አሸባሪው ህወሃት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

መነሻውን ከሰመራ ያደረገ ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር A47679 አይሱዙ ተሽከርካሪ መዳረሻውን ወደ አሸባሪው ህወሓት ቡድን በማድረግ 3000 /ሦስት ሺህ/ ሊትር ናፍጣ እና 2000 /ሁለት ሺህ/ ቤንዚል ካልዋን ላይ ሲደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙት መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት አሸባሪው ህወሓት በሀገራችን ላይ ጦርነት ቢከፍትም በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን አፀፋዊ ምላሽ እየተሠጠ ባለበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ለጠላት ሊደርስ የነበረን ነዳጅ መቆጣጠር ችለናል ብለዋል።

መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ አክለውም በቀጣይም ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን በህገወጥ መንገድ ሊደርስ የሚችል ማንኛውም ነገር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ምንላርግህ ሞሴ
ፎቶ ምንላርግህ ሞሴ Ethiopian Defence fb

Leave a Reply