መንግስት ትህነግ በድርድሩ “አማጺ ቡድን” ተብሎ እንዲጠራ አሳሰበ

ለግማሽ ምዕተ ዓመት ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” በሚል ስያሜ የሚጠራውና በዚሁ በተገንጣይ ስም ኢትዮጵያን ለሃያ ሰባት ዓመታት የመራው ቡድን በትክክለኛ ስሙ እንዲጠራ መንግስት ህገመንግስት ዋቤ አስድርጎ ማሳሰቢያ ሰጠ።

በመንግስት የፋክት ቼክ በይፋ እንድተባለው እንደተጠቆመው ትህነግ ትግራይ ሆኖ ለራሱ እየሰጠ ያለው ስም፣ ይህንኑ ስም አንዳንድ ሚዲያዎችና ተቋማት መጠቀማቸውን አግባብነት የጎደለው እንደሆነ በደፋናው ተቃውሟል። “አማጺ ቡድን” በሚል ሊጠራ እንደሚገባውም አመልክቷል።

የሚደረገው ድርድር በአንድ ሕዝብ በመረጠው መንግስትና በአማጺ ቡድን መካከል እንደሆነ መንግስት በይፋ ተናግሯል። በትግራይ ህዝብ የመረጠው ህጋዊ አስተዳደር እንደሌለም ህገመንግስት አመላክቶ በማስታወቅ ምክንያቱን ገልጿል።

የምርጫ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ ከአገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህግና ደንብ ውጪ ምርጫ በማካሄድ ለራሱ እውቅና የሰጠው ትህነግ በወቅቱ ምርጫ ቦርድ እውቅና እንደማይሰጠው በደብዳቤና መንግለጫ ደጋግሞ አስታውቆት እንደነበር ይታወሳል።

የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር ቆይቶ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ምርጫ ያደረገው ትህነግ በወቅቱ መንግስትን እንደማይቀበል፣ እሱ ብቻ ህጋዊ ምርጫ አካሂዶ ስልጣንን ከህዝብ የተረከበ መሆኑንን በማወጅ፣ “የፌደራል ሃይሎች” በሚስጢርና ነገሃድ ካሰባሰባቸው ድርጅትና ገለሰቦች ጋር በመሆን የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እንደሚሰራ በወቅቱ አመልክቶ ነበር። ትህነግ በወቅቱ ከፍተኛ የሰራዊት ሃይልና አቅም አሰባስቦና አዘጋጅቶ ስለነበር የማዕከላዊ መንግስትን ለማስወገድ ሳምንታት እንደማይፈጅበትም አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።

በአገሪቱ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የብልጽግና ፓርቲን አፈራርሶ ለማስወገድ ሰፊ ዘመቻ ቢደረግም ምርጫው ተካሂዶ ተጠናቀቅ። ከምርጫው መጠናቀቅ በሁዋላ ትህነግ ደብረሲናን አልፎ ወደ ደብረብርሃን ሲጠጋ “ከማን ጋር ነው የምንደራደረው” በሚል የትህነግ መሪዎች የሰላም ንግግርን ማጣጣላቸውም አይዘነጋም።

የትህነግ ሃይሎች በሳምንታት ውስጥ በሃይል ከያዟቸው አካባቢዎች እንዲለቁ ከተደረገ በሁዋላም ሆነ ከዚያ በፊት የሰላም ንግግርን በቅድመ ሁኔታ አጅቦ ሲያቀርብ የነበረው ትህነግ በቅርቡ ቆቦን ከመያዙ በፊት ” መንግስትን አፍንጫውን ይዘን የምንፈልገውን ሁሉ እናስፈጻማለን” በሚል መግለጫና ቃለ ማብራሪያ አሰምተው ነበር።

ትግራይን ለቆ መውጣቱን ካስታወቀ ጀምሮ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንን፣ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ እንደምያስፈልግ ጠቅሶ አቋሙን ያንጸባረቀው መንግስት በሳምንቱ መጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ላቀረበው የሰላም ንግግር ቅድሚያ አዎንታዊ ምላሺን ሲሰጥ የትህነግ አመራሮች በበኩላቸው ዘገየት ብለው ጥሪውን ተቀብለው ለንግግር ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚሄዱ ከመለስተኛ ማብራሪያ ጋር አስታውቀዋል።

See also  «ሂዱ አማራንና አፋርን እንዲሁም ቀሪዉን የኢትዮጵየሠ ህዝብ ውረሩ፣ ሀብት ንብረቱንም ዝረፉ ኢትዮጵያንም አፍርሱ…»

ቀደም ሲል “ስንፈግል ዳግም እንይዘዋለን” በሚል ከአማራ ክልል በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ገልጸው የነበሩት የትህነግ አመራሮች በራሳቸው ደጋፊዎች ሳይቀር ተቃውሞ እየተሰነዘረባቸው ከርመው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሰላም ንግግር እንደሚያመሩ ሲያስታውቁ ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጡም። ይልቁኑም ያነሱት የድህነነት፣ የሎጂስቲክና የሌሎች ታዛቢዎችን መኖር ነበር።

ከስልጣን እርከናቸው፣ እንዲሁም ህገ መንግስቱን በሚጻረር መልኩ በቀጥታ ለተመድና ለተለያዩ አገራት ደብዳቤ በመጻፍ እንደ አንድ መንግስት የመታየት ፍላጎታቸውን ሲያንጸባርቁ ቢከርሙም መንግስት በስተመጨረሻ ድርድሩ ላይ የስያሜ ስህተት መኖሩን አብራርቶ እንዲስተካከል መጠየቁ በበርካቶች ዘንድ ደስታን ፈጥሯል።

“ትህነግ አማጺ እንጂ የትግራይ ባለቤትና አስተዳዳሪ አይደለም። ትግራይ ኢትዮጵያ ናት። እሱም ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል የሚነከላወስ ወንበዴ ነው።” በማለት የመንግስት መገናኛዎች ሳይቀሩ የስያሜ ግድፈት ሲፈጽሙ እንደነበር በርካቶች አስተያየት ሲሰጡ ቆይተው ነበር።

መንግስት የሃይል የበለይነቱን በያዘበትና የትግራይ አካባቢዎችን ከወራሪው አማጺ የትህነግ ጭፍራ ነጻ ባወጣበት በአሁኑ ወቅት ትህነግ ከመደራደር ውጭ ምንም አማራጭ እንደሌለው የሚገልጹ ታሪኩን “ግጥምጥሞሽ” እያሉት ነው። በ1983 ሎንዶን ላይ ድርድር ሲደረግና ኢትዮጵያን ወክለው የነበሩት ባለስልጣኖች ከድርድሩ ሲወጡ አገር አልባ መሆናቸውን ያወሱ፣ ” አሁንም መቅለ ዙሪያዋ ተከቦ የሚደረግ ድርድር ከአዳራሹ ሲወጣ ሌላ ታሪክ ሊያሰማ ይችላል” ይላሉ።

ምክንያቱ ባይታወቅም አንዳንድ መረጃዎች ለድርድር ከመቀለ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱትን አካላት ለመሰየም መግባባት ላይ እንዳልተደረሰ እየተገለጸ ነው። እንደውም ከተማዋን ለቀው የወጡ ባለስልጣናትም እንዳሉ እየተነገረ ነው። በድርድሩ ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለስልጣናት መሰወራቸው ተሰምቷል። ወታደራዊ አመራሮች የከረረ አቋም ይዘዋል።

በዚህ ሁሉ መሃል ነው መንግስት ንግግሩ ከአማጺ ወንበዴ ጋር መሆኑንን ጠቅሶ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳሰቢያ ያሰራጨው።

Leave a Reply