ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ – ተመትቶ ስለወደቀው አንቶኖቭ አውሮፕላን አንቶኖቭ 26

“ሁሌም በተጠንቀቅ”፦ በአየር ኃይላችን ተመትቶ የወደቀው አንቶኖቭ አውሮፕላን

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለአሸባሪው ሕወሓት ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ በመግባቱ በየኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመትቶ መውደቁን መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ እና ለአሸባሪው ሕወሓት ድጋፍ ለማድረግ የአገሪቱን አየር ክልል ጥሶ እንደገባ በተደረገ ማጣራት የተረጋገጠው “አንቶኖቭ 26” የተሰኘው የራሽያ ስሪት የሆነ አውሮፕላን እንደሆነ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ነሀሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡50 ሰአት ላይ በአየር ኃይል ራዳር የታየው አውሮፕላኑ በተከለከለ ቀጠና በመግባቱ እና በተደረገው ማጣራት ያልተፈቀደለት መሆኑ በመረጋገጡ ከምሽቱ 3 ሰአት 30 ላይ ተመትቶ መውደቁን ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ገልፀዋል።

አውሮፕላኑ የመጫን አቅሙ 5 ቶን ሲሆን 40 ወታደሮችን ከነሙሉ ትጥቃቸው እንደሚይዝ እና አጠቃላይ ክብደቱም 24 ሺህ ኪሎ ግራም እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ በመተላለፍ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ የገባውን አውሮፕላን የተኩስ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ጀግናው አየር ኃይል በታጠቀው የውጊያ አቅም በተወሰደው የተሳካ እርምጃ ተመትቶ መውደቁን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ገልፀዋል።

የአየር ኃይሉ ዋነኛ ተልዕኮ ማንኛውም ያልተፈቀደለት አውሮፕላን የአገሪቷን ሉአላዊ የአየር ክልል ጥሶ እንዳይገባ ማድረግ መሆኑን ያስታወሱት ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ በታጠቃቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች በመታገዝ የአየር ክልሉን ለ24 ሰአታት እና ለ7 ቀናት ያለማቋረጥ እንደሚያስከብር በድጋሚ አረጋግጠዋል። EBC

See also  የጸጥታው ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ጎን እንዲቆም ተጠየቀ

Leave a Reply