የፍጹም ጸጋዬ ኑዛዜ!! መቀለ መከላከያን ናፍቃለች

በሳምንታት ውስጥ የአገር መከላከያን አፈራርሶ አዲስ አበባን በመቆጣጠር ዳግም አገር እንደሚያስተዳድር ሲያውጅ የነበረው ትህነግ እንኳን ያሰበውን ሊያሳካ አሁንላይ የአመራሮቹ ድምጽ ደብዛ እየጠፋ ነው። ምንም ነገር ሲደረግና ሊደረግ ሲል ውብ አድረገውና በፖለቲካ ድልህ አዋዝተው የሚያቀርቡት አቶ ጌታቸው ከመድረክ ከተጠፉ ስነባብተዋል።

ሽራሮን የተቆጣጠረው በመከላከያ የሚመራው የጥምር ጦር ወደፊት እየገሰገሰ እንደሆነ ለኦፐሬሽኑ ቅርበት ያላቸው ከሚገልጽት ውጪ መንግስት ትንፋሹን ቆልፎ እያካሄደ ባለው ትግራይን ያማጽዳት ተግባር ወደ መቀለ በተቃረበ ቁጥር የትህነግ አመራሮች ስምጥ ይግቡ ሰርጥ የታወቀ ነገር የለም።

የትህነግን ሃይል የሚመሩት የቀድሞ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ” ግዙፍ ሃይል ነው፣ እጅግ ግዙፍም በጣም …” እያሉ ዙሪያውን እንደተቆጣጠተረና ወደፊት እንየገፋ እንደሆነ የመስከሩለት የጥምር ሃይል ከላይ በ አቶ ጊታቸው አየር ሃይል እየታገዘ የበልይነት መያዙን ያልተቀበሉት ብቻ ነበሩ። አቶ ጌታቸው ዘጠና ሺህ ጦር መግደላቸውን በተናገሩ በሁለተኛው ቀን “ኢሳያስ ወረረን” በሚል ክተት ካወጁ በሁዋላ አልተሰሙም።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያስረዱትና መንግስት ሰሞኑን ይፋ ያደርገዋል በተባለው ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ መከላከያ በገባባቸው የትግራይ ወረዳዎችና ከተሞች ሕዝብ ያደረገለት አቀባበል አስገራሚ ነው። መንግስት ባሰለጠናቸው ባለሙያዎች አማካይነት ታጣቂዎች መሳሪያ እያስረከቡ ሰላማዊ አስተዳደር በመሰየም ላይ ናቸው።

በትግራይ የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመርና የትግራይ ህዝብ ከገባበት መከራ ባስቸኳይ እንዲወጣ የተቋቋመው የቴክኒክ ቡድን እግር በግር እየተከተለ አገልግሎት ለማስጀመር እየተጋ እንደሆነና ከመቀለ መያዝ ጋር ተያይዞ ሁክሉንም ጉዳይ ወደነበረበት ለመመልስ ዝግጅት መጠናቀቁ ታውቋል።

“በቆቦና ራያ በኩል ያለው ጦርነት መገባደጃው ተቃርቧል፣ አሁን ላይ ቆቦ ያለው ሃይል ድጋፍ ሰጪ ስለሌለው እጅ መስጠት ወይም ሌላ ነው እጣ ፋንታው” ያሉት መረጃ ሰጪ በዝምታ በተካሂደው ኦፕሬሽን የተሰራውና የተገኘው ድል ለህዝብ ለማቅረብ መቸራሻው መድረሱን አመልክተዋል። በርካታ መማረካቸው ብቻ ሳይሆን የተማረኩት ወገኖች ኑዛዜ እንደሚቀርብም ታውቋል።

“የትግራይ ሕዝብ ላኩን በሁዋላ ማንም አይፈንጭበትም” ሲል የውጭ ጉዳይ ቀደም ሲል ባስታወቀው መሰረት ዘመቻው ትግራይን ከትህነግ መንጋጋ የማላቀቅና የትግራይን ህዝብ ነጻ ማውጣት፣ ከትህነግ በሁዋላ ብሩህ ተስፋና ብሩህ ዝመን እንዳለ ማሳየትና ትህነግ ጠላት ሰርቶ ህዝቡን እንዲገለለ ያደረገበትን ትርክት በመስበር የትግራይ ህዝብ ከወዳጅ የአማራ፣ የአፋር፣ የኤርትራና መላው ህዝብ ጋር ያለ ስጋት የሚኖርበት የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ ከወዲሁ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የሚገልጹ ” ያለፈው ጥፋት አይደገምም” ሲሉ አልመክተዋል” ይህዝብም ተምሯል” ሲሉ አክለዋል። ከስር ሃብሳ አለቃ ፍጹም የተናዘዘው ነው። ፍጹም ሰሞኑንን እጁን ሰጥቶ የተናገረውን ከድምጽ ማስረጃው ክሰር ያድምጡ።

See also  የስንዴ አብዮት!! ኦባሳንጆ [ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ነች] ሲሉ መመስከራቸው ብስጭት ፈጠረ

ፍጹም ጸጋዬ

ሬዲዮ ግንኙነቱ ተቋርጧል።የስልክ መስመሮች ድምፅ አልባ ሆነዋል።የከተማው መብራት ጠፍቷል።የወታደራዊ ሬዲዮ ግንኙነት ክፍል አባላት የቅርብ አለቃቸውን ከበላይ አመራርጋ የሚያገናኘውን አዲስ የግንኙነት መስመር ፈጠሩ።

የሀገሪቱ ጦር የሰላ ጫፍ ለይ ያሉ ሰው በከበባ ውስጥ ያሉትን አዛዥ ለማነጋገር መስመር ለይ ተገኙ።ብርጋዴዬር ጄነራሉ ቀርበው በግራ እጃቸው የሬዲዮውኑን እጀታ ወደ ጆሯቸው አስጠጉ።በእልህ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ እጃቸው ጥይት በላንቃው የጎረሰ ሽጉጣቸውን እንደያዙ ናቸው።

እጅግ አስገምጋሚ ወታደራዊ ድምፅ በሞገድ ውስጥ መጣ።”አዝናለው እንዳለን ወዳጅነት!እንደመሪ እና ተመሪ ግንኙነታችን ልባዊ እና ጥልቅ የሆነ ሰላምታ ለመለዋወጥ የሚሆን ጊዜ የለንም።እስክንደርስለህ ድረስ ባለህ ነገር ሁሉ ተፋለም።ታንኮችህ ቀጥታ ተኩስ እየተኮሱ እንዲሁም የጠላትን ሀይል እየደፈጠጡ አንተ ወዳለህበት ማዘዣ ጣቢያ እንዲመጡ አድርግ።ከዛ ሀይልህን ይዘህ ጎረቤት ሀገር ግባ።”አሉ።ድማፃቸው ከወትሮ ወፈር ብሎ ቁጣ ይነበብበታል።

አዛዡ የተዳከመ እና የተሳለች በሚመስል ድምፅ”እሱን አልችልም።ብረት ለበሶቹም ሆኑ ታንኮቹ የሞሉት ነዳጅ እኔ ወዳለሁበት ማዘዣ ጣቢያ አያደርሳቸውም።ቀድመን የተዘጋጀነው ከፊት ለሚመጣ በአድ ጠላት እንጂ በወገናችን ከጀርባችን እንወጋለን ብለን አይደለም።”አሉ።ጡቁሩ የጦር ሰው ቀጠሉ።”መድፎችስ ባሉበት ሆነው እየተኮሱ ድጋፍ እንዲሰጡህ ማድረግ አትችልም!?”

“አለቃዬ!እርሶም እንደሚያውቁት ዳንሻ ያለንበት ካንፕ በህዝብ መሀል ይገኛል። የመጀመሪያው ጥይት ሲተኮስ ያረፈበትን አይቶ ለማረም ያስቸግራል።ከረዘመም ካጠረም ህዝባችን ለይ ይወድቃል።ያ ከሚሆን ደግሞ እኛ ብናልቅ ይሻላል።” ቆፍጠን ብለው መለሱ።

“ካንተ የቅርብ ርቀት ለይ ያሉት ሀይሎች የተሻለ ከፍታማ ቦታ ለይ ስላሉ እራሳቸውን ለመከላከል ጥቂት ሰው በቂ ነው።ስለዚህ የተወሰነ ሀይል ቀንሰው እንዲልኩልህ አድርግ።” ሲሉ ትዛዝ በሚመስል መልኩ ተናገሩ።

በተዳከመ እና በተሰላቸ ድምፅ “ጠላት ቀድሞ ተዘጋጅቶበት ስለሆነ ዲሽቃ እና መትረየስ የታጠቀ የተወሰነ ሀይል እንዳንገናኝ እና በተኩስ እንዳንተጋገዝ መሀል ለይ አስቀምጧል። ቢሆንም ግን ትንሽ መሰዋዕትነት ከፍለው የጠላትን ሀይል ሰብረው ለመምጣት ውጊያ ለይ ናቸው። እኔ እና አባላቶቼ ተሳክቶላቸው ይመጣሉ ብለን በብዙ ተስፋ እናደርጋለን።ከዛ እናንተ እስክደርሱ እራሳችንን እና የተቋሙን ትጥቅ እና ንብረት በጠላት እጅ እንዳይገባ እንከላከላለን።”አሉ።

See also  ከሱዳን ሰርጎ ህዳሴ ግድብን ለማስተጓጎል የገባ የትህነግ ተላላኪ ተደመሰሰ፤ " ምቱ ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ ነው"

ባለ ብዙ ኮኮቡ የጦር ሰው ቀጠሉ።” ባንተ የፀና እምነት አለኝ።ቀጥዬ የምነግርህ መመሪያ ነው።ልብ ብለህ አድምጠኝ።ካንተ ስር ያሉት አባላቶችህ ተስፋ ቆርጠው መዋጋታቸውን እንዳያቆሙ።ይህ ሆኖ ጠላት የድል መንፈስ እንዳይላበስ።ለዚህም ሲባል ለአንተ መሞትም ሆነ መማረክ በፍፁም አልፈቅድልህም።መልካም እድል።”ግንኙነቱ ተዘጋ። ከሌላኛው ካንፕ ወደ ማዘዣው ካንፕ ድጋፍ ለመስጠት የተወሰነ ሀይል ይዘው ይመጡ ከነበሩት ሁለቱ ኮረኔሎች አንዳቸው ቆስለው ከቡድኑ አንድ ሰው ሰውተው ከግቢው ደረሱ።

አዛዡ የነፍስ ወከፍ ኤኬም መሳሪያ ከዘጠና ጥይት ጋር የታጠቁ የእስታፍ አባላትን ይዘው በልበ ሙሉነት ገጠሙ።እንደ ጄነራል አዋጉ።እንደተራ ወታደር ተዋጉ።የግል አጃቢዎቻቸው እና ሹፌራቸው የታጠቁትን ቦንብ ወደ ተጠጋቸው የጠላት ሀይል ለይ ወረወሩ።ከፊታቸው ከተደቀነው ጠላት ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከሚወጋቸው ጡት ነካሽ ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ በዛች ጠባብ ግቢ ውስጥ እውን ሳይሆን ፊልም በሚመስል መልኩ አደረጉ።

በውጊያውም ጥቂት ጓዶች ተሰው ብዙዎቹ ቆሰሉ። ሀረር እና አለሙን የመሰሉ ጀግኖች እየተፋለሙ አብረዋቸው በበሉ በጠጡ ጓዶቻቸው ከጀርባቸው ተመተው ወደቁ።ሀረር ተመልሶ አልነቃም።

የመከላኪያ ኮማንዶ የአማራ ልዩ ሀይል ሶረቃ ለይ የነበረውን ጠላት ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር ደምስሰው ከፊታቸው ያገኙትን እየመነጠሩ አዛዡ የተከበቡበት ግቢ በአጥር እየዘለሉ ገቡ።

የሞት ሽረት ትግል ለይ የነበሩት አባላት አይናቸውን ማመን አቃታቸው።ጀግናው ኮማንዶ የአማራ ክልል ልዩ ሀይሎች ከምድር ይፍለቁ ከሰማይ ይዝነቡ እስካሁንም መልስ ያላገኙለት ጉዳይ ነው።

ክብር እና ምስጋና በጦር ሜዳ ውሎ ከመከላኪያ ሰራዊቱ ጎን ተስልፈው ለተዋደቁ የክልል ልዩ ሀይሎች!!

( ፎቶ ዳንሻ ለይ እነ ጄነራል ሙላለምን ከውስጥ ሆኖ የወጋቸው እና ለጠላት መረጃ እየሰጠ ያስጨፈጨፋቸው ሀምሳ አለቃ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሀኔ!!)

Leave a Reply