ትህነግ ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ጠየቀ፤ የሰው ማዕበል አሰለፎ የሚሟሟተው የድርድር ጉልበት ለመጨመር ነው

ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ የሚለው የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ከጦርነቱ ግንባር ጀርባ ጥቃት ሲጀመርበት፣ ያሰበውን ማሳካት የማይችልበት ደረጃ መድረሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኑንን እንዳስታወቀ ተሰማ። የመንግስት ሃይል በሌላ ግንባር እየገፋ ነው።

የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪያችን በቅርብ የሚገናኛቸውን ዲፕሎማት ጠቅሶ እንዳለው ትህነግ ለመደራደር መንግስት ያቀረበውን አሳብ እንደሚቀበልና የተኩስ አቁም እንደሚፈርም በወኪሎቹ አማካይነት አስታውቋል። ይህንኑ አስመልክቶ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ዲፕሎማትን ማናገር እንዳልቻለም አመልክቷል።

ከነዳጅ ዝርፊያው ጋር በተያያዘና ጦርነቱን ራሱ ትህነግ እንደጀመረ በመረጋገጡ ብቻ ሳይሆን በውጤቱም ያን ያልህል እንደማይገፋበት በመታወቁ ይመስልላ ሲያስታጥቁት ከነበሩት ሃይሎች ይህ ያህል ሙገሳ አለገኘም። ይሁን እንጂ መግፋት ከቻለ አጣድፈው የሽግግርጥያቄያቸውን እንደሚገፉበት ጥርጥር የለውም።

በየትኛው ግንባርና አቅጣጫ የመንግስት ሃይል እየገፋ እንደሆነ ለጊዜው ለመግለጽ እንደማይወዱ ያመለከቱት እማኞች፣ በትህነግ ተይዘው የነበሩ አንዳንድ ቦታዎች መከላከያ እጅ ገብተዋል።

ከጦርነቱ ዜና ጋር ሳማንታ ፓዎር ትህነግ ከ150 ሺህ በላይ ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን ፍጹም የሚወገዝ ተግባር እንደሆነ ማምለከታቸው፣ የአይሪሽ ዝርያ ያላቸው ሳማንታ ትህነግን በዚህ መልኩ ሲዘልፉና ሲቃወሙ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ፣ “እነሱ ሲያጣጥሉም ያውቁበታል” አስብሏል። መግለጫው ትህነግ መገፋት እንደደረሰበት አመልካች እንደሆነ ተወስዷል።

በወገንተኛነታቸውና ኢትዮጵያን ወክለው በተቀመጡበት ወንበር ልክ መመመዘን እንዳልቻሉ የሚወቀሱት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ወዳጅና ቅርብ እደሆኑ የሚነገርላቸው ሳማንታ ፓወር ብቻ ሳይሆኑ ” ትህነግ አዲስ አበባን ሊቆጣጠር አርባና ሃምሳ ኪሎሜትር ላይ ነው” በሚል የሃሰት ምስል ለጥፎ ሃሰት ሲረጭ የነበረው ሲኤን ኤንም ” ነዳጅ የዕርዳታ ስራ የጀርባ አጥንት ነው። ያለነዳጅ ድርጅቱ ምን ሊሰራ ይችላል። ድርጊቱ የሚወገዝ ነው” በሚል ትህነግን ሲዘልፍ መራር ቃላትን ተጠቅሟል።

See also  የህወሃት ታጣቂ በሚንቀሳቀስበት አብይአዲ አካባቢ የ3 ደንበር የለሽ የሃኪሞች ተገደሉ

የአሜሪካና ወዳጆቿ የአውሮፓ አገራት የጉዲፈቻ ልጅ እንደሆነ የሚነገርለት ትህነግ፣ ቆሜላታለሁ ለሚለው የትግራይ ሕዝብ ጉሮሮ ማርጠቢያና አንጀት መደገፊያ እንዳይደርስለት ከዓለም የመግብ ድርጅት የዘረፈውን ነዳጅ አስመልክቶ “አልዘረፍኩም ያበደርኩትን ነው የወሰድኩት” በሚል መግለጫ ቢያወጣም፣ ሲ ኤን ኤን “የትህነግ ታጣቂዎች የዓለም ምግብ ድርጅትን ቅጥር በሃይል አልፈው በመግባት ዘርፈዋል” ሲል ከስፍራው ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል።

ይህ በሆነ አንድ ጀንበር ስር ኢትዮጵያን ያለ ጥፋቷ ሲቀተቅጡ የነበሩ ታላላቅ ድርጅቶችና ሚዲያዎች እየመረራቸውም ቢሆን ትህነግ ላይ ዞረውበታል። መንግስትም “የጦር ወንጀል ነው” ሲል ዝርዝር ጉዳዩን አቅርቦ ለትግራይ ሕዝብ አገልግሎት ሲላክ የነበረውን ነዳጅ ትህነግ እንደዘረፈ እነዲመልስ፣ እርዳታ ለተገባለት ዓላማ ስለመዋሉ እንዲጣራለትና ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቋል። ይህን ባለ ሰዓታት ውስጥ ደግሞ የትህነግን ወታደራዊ ኢላማዎች ለይቶ እንደሚያጠቃ አስታውቋል። ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብ ከተመረጡ ወታደራዊ አካባቢዎች ራሱን እንዲያርቅ አመልክቷል።

“ከእንግዲህ አይደለም የጠላት አውሮፕላን ይቅርና ፍቃድ የሌለው በራሪ አዕዋፍ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ አይበርም። እበራለሁ ካለም ከሰማይ ወደ ምድር በእሳት እየተንቦገቦገ እንዲወርድ እናደረገዋለን።” ሲሉ የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ አስቀድመው እንዳስታወቁት አየር ሃይል ጥቃት መሰንዘር መጀመሩ ታውቋል።

መቀለ አካባቢና አዲግራት የሚገኝ የተመረጠ ስፍራ በኢትዮጵያ አየር ሃይል መደምሰሱ ተሰምቷል። አቶ ጌታቸው መንግስት መዋዕለ ህጻናት መምታቱን አመልክተዋል። ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ጥቃት እንደሚፈጸም ከማስተንቀቁ በቀር ስለተወሰደው እርምጃ ይህ እስከታተመ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

አሜርካና ወዳጆቿ ጦርነቱ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር እየወተወቱ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ትህነግ የጀመረውን ጦርነት መግፋትና ያለመውን ባያሳካም እንዳላቆመ ተመልክቷል። በዚህም የተነሳ መንግስት የሰላም አማራጭ እንዳለ ሆኖ ሙሉ ሃይሉን እንደሚጠቀም ይፋ አድርጓል። ከመንግስት ማረጋገጫ ባይሰጥም በቆቦ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ወደፊት እየገፋ መሆኑን ምስክሮች ተናግረዋል።

See also  በሶስት ጣቢአይዎች ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው ስለተገኙ ነገ ምርጫ አይካሄድባቸውም፤ አጥፊዎቹ በህግ ይጠየቃሉ

መደበኛ ካልሆኑ የመረጃ ሰዎች እንደተደመጠው ትህነግ ወደ ጦርነቱን አቁሞ ወደ ንግግር ካልመጣ የመንግስት ሃይሎች በአጭር ቀን መቀለን ለመያዝ እንደሚገደዱ ገልጸዋል።

የፋርና የአማራ ልዩ ሃል፣ ሚሊሻና የጸጥታ ሃይሎች፣ እንዲሁም ሕዝብ በተጠንቀቅ እንዲቆም መታዘዙ ይፋ በሆነበትና የትህነግ ወዳጆች ዝም ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ” ለተቸገሩ ዕህል ለማደረስ ነዳጅ የለም” ሲሉ የነበሩት ዶክተር ቴዎድሮስ ” ለተራቡ ቤተሰቦቼ ገንዘብ መላክ አልቻልኩም” የሚል መልዕክት በማህበራዊ ገጻቸው ለጥፈዋል። አክለውም ” ለራስህ መቆም አለብህ፤ ለራስህ ካልቆምክ ማንም ላንተ አይቆምም” ብለዋል። ይህ ጥቅሳቸው ” አሁንስ ተስፋዬ አሜሪካና አውሮፓ አይደለምን የሚለውንና ለዚህ መቀመጫ ያበቃቸውን መሃላቸው የት ገባ የሚያሰኝ ነው። ሰዎቹ ሲከሰክሱ ያውቁበታል” የሚል ትችት አስነስቶባቸዋል። ይህንኑ አሳባቸውን ባሰፈሩበት የማህበራዊ ገጽ አውዳቸው ክፉኛ ተውቅሰዋል። ለወገኑ እንደሚቆረቆር ባለስልጣን ድርጅታቸው ነዳጅ ሲሰርቅ አለመቃወማቸው በባልደረቦቻቸው ሳይቀር እንዳስተቻቸው ተሰምቷል። ለዚህም ነው ” እያለህ ካልሆነ” አይነት ዘፈን የዘፈኑት።

Leave a Reply