“አሳዛኝ ነገር ግን የሚጠበቅ ዜና” ትህነግ ከመከላከያ ሰራዊት ይልቅ የትግራይን ሰራዊት ደግፉ አለ

ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ተሰጠ በተባለው የ”ተወጋን” አቤቱታ ግርጌ የተሰጠው አስተያየት መራር ሲሆን ” ቀደም ሲል እንደ ባዕድ ቆጥራችሁ የበተናችሁትን፣ያረዳችሁትን፣ የከዳችሁትን፣ እንዲሁም የጎሳ ፖለቲካ ረጭታችሁ አገሪቱ ለማፍረስ ሌት ከቀን እንደምትሰሩ፣ ሳንሞት በህይወት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈርሳ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም…ስትሉ እንዳልነበር፣ አሁን ለዚህ ሃይል ድጋፍ መጠየቅና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አይኑ ብሌን ከሚያየው መከላከያ አስበልጦ ወገናዊ እርዳታ እንዲያደርግለት መጠየቅ ዳግም ክህደት ነው። ጊዜ ሳትፈጁ ለሰማዊው ህዝብ ስትሉ ወደ ሰላም ኑ” የሚሉ አሳቦች ተሰንዝረዋል።

“አሳዛኝ ነገር ግን የሚጠበቅ” ሲሉ ትህነግ የጀመረውን ጦርነት በመኮነን ካናዳዊቷ ፕሮፌ ሰር አን ፊትዝ ጌራልድ አስታወቁ። በማለዳ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ስያሜ የሚጠራው ትህነግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከትግራይ ሰራዊት ወገናዊ ደጋፍ እንዲሰጥ መጠየቁ ስላቅ አስነሳ። የኢትዮጵያ ባለውለታ መሆኑንንም አስታውሷል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ ለትግራይ ወጣቶች የሰላም ጥሪ አቀረቡ።

“ጦርነት ናፋቂ” ሲሉ የገለጹትና ፓርላማ አሸባሪ ብሎ የሰየመው ትህነግ፣ “የሚጠበቀውን ጦርነት ጀምሮታል” ሲሉ ፕሮፌ ሰር አን ፊትዝ ጌራልድ አመልክተዋል። ይህን ለማለት ያስደፈራቸውን ምክንያት ለኢፕድ ዘርዝረዋል።

ጦርነት ናፋቂው አሸባሪው ትህነግ “የሚጠበቀውን ጦርነት ጀምሮታል” ያሉት ፕሮፌሰሯ፣ ትህነግ ጦርነቱን እንደሚጀምርና የሰላም መንገዱን እንደሚረግጥ ግልጽ እንደሆነ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጌራልድ፤ ትህነግ ዛሬ የጀመረውን ጦርነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት የህወሓት የሰሞኑ መግለጫዎች ለሰላም ጥረቱ እንቅፋቶች እንደነበሩ አውስተዋል። በቡድኑ ይለቀቁ የነበሩ መግለጫዎችና የተባባሰው የውሸት መረጃ የጦርነቱ አመላካች እንደነበሩም ነው ፕሮፌሰር አን የገለጹት።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ፣ ፍትሃዊ ያልሆነው ማዕቀብ እና የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔን የተቹት ፕሮፌሰሯ፤ ህወሓት የጀመረው ጦርነት በእነዚህ ምክንያቶች ማንም ሊያስቆመው እንደማይችል ግልጽ ነበርም ብለዋል።

ፕሮፌሰግ አን እንዳሉትም፤ የሰሞኑ የሽብር ቡድኑ መግለጫ፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም ትችት፣ የፕሬዝዳንት ባይደኑ የነጩ ቤተመንግስት መግለጫ፣ የሽብር ቡድኑ መሪ ደብረጽዮን ደብዳቤ እና ሌሎች መረጃዎች ህወሓት ጦርነት እንደሚከፍት አመላካቾች ነበሩ።

See also  protests-erupt-in-sudan-over cost of living

እንደተለመደው ጦርነቱን ከጀመሩ በኋላም ልክ ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈጽመውና ጦርነት ጀምረው ሲያበቃ ቃል አቀባያቸው ሴኩ ቱሬ ባልጠበቁት መንገድ በአደባባይ ወጥቶ እስኪናገር ድረስ “እኛ ይደለንም” ብለው ክደው እንደነበረ ሁሉ አሁንም “ጦርነት ተከፈተብን” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ከፍተዋል።

ለህዳሴ ግድብ “እንኳን ደስ ያላችሁ” ያለው ማርቲን ፕላውት አጭበርብሮ የለጠፈው ምስል ሲጋለጥ የሚያሳይ

የዚህ ዘመቻ ዋና አቀናባሪ ከሆኑት የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎች መካከል አንዱ ማርቲን ፕላውት በኢትዮጵያ መከላከያ የተሰጠውን ትክክለኛ መግለጫ ለማቃለል በሞከረበት ሀሰተኛ ዘገባ ሀሰተኛ ምስል ተጠቅሞ የሽብር ቡድኑ የውሸት ዘመቻ በይፋ መጀመሩን በራሱ ዘገባ አጋልጧል።

ማርቲን ፕላውት ሌላ አገር ላይ የወደቅን አነስተኛ የአውሮፕላን ምስል በመጠቀም ኢትዮጵያ መትቼ ጥያለሁ የምትለው ይህንኑ አውሮፕላን እንደሆነና አውሮፕላኑ ያን ያህል ብዛት ያለው የጦር መሳሪያ ሊያጓጉዝ አይችልም ሲል የመንግሥትን መረጃ ለማስተባበል ሞክሯል።

ይሁን እንጂ ምስሉ ሀሰተኛም ብቻ ሳይሆን የሽብር ቡድኑ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ “የተመታ አውሮፕላን የለም” ብሎ ከሰጠው መረጃ ጋር እንኳን የማይገናኝ ያልተናበበ የውሸት መረጃ መልቀቅ መጀመራቸው በግልጽ ታይቷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የትግራይ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው በመነጋገር፣ በመወያየት እና በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ ለትግራይ ወጣቶች የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር አብርሃም በላይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የፌደራል መንግስት ለሰላም ያሳየውን ዝግጁነትና ያቀረበው ጥሪ አሸባሪው ህወሓት ወደ ጎን በመተው፣ የትግራይ ህዝብ ተስፋ ያደረገበትና በጉጉት ሲጠብቀው የቆየውን የሰላም አማራጭ በመተው ዛሬ ጦርነት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ማለዳ ጦርነቱ መጀመሩን ያበሰረው የትህነግ መግለጫ “ለተከበራቹህ የኢትዬጵያ ህዝቦችና የፖለቲካ ሃይሎች” ይላል፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሃይል መግለጫ ቀጥሎም “የትግራይ ህዝብ ‘ሀገሬ ለሚላት ኢትዬጵያ’ እጅግ ውድ ዋጋ የከፈለ ጠንካራ ኢትዬጵያዊ እንጂ የኢትዬጵያ ጠላት አይደለም” ሲል ያክላል። ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ያለፉትን ሃምሳ ዓመታት ሲሰራ የነበረው ትህነግ ለኢትዮጵያ የለፍበትን ታሪኩን አስታውሷል። ይህን ያዩ ይህ የሆነው የድርጅቱ መሪ ” ሰላም ሰላም እያሉ የሚለምኑን ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ነው” በማለት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰሩ በይፋ በትግርኛ ቋንቋ ካስታወቁ ከሳምንት በሁዋላ መሆን አስገራሚ እንደሆነ አመልክተዋል።

See also  ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር መርማሪ ኮሚሽኑ ሊያወጣ ያዘጋጀው ሪፖርት ዓላማ ፖለቲካዊ ነው

” … ጠላቶቻችን ራሱን ፅኑ ኢትዬጵያዊ ኣድርጎ ያምን በነበረው የትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፅሙት ያለውን ጆኖሳይድ በመቀጠል እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከበው ለረሃብ ፣ ለበሸታና ጭንቀት ከዳረጉት በኋላ ዛሬ ወታደራዊ ጥቃት ጀምረውበታል።ይሁንና ፍላጎታቸው በሃይል ሊያሟሉ ከቶም እንደማይችሉ ተገንዝበው ጦርነቱን እንዲያቆሙ ፣የትግራይ ህዝብ እንደ ሕዝብ የህልውናውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል ወገናዊ ድጋፋቹሁን እንድታሳዩት የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ጥሪዉን ያቀርባል” ሲል በተለይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀርበው ጥሪ ” የትህነግን ሃይል ከመከላከያ በላይ ውደዱ፣ አፋርና አማራ ክልልን ዓመድ አድርጎ፣ ዘርፎ፣ጨፍጭፎና አስነዋሪ ድርጊት ፈጽሞ ለሄደው ሽፍታ ወግኑ በሚል ትህነግ ለማን ጥሪ እንደሚያቀርብ አለመረዳቱ የድጅቱን መበስበስ አመላካች ነው” ብለውታል።

ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ተሰጠ በተባለው የ”ተወጋን” አቤቱታ ግርጌ የተሰጠው አስተያየት መራር ሲሆን ” ቀደም ሲል እንደ ባዕድ ቆጥራችሁ የበተናችሁትን፣ያረዳችሁትን፣ የከዳችሁትን፣ እንዲሁም የጎሳ ፖለቲካ ረጭታችሁ አገሪቱ ለማፍረስ ሌት ከቀን እንደምትሰሩ፣ ሳንሞት በህይወት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈርሳ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም…ስትሉ እንዳልነበር፣ አሁን ለዚህ ሃይል ድጋፍ መጠየቅና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አይኑ ብሌን ከሚያየው መከላከያ አስበልጦ ወገናዊ እርዳታ እንዲያደርግለት መጠየቅ ዳግም ክህደት ነው። ጊዜ ሳትፈጁ ለሰማዊው ህዝብ ስትሉ ወደ ሰላም ኑ” የሚሉ አሳቦች ተሰንዝረዋል።

Leave a Reply