎችና ደጋፊዎች አንደበት ሲነገር እንደነበረው ዓይነት ደብረጽዮን ይህን ማለታቸው ከምን መነሻ እንደሆነ ለጊዜው ግልጽ መረጃ አልቀረበም።

ስለ ሃይል አሰላለፍ ጠንቀቀው የሚያውቁ ኢትዮጵያ አሁን እፎይታ ሰራዊቷን ፕሮፌሽናል አድርጋለች፣ ከባድ መሳሪያ ተኳሽ አብቅታለች፣ ዎፒ በበቂ አላት፣ ትንንሽ ቁጥር ሆነው በስውር ገብተው የሚያጠቁ ኮማንዶዎች በብዛት አሏት። ሜካናይዝድ ሃይል የነበረበት የባለሙያ ችግር ተቀርፏል። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ገንብታለች፣ አየር ሃይሉ በከፍተኛ ደረጃ ተደራጅቶ ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቋል። ሙሉ በሙሉ ዘመቻውን በቴክኖሎጂ መምራት የሚያስችል አቅም አለ። የክልል ልዩ ሃይል ሳይጨምር መከላከያ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠር ሃይል አለው። ተተኪ ማስለጠኛ ተቋማት ውስጥ አለ። በዚህ ሁሉ ላይ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል በከፍተኛ ደረጃ ተደራጅቷል። ድፍን የወልቃይት ህዝብ ወታደር ነው … የሚሉ ትህነግ ጦርነትን አይሞክርም፣ ከሞከረም እብደት ሊሆን እንደሚችል ከግምት በላይ ይናገራሉ።

በትህነግ በኩል ደሞዝ የለም። ድሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተኝቶ በነበረበት ወቅት ከተቀበረ መሳሪያና ነዳጅ በስተቀር የኢትዮጵያን መከላከያ ሊቋቋም የሚችል አቅምና ቴክኖሎጂ እንደሌለው እያወቀ ስለ ጦርነትና ቅድም ሁኔታ መናገሩ በራክቶችን እያነጋገረ ነው። ከሁሉም በላይ ህዝብ የጠላውና ዳግም ሊያየው የማይፈልግ ድርጅት ሆኖ ሳለ ከትግራይ ውጭ ለምን እንደሚያስብ በርካቶችን ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነው።

በትግራይና የትግራይ አጎራባች አካባቢዎች በከፍተኛ ችግር ላይ እንዳሉ የሚያሳዩ መረጃዎች በስፋት በሚወጡበት በአሁን ሰዓት፣ እህቶች ራሳቸውን ለገበያ እያቀረቡ ባሉበት በዚህ ወቅት በምንም መስፈርት ጦርነት ማሰብ አገባብ እንዳልሆነ የሚናገሩ ” ህዝብ ጫና ማድረግ አለበት። አለበለዚያ ጦርነት ከተጀመረ ጣጣው እስከወዲያኛው ይሆናል” ሲሉ እያስተነቀቁ ነው።

ከትግራይ አምልጠው እንደመጡ የሚናገሩ በሚሰጡት ምስክ የሰሙ ትህነግ ” ቢበቃውስ” ሲሉ ይጠይቃሉ። የትህነግ ወዳጆችም በጭፍን ውጭ ቁጭ ብለው ጦርነት ከሚቀሰቅሱ ሰላም እንዲሰፍን ቢሰብኩ እንደሚሻል ይመክራሉ።

Leave a Reply