የለሚ ኩራ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት 44,395 ካርታዎችን አስወገደ

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከ44 ሺህ በላይ የሚሆኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ነባር ካርታዎችን ኦዲት አድርጎ ማስወገዱን አሳወቀ ።

በከተማ ደረጃ በወረደው አቅጣጫ መሠረት በመሬት አካባቢ የሚስተዋሉ ለሌብነትና ብልሹ አሠራሮች አንዱ መንስኤ ነበሩ ያላቸውን 44,395 (አርባ አራት ሺህ ሶሰት መቶ ዘጠና አምስት) ካርታዎች የለሚ ኩራ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው እለት እንዲወገዱ ማድረጉ ገለፀ።

በእለቱ የተወገዱ የካርታ አይነቶች ሠባት አይነት ሲሆኑ ለተለያየ አገልግሎቶችም ሲውሉ እንደነበር ተጠቅሷል።

እየተወገዱ ያሉት ካርታዎች በክፍለ ከተማው በመሬት ዙሪያ እየተሠሩ ካሉ የሪፎርም ስራዎች አንዱ ነው ያለው ጽ/ቤቱ ካርታዎች ከ2013 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ተቋሙ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ካርታዎች ተወግደው በአዲስ መልክ ከተማ አስተዳደሩ ያተማቸውን ለመጠቀም ያለመ ስለመሆኑም ተገልጿል።

ካርታዎቹ እንዲወገዱ የተደረገበት ምክንያትም በዋናነት ከዚህ በፊት ታትመው ስራ ላይ እንዲውሉ የተደረጉ ካርታዎች በተለያየ መንገድ የተለያዩ ሰዎች እጅ ላይ ገብተው ለማይገባ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በመደረጉ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የእነዚህ ካርታዎች መወገድ በህብረተሰቡ ዘንድ እፎይታን የሚፈጥርና ለተቋሙ የለውጥ ማነቆ የሆኑ የሌብነትና ብልሹ አሠራር ምንጮች ለማክሰምና ለማድረቅ የሚያግዝ አንዱ የውሳኔ አካል ነው ተብሎለታል።

በሌላ በኩል በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህ ካርታዎች ታትመው ሰው እጅ ላይ የገቡ ካሉ የትኛውንም አገልግሎት እንዳያገኙና ስራ ላይ እንዳይወሉ ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞችና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ማሳወቁን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ገረመው ወርቁ በመልዕክታቸው ጽ/ቤቱ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ህብረተሠቡ በተለያዩ ጊዜአት ሲያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እያደረግ ነው ካለው ጥረት አንዱ ይህ የዛሬው ተግባር አንዱ አካል ነው ያሉት ኃላፊው የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ለመቀራመት የሚሞክሩ አካላትን ከጽ/ቤቱ ጋር ሆኖ ህብረተሠቡ እንዲታገልና እንዲያጋልጥ እንዲሁም አሁን የተጀመረወን ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረውና ማንኛውም ተገልጋይ ምቹና፣ፈጣን እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እያደረግነው ያለውን ጥረት ህብረተሰቡ እንዲደግፍና ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

See also  333 የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት መደምሰሳቸውና 671 መማረካቸው ታወቀ

Leave a Reply