“መከላከያ ሲዋጋ ሐሞት አፍሳሽ መግለጫ ለሚያወጡ ትዕግስት የለንም”

“መከላከያ ሲዋጋ ሐሞት አፍሳሽ መግለጫ” ለሚያወጡ ትዕግስት የለንም” ዶ/ር አለሙ ስሜ በጠ/ሚ ቢሮ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚንስትር አስጠንቅቀዋል

የህወሃትን ወንጀል በማለባበስ የዕርዳታ አቅርቦት እንዲሁም አስቸኳይ የ”ሰላም” መግለጫ ያወጡ ሲቪል ማኅበራት እርምት ካላደረጉ ርምጃ ይጠብቃቸዋል።

ዶ/ር አለሙ ስሜ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችን አርብ ዕለት ሰብስበው በሰጡት ማብራሪያ “የሲቪል ማህበራቱ ያወጡት መግለጫ ስህተት በመሆኑ እርምት በማያደርጉት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።

አገር በቀል ናቸው የተባሉትና 35 የሚደርሱ ሲቪል ማኅበራት በጳጉሜ 01 “በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልል ያለው ጦርነት ” በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እንዲቀጥልና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲቀርብ ያቀረቡት “አስቸኳይ የሰላም ጥሪ” በሀገሪቱ የተከሰተውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበ፣ በህወሃት የተፈጸመውን ጥፋት ያልገለጸ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ነቅፈዋል።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ማብራሪያ ባደረጉበት ወቅት ዶ/ር አለሙ ስሜ እንዳሉት “ሲቪል ማኅበራቱና ድርጅቶቹ ከህወሃት ጋራ በሚደረገው ጦርነት መንግሥት መደገፍ ካልቻሉ ወይም ካልፈልጉ “ዝም ብለው የተመዘገቡበትን ስራ” ብቻ እንዲያከናውንና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግልጫ ከመስጠት እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ ውጭ “አንፈቅድም” ብለዋል። ሁሉም በተመዘገበበት መስክ ከመስራት ውጭ፣ “መከላከያ ሲዋጋ ሐሞት አፍሳሽ መግለጫ ለሚያወጡ ትዕግስት የለንም” ያሉ ሲሆን “የሚያጠፋውን ተከታትለን በጋራ እናርማለን፣ ከዚያ ያለፈ እርምጃ የሚያስፈልገውንም ለኢትዮጵያ ስንል ርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።
#የዓባይልጅ

See also  ወርቁ አይተነው የዘይት ፋብሪካቸውን እየሸጡ መሆኑ ተሰማ

Leave a Reply